Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ለዕይታ ሊቀርብ ነው

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ባለ ቀለም ፊልም ወደ ዲጂታል አስቀይሮ ሊያስመርቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽን አማካኝነት ሀገራዊ ዘዉግ ላይ ተንተርሶ የተሰራውና "አስቴር" የተሠኘው አትዮጵያዊ ፊልም የአጻጻፍ ደረጃው ከፍ ያለና ከድርሰት እስከ ፕሮዳክሽን ሙሉ በሙሉ በሀገር ባለሞያዎች የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"አስቴር" የተሰኘው የመጀመሪያው ፊልም የዛሬውን የፊልም ኢንዱስትሪና የፈጠራ ክህሎትን ለማሳደግ መነሻ መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ፤ ቢሮው በቴክኖሎጂ ምክንያት ለዕይታ ሳይበቁ የቆዩ የቀደምት የፊልም ሥራዎችን ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በማፈላለግ ዲጂታላይዝድ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

የፊታችን ህዳር 8 ቀን 2017 ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የፊልሙ ባለቤቶች፣ ተዋናይናዮችና የኪነ ጥበብ አፍቃሪያን በታደሙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ታላላቆችን እናክብር" በተሰኘ ልዩ መርሐግብር 13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅና ሊበረከትላቸው ነው

በተወዳጅ ሚዲያ የተዘጋጀውና በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች የሚመሰገኑበት ልዩ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ ህዳር 7 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል።

በዚህ ልዩ የምስጋና ዝግጅት ላይ 13 የቀድሞ  ጋዜጠኞች ዕውቅና ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ ተብለው የሚጠበቁት ተመስጋኝ ጋዜጠኞች አቶ አስፋው ኢዶሳ፣ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ፣አቶ ሀዲስ እንግዳ፣አቶ ዋጋዬ በቀለ፣ወይዘሮ ሚሊየን ተረፈ፣አቶ ሀይሉ ወልደፃድቅ፣አቶ ተሾመ ብርሀኑ ከማል፣አቶ ተክሉ ታቦር፣ አቶ ይንበርበሩ ምትኬ፣ አቶ ታዬ በላቸው፣አቶ ግርማይ ገብረፃድቅና አቶ ኢሳያስ ሆርዶፋ ናቸው።

ዝግጅቱ ላይ እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸው ያለፈው የሚድያ ሰው ሙለጌታ ወልደሚካኤልም በልጆቻቸው አማካይነት ዕውቅናው ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

እነዚህ ዕውቅና የሚቸራቸው አንጋፋ የሚድያ ሰዎች ከዚህ ቀደም ተገቢውን ዕውቅና ሳያገኙ የቀሩና በሌሎች የሽልማት መርሀግብሮች ያልተካተቱ ነበሩ።

በሁሉም ተመስጋኞች የህይወት ታሪክ ላይ በቂ ጥናት እና ምርምር መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።

በዕለቱ የቀድሞ ጋዜጠኞችን የቆየ ድምፅና ቪድዮ የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ መሰናዶ የሚኖር ሲሆን የሙያ ማህበራት፣የሚድያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህራን እና ሌሎችም ታላላቅ እንግዶች ይታደማሉ፡፡

የመርሀግብሩ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆን ከዚህ ቀደም የ45 ሰዎችን  ታሪክ  በሲዲ የ20  ሰዎችን ታሪክ  ደግሞ  በመፅሐፍ ያሳተመ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ለዝና" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ

የወጣቱ ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ "ለዝና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃ ትላንትና ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ቀርቧል።

የዚህ ነጠላ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ በድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር እና ሚክስ ማስተር ሮቤል ዳኜ ተሳትፎበታል።

ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ ከዚህ ቀደም "ነይ " "አይናለም" "አይከረም" የተሰኙ ነጠላ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ !

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ ስርጭቱን ጀመረ

ከዚህ ቀደም በድረገፅ፣ በቴሌግራም እና በፌስቡክ አማራጮች ብቻ ዕለታዊ ተመራጭና አማራጭ የኪነጥበብ እና ሁነት መረጃዎችን ሲያቀረብ የቆየው ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ የማኀበራዊ ትስስር ገፅ ከዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መረጃዎችን ማቅረብ ጀምሯል።

ሊንክ: tiktok.com/@eventaddis1

በተጨማሪም በቅርቡ በሌሎችም የማህበራዊ ትስስር ገፅ አማራጮች እንመጣለን።እናመሰግናለን ።

ቴሌግራም: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ድረገፅ: https://eventaddis.com/

Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
📌የዝነኛው የቴአትር መምህር መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የ"በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" "የአና ማስታወሻ"ን ጨምሮ በርካታ ተውኔቶችን ያዘጋጁትና  በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ት/ክፍል ውስጥ ተፈሪና ተወዳጅ የሆኑት ዶ/ር ተሻለ አሰፋ ያዘጋጁት "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊን " መጽሐፍ ሊመረቅ እንደሆነ ተሰምቷል።

