Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"የቅርብ ሩቅ" ተውኔት ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በእሸቱ ዱብ ተደርሶ በተስፋዬ ገብረማርያም የተዘጋጀው "የቅርብ ሩቅ" ተውኔት ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለመድረክ ይበቃል።በተውኔቱ ላይ ሉሌ አሻጋሪ፣ሔኖክ በሪሁን፣ቅድስት ብሩክ፣ናትናኤል መኮንን፣ብሩክታዊት እሸቱና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ሊመረቅ ነው

በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።

በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።

የተውኔቱ የምርቃ ሥነሥርዓትም የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል። እንዳትቀሩ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ አሸንፏል

ሁለተኛውን የኢጋድ የ2024 የሚዲያ አዋርድ ኢትዮጵያዊው ወጣት ጋዜጠኛ ምስክር አወል አሸናፊ ሆኗል።

ጋዜጠኛ ምስክር "Narratives of Hope: Inspiring Peaceful, Secure, and Inclusive Future." በሚል ሃሳብ ላይ ተወዳድሮ ነው ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋዜጠኞች ቀዳሚ መሆንና ማሸነፍ የቻለው።
ሽልማቱንም በኬንያ እየተካሄደ ባለው የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ ስነ ስርዓት ላይ ተቀብሏል።

ጋዜጠኛ ምስክር ቀደም ሲል በሸገር ራዲዮ የሰራ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢቢሲ የብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያው ባልደረባ ነው።

መረጃው: የ https://news.1rj.ru/str/AhunawiMereja ነው።

ለትኩስ መረጃዎች "አሁናዊ" ቴሌግራም ይቀላቀሉ።
Channel name was changed to «Event Addis Media»
Channel photo updated
📌EVENT ADDIS MEDIA

በቅርብ ይጠብቁን!!
📌"ክንፋም ከዋክብት" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

50 ገጣሚያን የተሰባሰቡበት "ክንፋም ከዋክብት" ቅጽ አንድ የግጥም መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም የተመረጡ ግጥሞች በገጣሚያን፣አጭር ሂሳዊ ዳሰሳ፣አኩስቲክ ሙዚቃ ጨዋታን ጨምር ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ይከናወናሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ


📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: አርብ (በልዩ ዝግጅት )
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አይዞን" ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል 

ድምጻዊ አብዱ ኪያር እና ናትናኤል አያሌው (ናቲ ማን) የተጣመሩበት "አይዞን" የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
   
በዚህ ኮንሰርት አብዱ ኪያር የተለያዩ ተወዳጅ ስራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን እንዲሁም ናቲ ማን ከረጅም ዓመታት በኋላ ስራዎቹን ያቀርባል።

የመግቢያ ዋጋ ፦ ለመደበኛ 600 ብር፣ በር ላይ  800 ብር፣ ለቪአይፒ ደግሞ 2000 ብር ሲሆን ትኬቶችን በሚሊንየም አዳራሽ፣ ቦሌ ፍሬንድሺፕ በሚገኘው ቻካ ኮፊ፣ 22 በሚገኘው ቻካ ኮፊ፣ ፊሊ ኮፊ ሜክሲኮ፣ አትላስ ቸሩ መድሀኒአለም፣ ይማና ክትፎ እንዲሁም ቴሌ ብር ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጠረፍ ካሣሁን አዲስ ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል

የድምጻዊት ጠርፈ ካሣሁን(ኪያ) "ለምን ብዬ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል።

በሙዚቃው ላይ በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ በዜማ ብስራት ሱራፌል፣ በቅንብር ናኦል ኤቤሳ ተሳትፈውበታል።

ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን ከወራት በፊት "ጥሉ ከማን ነው?" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ለአድማጮች ማድረሷ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ድምጻዊት ሌሊ ሌንሳም "ሳድግ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊት ሌሊ ሌንሳሞ "ሳድግ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃዋ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቂቃዎች በፊት በራሷ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

"ሳድግ" ሙዚቃ ግጥምና ዜማው በራሷ በሌሊ ሌንሳሞ የተሰራ ሲሆን ሚክስንግና ማስተሪጉን ዳጊ ሙዚየክ ሰርቷል።የሙዚቃው ቪዲዮው ላይ ሮብ ፕሮዳክሽን ተሳትፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የፍሬዘር ቀናው "ጀሚላዋ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊ ፍሬዘር ቀናው (ባቢ) " ጀሚላዋ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአድማስ ሙዚቃ ዩቲዩብ ቻናል ተለቋል።

"ጀሚላዋ" ሙዚቃ ግጥም በጥላሁን ሠማው ዜማ በአቡዲ ሙዚቃ ቅንብርና ሚክሲንግ በታምሩ አማረ ተሰርቷል። የሙዚቃው ቪዲዮ ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን ነው።

