Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የጎሳዬ ተስፋዬ "ዝም" ሙዚቃ ተለቀቀ

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በሞት ያጣናቸውን የሙዚቃ ባለሞያዎች ያስታወሰበትና "ዝም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውን ነጠላ ሙዚቃ ከደቂቃዎች በፊት ለአድማጮች አድርሷል።

በዚህ የሙዚቃ ስራ ላይ ከአንጋፋዎች ጥላሁን ገሠሠ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ምኒልክ ወስናቸው፣ህሩት በቀለ ከወጣቶቹ ኤልያስ መልካ ፣ሀጫሉ ሁንዴሳ፣ እዮብ መኮንን፣ዳዊት ነጋ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ሚካያ በኃይሉ እና ሌሎችንም የሙዚቃ ባለሞያዎች አነሳስቷል።

በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ ጎሳዬ ተስፋዬ በቅንብር ታምሩ አማረ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት ሚካኤል ታምሬ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር አርቲስት ሚካኤል ታምሬን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን  ማክሰኞ ጥቅምት 19 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል ታምሬ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርት በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው

የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርት የፊታችን ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ በማህበራዊ ትስስር ገፁም “የኔ ዜማ" አልበም ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሙዚቃ ስራዎቼ ከመዝናናት ባለፈ ልዩ አክብሮት እና ፍቅር እንዲሁም ገንቢ አስተያየቶችን ለሰጣችሁኝ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ"

"የኔ ዜማ" ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ጉዞ የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስአበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርታችንን ለማቅረብ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን ሲሆን በዚህ ደማቅ ምሽት ላይ ተገናኝተን የማይረሳ ጊዜ እንድናሳልፍ ስል በአክብሮት እጋብዛለሁ"ብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ አልበም ቅዳሜ ይመረቃል

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ላይ ዘቢባ ግርማ፣ ሀና ግርማ፣ ዚጊዛጋ እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የፊታችን ቅዳሜ መጠሪያዬ የተሰኘው አልበሜን ልናስመርቅ ነው እንዳትቀሩ "ብላለች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሮፍናን ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል

የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ሮፍናን ኑሪ ከሳምንታት በፊት በሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ስኬታማ ኮንሰርት እንዳቀረበ ማስታወቁ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት

"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት ትላንት በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል ተካሄዷል።በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን(ኪያ) እና ድምጻዊት ምንሹ ክፍሌ የሙዚቃ ስራዎቻቸው አቅርበዋል።

ፎቶ: በተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ዳናሽ” ፊልም ዛሬ ይመረቃል

በአብርሃም ታደሰ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው "ዳናሽ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም  በዓለም ሲኒማ ተመርቆ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በ"ዳናሽ" ፊልም ሔኖክ በሪሁን፣ ኤደን አይሹሽም፣ጌታቸው ስለሺ፣ ምስክር ተስፋዬ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈዋል።

በኢነርጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በቆንጆ ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በየሚ ፒክቸርስ አማካኝነት ለሕዝብ እንዲቀርብ የተሰናዳው ፊልም በዓይነቱ ለየት ያለ እና ጠንካራ ሃሳብ ይዞ የመጣ መሆኑን የፊልሙ አዘጋጅ አብርሃል ታደሰ ገልጸዋል፡፡

አጠቃላይ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት እና 1 ሰዓት ከ46 ደቂቃ የሚፈጅ ርዝማኔ ያለው ፊልሙ ለኢትዮጵያ ፊልም ተመልካቾች የሚመጥን ሃሳብ በማንሳት የሚሞግት፣ ብሎም ለመልካም እሴቶቻችን ዘብ እንድንቆም የሚያበረታታ ስለመሆኑ አዘጋጁ አብርሃል ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት በይፋ ተመረቀ !

በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመርቋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥነ-ጥበብና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በቴአትሩ የአንድ ዓመት ጉዞ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሞያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።

@EventAddis1
📌የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ

የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት ተወዳጅ መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀረበዋል።

በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉትና ከገበያ ጠፍተው የነበሩ የበዕውቀቱ ስዩም "መግባት እና መውጣት" ፣"ስብስብ ግጥሞች" እና "ከአሜን ባሻገር የተሰኙ ሶስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል::

ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም  በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይህን መልዕክት አስፍሯል"ውድ የመጽሀፍ ወዳጆች! ከገበያ ጠፍተው የነበሩት የበእውቀቱ ስዩም መጻሀፍት መካከል ፥ መግባት እና መውጣት፥ ስብስብ ግጥሞች እና ከአሜን ባሻገር ' በድጋሜ ታትመው ለገበያ ቀርበዋል፤ መግዛት ወይም መሸጥ የምትፈልጉ ፥ ለገሐር አመልድ ህንጻ፥ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አይንአለም መጽሀፍ መደብር ጎራ በሉ፤ ስልክ  0911814536"።

መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1