እነሆ ዝርዝሩን: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/
📌 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ከ34 ዓመታት በኃላ ለዕይታ ቀርቧል።

እነሆ ዝርዝሩን በድምጻችን ይስሙ: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ወደ መድረክ ልትመለስ ነው

ለረጅም ጊዜ ከመድረክ እርቃ የቆየችው ሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ በሚካሄድ አንድ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ስራዎቿን እንደምታቀርብ ተሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhtvQybR/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
1
📌በ"ማለዳ ኮኮቦች" ፕሮግራም የምናውቀው ፍፁም አስፋው አዲስ የቴሌቪዥን ዝግጅት ሊጀምር ነው።

"የማለዳ ኮኮቦች" እና "ቅን ልቦች"የተሰኙ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ሲያቀርብ የቆየው ሁለገቡ የፊልም ባለሞያው ፍፁም አስፋው "ፎቶ እና ጨዋታ" የተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በአባይ ቴሌቪዥን ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhnf3xPS/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ በድምቀት ይመረቃል።

በሸገር ሬድዮ 102.1 "ስንክሳር"  የሬድዮ ዶክመንተር ጨምሮ በበርካታ የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፉን የፊታችን ቅዳሜ ሊያስመርቅ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhnfcPrS/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ማልኩልሽ"ሙዚቃ ሊለቀቅ ነው።

ከሰሞኑ በቲክቶክ ማህበራዊ ትስስር ገፆች በርካቶች ሲቀባበሉት የቆዩት የድምጻዊ ሙሉዓለም ታከለ"ማልኩልሽ" ነጠላ ሙዚቃ የሚለቀቅበት ቀን ይፋ ሆኗል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhWcoBNR/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የገጣሚ ታዲዮስ አዲሱ "አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ አርብ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ መጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ወጣትና አንጋፋ የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ቤርሙዳ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው።

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በዶክተር ተሻለ አሰፋ የተዘጋጀውና ተቋረጦ የቆየው "በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" ቴአትር ወደ መድረክ ሊመለስ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhWcE2fr/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተውኔት ማሳየት ሊጀምር እንደሆነ ተገለፀ።

ከ80 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ወደ ቀደመ አገልግሎቱ ሊመለስ እንደሆነ ተገልጿል::

ቴአትር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩ በጀመረው የኮሪደር ልማት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከፊታችን እሁድ ህዳር 15/2017 ጀምሮ ትያትሮችን ማሳየት ይጀምራል ተብሏል::

ትርኢት ማሳየት የሚጀመረው 'ቤርሙዳ' በተሰኘው ተውኔት እንደሆነም የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የመድረክ አስተባባሪ አርቲስት ዮሀንስ አፈወርቅ አስታውቋል፡፡

በቲያትር ቤቱ ግቢ ውስጥ በቅርስነት የተመዘገቡ ክፍሎች እንዳይፈርሱ እና ታሪክ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ቢሞከርም ሳይሳካ ቀርቶ ቅርሶቹ መፍረሳቸው ይታወሳል::

አሁን ላይ በአዲስ አበባ ያሉት ትያትር ማሳያዎች 3 ብቻ ሲሆኑ ብሔራዊ ፣ ሀገር ፍቅር እና የሕፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት ናቸው::

📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ


📍 "የሕይወት ታሪክ"

ድርሰት: ነብዩ ባዬ እና ቢኒያም ወርቁ
አዘጋጅ: ነብዩ ባዬ እና ቢኒያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አለማየሁ ሄርጶ አዲስ አልበም ሊያወጣ ነው

ተወዳጁ ድምፃዊ አለማየሁ ሄርጶ አዲስ አልበም ሊያወጣ መሆኑን የሙዚቃ ባለሙያው አለማየሁ ደመቀ ለሁሉ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ተናግሯል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMh74T5gA/

Credit: ሁሉአዲስ የሬድዮ ፕሮግራም።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ ዶክተር ዳዊት አሰፋ እና ዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ መጻሕፍት ደግሞ "የሁሉ" እና "ኦቲዝምና አንዳንድ ከያንያን ስለሚያጠቃቸው የአዕምሮ ሕመም" ናቸው።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

50ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ተመስገን ዋና " ሳይንስ እና ኃይማኖት:በተዋሥኦ መካከል" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 የሮፍናን ኮንሰርት በአዳማ  ተሰርዘ

ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቅዳሜ ህዳር  14 2017 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ ይዞለት የነበረው "የኔ ትውልድ" ኮንሰርት ሙሉበሙሉ እንደተሰርዘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMh7w27h3/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1