ድምጻዊ ፍሬዘር ቀናው ከዚህ ቀደም "ውሎ መጀን" ፣ "ሙሐባ" ፣ "ናፍቀሽኛል" እኔ ሌሎችም ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌#ኖህ ሪል ስቴት

ኖህ ሪል ስቴት ዛሬ ጥቅምት 16 2017 ዓ.ም ከ750 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን ለድንበኞቹ አስተላልፏል።

ኖህ ሪልስቴት ዛሬ ያስረከባቸው ቤቶች ሰሚት አከባቢ "ኖህ ኤርፖርት ድራይቭ ሳይት" የተሰኘ ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ለቤት ባለቤቶች የተላለፉት መኖሪያ ቤቶች ከ75 ካሬ እስከ 128 ካሬ ስፋት ያላቸው መሆናቸውን ተነግሯል።

ቤቶቹ ከባለ 2 እስከ ባለ 3 መኝታ ክፍሎች ያሏቸው 750 በላይ አፓርታማ የመኖሪያ ቤቶች፣ 32 በላይ ቪላ ቤቶች እና 45 የንግድ ሱቆች ናቸው።

ኖህ ሪልስቴት ዛሬ ያስረከባቸው መኖሪያ ቤቶች መዋኛ ገንዳ፣ የከርሰ ምድር ውሃ እንዲሁም የስፖርት ማዘወተሪያ ያካተቱ መሆናቸው ተገልጿል።

የኖህ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ አዋሽ  ኖህ ሪል ስቴት የመኖሪያ አፓርተማዎችን በጊዜ እና በጥራት በመገንባትና በማጠናቀቅ ኩባንያው የደንበኞቹን እምነት ያተረፈ ኩባንያ ነው ብለዋል።

ኩባንያው በቅርቡ በእንቁላል ፋብሪካ "ኖህ አስኳልን" 750 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ፣በአዋሬ ሴቶች አደባባይ "ኖህ ቪክትሪ ሳይት" 152 ቤቶችን  ለቤት ባለቤቶች እንደሚያስረክብ አስረድቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኖህ ሪል ስቴት በቀጣይ ወር በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ቦሌ ሆምስ በሚባለው አካባቢ ከ2500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ግንባታ አስጀምራልሁ ብሏል፡፡

ኖህ ሪል ስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት በ33 ሳይቶች ከ9,800 በላይ የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ማዕከላትን ከ25,000 በላይ ለሚሆኑ ቤት ፈለጊዎች ገንብቶ አስረክቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጎሳዬ ተስፋዬ "ዝም" ሙዚቃ ተለቀቀ

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በሞት ያጣናቸውን የሙዚቃ ባለሞያዎች ያስታወሰበትና "ዝም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውን ነጠላ ሙዚቃ ከደቂቃዎች በፊት ለአድማጮች አድርሷል።

በዚህ የሙዚቃ ስራ ላይ ከአንጋፋዎች ጥላሁን ገሠሠ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ምኒልክ ወስናቸው፣ህሩት በቀለ ከወጣቶቹ ኤልያስ መልካ ፣ሀጫሉ ሁንዴሳ፣ እዮብ መኮንን፣ዳዊት ነጋ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ሚካያ በኃይሉ እና ሌሎችንም የሙዚቃ ባለሞያዎች አነሳስቷል።

በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ ጎሳዬ ተስፋዬ በቅንብር ታምሩ አማረ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት ሚካኤል ታምሬ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር አርቲስት ሚካኤል ታምሬን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን  ማክሰኞ ጥቅምት 19 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል ታምሬ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርት በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው

የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርት የፊታችን ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ በማህበራዊ ትስስር ገፁም “የኔ ዜማ" አልበም ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሙዚቃ ስራዎቼ ከመዝናናት ባለፈ ልዩ አክብሮት እና ፍቅር እንዲሁም ገንቢ አስተያየቶችን ለሰጣችሁኝ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ"

"የኔ ዜማ" ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ጉዞ የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስአበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርታችንን ለማቅረብ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን ሲሆን በዚህ ደማቅ ምሽት ላይ ተገናኝተን የማይረሳ ጊዜ እንድናሳልፍ ስል በአክብሮት እጋብዛለሁ"ብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ አልበም ቅዳሜ ይመረቃል

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ላይ ዘቢባ ግርማ፣ ሀና ግርማ፣ ዚጊዛጋ እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የፊታችን ቅዳሜ መጠሪያዬ የተሰኘው አልበሜን ልናስመርቅ ነው እንዳትቀሩ "ብላለች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሮፍናን ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል

የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ሮፍናን ኑሪ ከሳምንታት በፊት በሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ስኬታማ ኮንሰርት እንዳቀረበ ማስታወቁ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት

"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት ትላንት በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል ተካሄዷል።በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን(ኪያ) እና ድምጻዊት ምንሹ ክፍሌ የሙዚቃ ስራዎቻቸው አቅርበዋል።

ፎቶ: በተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1