📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ለንባብ ይበቃል
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበትን"እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ ይበቃል።
"እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ከቅጽ አንድ የቀጠለ ሲሆን በቅጽ ሁለት መጽሐፍ "ስንክሳር" የሬድዮ ዝግጅት ላይ ከቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ውስጥ ለቅምሻ እንደተካተተበት ተነግሯል።
ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በመጽሐፉ የቅምሻ ክፍል ላይ የሚከተለውን ብሏል"ቅጽ አንድን ሳዘጋጅ የእኔን የሙያ ትሩፋት ለመስጠት ሳይሆን በእኔ ዘንድ ያለውን ለእናንተ ማካፈል ደስታን ስለሚሰጠኝም ጭምር ነው፡፡ በቅጽ ሁለት ቀሪዎች ስራዎችን ለእናንተ ለማድረስ ደፋ ቀና ስል አንድ ሀሳብ ውስጤ ተጫረ፡፡ ስንክሳር።ስንክሳርን ብዙ የሚዲያ ወዳጆቼ ሰምተው የተደመሙበት የተማሩበትና የተዝናኑበት እንደሆነ ሲነግሩኝ ከርመዋል፡፡ ስንክሳር በተለያዩ ጉዳዮች ማለትም በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነቶች ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሥራ ነው፡፡እነሆ ማሟሻ ስታድግ በወርድና ስፋቷ ስንከሳርን ታክላለች፡፡ እና ለወዳጆቼ ለምን ስንክሳርንስ አላጋራም? ነበር ውስጤ የተጫረው ሀሳብ። ከብዙ ስራዎቼ ለሚቀጥሉት ህትመቶች በር መክፈቻ ብትሆን እነሆ የስንከሳርን ቅምሻ ላቀርብ ወደድኩ"።
መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን ከአርብ ጀምሮ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፤ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌የሐና ግርማ አዲስ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል
የወጣቷ ድምጻዊት ሐና ግርማ "ምን መሰለህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ነገ አርብ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድ በኩል ይለቀቃል። በዚህ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አቡዲ፣በቅንብርና ማስተሪንግ ታምሩ አማረ፣በሙዚቃ ቪዲዮ ዳይሬክቲንግ ዮሴፍ ባዬ ተሳትፈውበታል።

📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት መርሐግብር
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ አቀናባሪው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ እና ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረማሪያም (ኪንግ ሶሎን )ጨምሮ በሲያትል ከተማ እውቅና ተሰጣቸው ።
ደዊት ፅጌ በ2024 በአሜሪካን ከተሞች ያቀረባቸው የተሳኩ ዝግጅቶች በማስመልከት እና ልዩ ተስጦ ያለው ድምፃዊ በመሆኑ ለሙዚቃው ላበረከተው አስተዋፆ ጭምር እውቅና አግኝቷል።
የሙዚቃ አቅናባሪው አበጋዝ ሺዎታ በኢትዮጵያ የምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁ እውቅና በክብር ተሰጥቷቸዋል።
በተያያዘ ዜና - የኪንግ ሶሎ ፕሮሞሽን ባለቤት ፕሮሞተር ሰለሞን ላለፉት 10 ዓመት በሲያትል ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እውቅና ተሰጥቶታል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሃያላኑዋ አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከሚንቅሳቅስባቸው ዋንኛዋ ከተማ የሆነው ሲያትል ዋሽግተን ምክትል ከቲባዋ መሆናቸው ለኢትዮጵያን ትልቅ ኩራት መሆኑ ተገልጿል።
ድምፃዊው እና ሙሉ ባንዱ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
በቅርቡም በአዲስ አበባ ትልቅ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁም ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

📌"የሚልየነሮች መንገድ" የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
በበላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል የተዘጋጀውና በርካቶችን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት "የሚልየነሮች መንገድ' የተሰኘ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።
"የሚልየነሮች መንገድ" የፕሮጀክት ሀሳብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ ቢዝነስ ፕላን ለወጣቶች፣ለጀማሪ ነጋዴዎች፣ በቢዝነስ ላይ ላሉ ሁሉ የሚጠቅም የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት እንደሆነ ተነግሯል።
በላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ስለሚያደርገዉ "የሚሊየነሮች መንገድ" ፕሮጀክት ባስተዋወቁበት መድረክ "ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት በርካታ አዋጭ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ጥናቱን ሲያካሄድ ቆይቶ በልምድ የተረጋገጠ የአስር ዓመት አዋጭ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት የዛሬ ሰባት ዓመት በ500 ብር መነሻ ካፒታል አምስት ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ በማስገባት ብቻ የጀመሩትን ቢዝነስ አሁን ባለበት ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አምስት መሸጫ ቦታዎች ትላልቅ የአትክልትና አስቤዛ ማዕከል ቅርንጫፎችን በመክፈት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባሻገር በቋሚነት ከ75ሺ በላይ ደንበኞችን በማፍራት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል "ብለዋል።
ማዕከሉ በቅርቡም "የሚሊየነሮች መንገድ" የተሰኘ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከጥቅምት 30 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እና በሀገሬ ቴሌቪዥን ላይ እንደሚጀምር አስታውቋል።

📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት ተካሄደ
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ተካሄዷል።
በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ በሰባት ዘርፎች አስር ለሚሆኑ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ መሰረት ተሸላሚ ተቋማትና ግለሰቦች ዝርዝር ታውቋል።
1.የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (በሚዲያ ዘርፍ)
2. አንድነት ፓርክ (በመዳረሻ ልማት ዘርፍ)
3 ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢኒስቲትዩት (በቱሪዝም ተቋማት ዘርፍ)
4.ሀይሌ ሆቴሎች (በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ )
5.ሔኖክ ያሬድ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)
6.ጋዜጠኛ ፀሐይ ተፋረደኝ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)
7.አንቶኒዮ ፍዮርንቴ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )
8.ህሊና ታፈሰ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )
9.ኪሮስ ኃ/ስላሴ (በ"ኢትዮጵያን እንቃኝ" ልዩ ተመስጋኝ )
10.ቴዎድሮስ ደርበው (በቱሪዝም ባለሞያ ዘርፍ)

📌አሻም ቲቪ የስያሜ ለወጥ አያደርግም ተባለ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍተሐብሔር ምድብ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 228079 በቀን 20/08/2014 ዓ.ም እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 229220 በቀን 21/10/2016 ዓ.ም አሻም የሚለውን ስያሜ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለማስፈጸም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአሻም የማሳሰቢያ ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል፡፡
በዚህም ፍርዱ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ አሻም የሚለውን ስያሜ መጠቀም እንድታቆም እና እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አዲሱን ስያሜ አሻም እንድታሳውቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷት ነበር።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ፍ/ብሔር ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት የፍርድ ባለዕዳ ‹‹ አሻም ›› በሚል ስያሜ በመጠቀም የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንዲያስቆሙ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ለፌደራል ፖሊስ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡
ይሁንና የፍርድ ባለመብት (ኢካሽ የማማከር፣ ስልጠናና ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ) እና የፍርድ ባለዕዳ (አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ) ጉዳዩን በእርቅ ለመፍታት ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የእርቅ ሥምምነቱ ህግንና ሞራልን የማይቃወም መሆኑን በመረዳት እርቁን ተቅበሎታል፡፡
ፍርድ ቤቱ አክሎ እንደተናገረው ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ሰጥቶ የነበረው የአፈጻጸም ትዕዛዝ በዚህ ተለዋጭ ትዕዛዝ ቀሪ በማድረግ እንዲሁም ይህንን የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተከትሎ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊሲም ሆነ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተሰሩ ሥራዎች ያሉ ከሆነ ቀሪ እንዲደረግ አዝዟል፡፡

📌የጉማ አዋርድ የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል
የኢትዮጵያ ፊልሞችንና ፊልም ስሪዎችን ለዘጠኝ ዓመታት እየሸለመ የቆየው ጉማ አዋርድ ዘንድሮ ለአስረኛ ጊዜ የሽልማት ሥነሥርዓቱን ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
የዘንድሮውን ሽልማት አስመልክቶ የሽልማቱ አዘጋጆች" በ2015 ዓ.ም በሀገራቸን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 32 ፊልሞች ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪም ከጉማ ጅማሬ አንስቶ በተለያዩ ሙያተኞች ሲጠየቅ የነበረው የተከታታይ ፊልም ምድብ እና የዘጋቢ ፊልሞችን በዚህ ዓመት እንዲካተቱ ተደርጓል"ያሉ ሲሆን
በተጨማሪም"በዚህ ዓመት ዘርፎቹ ወደ 29 ከፍ ያሉ ሲሆን የጉማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍ ፤የጉማ የሄርሜላ የሴቶች ሽልማት ተሸላሚ፤ የጉማ የበጎ ስራ ተሸላሚ ብቻ ያለ ውድድር በኮሚቴው ጥናትና ምርጫ ተወሰኗል"ብለዋል።
ከቀናት በፊትም የጉማ አዋርድ ዕጩ ፊልሞች ይፋ ተደረገዋል። ዶቃ ከ16 ዘርፍ በ14ት ዘርፍ ታጭቶ ከፊት ይገኛል፣ ወዳጅ እና ዝምታዬ ፊልሞች በ10 ዘርፍ ይከተላሉ፣ ልባም ፊልም በ9 ዘርፍ በመታጨት 3ተኛ ነው፣ ገምዛ እና የአገር ምስጢር አለኝ በ8 ዘርፍ በመታጨት አራተኛ ላይ እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

📌"ሶስት አይጦች" በልዩ ዝግጅት ይቀርባል!
በኤልያስ ተስፋዬ ተደርሶ በካሌብ ዋለልኝ የተዘጋጀውና ዘወትር ማክሰኞ በ11:00 የሚታየው "ሶስቱ አይጦች" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ጥቅምት 8 አርብ በ11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚቀረብ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በኤልያስ ተስፋዬ ተደርሶ በካሌብ ዋለልኝ የተዘጋጀውና ዘወትር ማክሰኞ በ11:00 የሚታየው "ሶስቱ አይጦች" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ጥቅምት 8 አርብ በ11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚቀረብ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል
በፍፁም ወንድወሰን የተዘጋጀው "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።
"ይፈለጋሉ" ፊልም ላይ ሰለሞን ሙሄ፣ ቃልኪዳን ታምሩ፣ ዋሲሁን በላይ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።
የደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ወንድወሰን "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ አርብ በ8፣ በ9 እና በ10 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በእኩል ሰዓት ይመረቃል ተብሏል።

📌የቀደሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ተሾመች ።
በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በሌሎችም የብዙሃን መገናኛዎች ላይ በጋዜጠኝነት የሰራችው የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለከታል።
የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴአታ በመሆን እያገለገለች እንደነበር ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በሌሎችም የብዙሃን መገናኛዎች ላይ በጋዜጠኝነት የሰራችው የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለከታል።
የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴአታ በመሆን እያገለገለች እንደነበር ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌የ10ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች ዝርዝር!
አስረኛው የጉማ አዋርድ የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በደማቅ ሁኔታ እንደተካሄደ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
የዘንድሮው የ #ጉማ አዋርድ ሽልማት አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል።
📌 የህይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፍቅርተ ደሳለኝ
📌 አርአያ ሰብ ከያኒ፦ ይገረም ደጀኔ (አስቴር)
📌 የሐርሜላ ተሻላሚ፦ አዜብ ከበደ
📌ምርጥ አጭር ፊልም፦ "የራስ ጠላት" እስክንድር አብርሃም
📌 ምርጥ የተማሪዎች አጭር ፊልም፦ "እንደ .." ናርዶስ ይልማ
📌ምርጥ ዶክመንተሪ ፊልም፦"እረኝነት"ብሩክ ሞላ
📌ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይት፦ መዓዛ ታከለ (አፋፍ)
📌ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ፦ አበበ ባልቻ "በህግ አምላክ"
📌 ምርጥ ድራማ፦ "እንደ አንድ"
📌 ምርጥ ድምፅ፦ አበበ አሰፋ እና ቢንያም ሰለሞን (ዶቃ)
📌ምርጥ ኤዲተር፦ ነብዩ ሰዓዲ እና ልዑል አባዲ (ዶቃ)
📌ምርጥ ስኮር፦ እዮኤል መንግስቱ (በዶቃ )
📌ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ ሙሉዓለም ተከለ ፣ ዘቢባ ግርማ እና አቤል ሀጎስ( ወዳጅ)
📌ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ብስራት ጌታቸው እና ሰደኪያል አየለ ( ዶቃ )
📌ምርጥ ሜካአፕ፦ ዳግማዊ አለማየሁ (ዶቃ)
📌ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ ቤዛ ሀይሉ እና ቅድስት ይልማ (ዶቃ)
📌 ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ መቅደላዊት ግርማ "(ሌባ እና ሌባ)
📌 ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ በረከት ግዛቸው (ጭረት )
📌ምርጥ ረ/ተዋናይት፦ ድርብወርቅ ሰይፉ (ዶቃ)
ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ ቴዎድሮስ ተሾመ (ዝምታዬ)
ምርጥ ተዋናይት፦ ቃልኪዳን ጥበብ (ልባም)
📌 ምርጥ ተዋናይ:- ሙሉዓለም ጌታቸው (ገምዛ)
📌የተመልካች ምርጫ፦ ወዳጅ ፊልም
📌 ምርጥ ዳይሬክተር፦ ቅድስት ይልማ (ዶቃ)
📌 ምርጥ ፊልም፦ ዶቃ
ከ16ቱ ዘርፎች ከግማሽ 9ኙን ሽልማት በመውሰድ "ዶቃ" ፊልም ከፊት ይገኛል፣ "ወዳጅ"ፊልም ሁለት ሽልማቶችን "ሌባ እና ሌባ፣ ልባም፣ ገምዛ፣ ዝምታዬ እና ጭረት ፊልሞች ደሞ አንድ አንድ ሽልማቶችን ወስደዋል።
©️መረጃው የጋዜጠኛ ፅዮን ታምራት ነው።
ለተጨማሪው: @EventAddis1

❤1