Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌በቻይና ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ተሸለመች

ጋዜጠኛ ሰላም ተሾመ ከሰሞኑ በቻይና በተካሄደው የ"Road and Belt journalist forum" ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ተገኝታ ነበር።

በፎረሙ ከ30 በላይ ሃገራት ከተወከሉ የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ጋዜጠኛ ሰላም ተሾመ ባቀረበችው ስራ ከፍ ያለ ዕውቅና ተሰጥቷት።

በዚህም ስራዋ ተሸላሚ ሆና የሀገራችንን ስም አስጠርታለች።

©️ጋዜጠኛ ያልፋል አሻግር

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
11
📌ድምጻዊ ብስራት ጋረደው "ከእንግዲህ በኃላ በመዝሙር ጠብቁኝ" ሲል ተናገረ

ድምጻዊ የግጥምና ዜማ ደራሲው ብስራት ጋረደው በአርትስ ቴሌቪዥን በኩል በሚተላለፈው 'ዘጠናዎቹ' የቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆኖ ቀርቦ ነበር በዚህም ዝግጅት ላይ "ከእንግዲህ በኃላ በመዝሙር ጠብቁኝ" ሲል ተናግሯል።

ብስራት ጋረደው በተጨማሪም "ከሞትኩበት ያነሳኝን አምላኬን ዘፍኜ አላሳዝነውም" ብሏል።

ድምጻዊ ብስራት ጋረደው በዘጠናዎቹ በለቀቀው "ሳላምንበት" በተሰኘው ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሙ ከበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ጋር ተዋውቋል።

በተጨማሪም ለበርካታ ድምጻዊያን የግጥምና ዜማ ስራዎችን አበርክቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
3
📌የጋዜጠኛው የስለት ጥቃት ሀሰት ሆኖ ተገኘ

የስፖርት ጋዜጠኛው አሉላ ፍሬው "በጩቤ ተወጋሁ" ያለው ጉዳይ በመረጃና ማስረጃ ሀሰት ሆኖ ተገኘ

የCD ስፖርትና የNBC ኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛው አሉላ ፍሬው በስለት የመወጋት አደጋ እንደደረሰበት ከ51 ቀናት በፊት በራሱ የፌስቡክ ገፅ አስታውቆ ነበር።ይህም አስነዋሪ ድርጊት በወቅቱ መነጋገሪያ እንደነበረ ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ እና ባልደረቦቹ ጥልቅ ምርመራ አድርገው ፣መረጃዎችን አጣርተው ነበር።

ይህ "ጋዜጠኛው ላይ ጉዳት ያደረሰው ማነው?" በሚል ርዕስ የቀረበው ሰፋ ያለ ዘገባ "የፖሊስ፣ የክሊኒክ፣ የማህበሩና የፌዴሬሽኑን ምላሽ" ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

በምርመራቸውም የስፖርት ጋዜጠኛው የሰጣቸው መረጃና በምርመራ ያገኙት መረጃ ፍፁም የማይገናኝ በመረጃና ማስረጃ ሀሰት እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዘገባቸው ላይ ተመልክቷል።

የምርምር ቡድኑ "የዚህ ዘገባ አላማ የሙያ ባልደረባችን ያጋጠመውን ጉዳት መነሻ በማድረግ በሙያተኞች ላይ የሚደርሰውን በደልና ጥቃት ማውገዝ ብሎም ማጋለጥ ነበር፤ ሆኖም መረጃውን ስናጣራ ውጤቱ ይህ ሆኗል" ሲል አስታውቋል።

ሙሉ መረጃውን ከጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ የፌስቡክ ገፅ ያንብቡ: https://www.facebook.com/1812918430/posts/pfbid02E2uAome5LTwaR9YZbYBQsLwiQX93kyqysRYPSpC5SpC9U3FiekbqriQpGjDAQxVpl/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4😁4🔥2🤔1
📌የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ከ" ንጉሥ አርማህ" ተውኔት የመክፈቻ ሥነሥርዓት ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው የታዳሚያን መጉላላት በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

ቴአትር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በትናንትናው ዕለት ማለትም ሐምሌ  20 ቀን 2017 ዓ.ም  ‹‹ንጉሥ አርማህ›› ቴአትር በይፋ መከፈቱ ይታወቃል፡፡ በዕለቱ የተመልካቹ ብዛት ከቴአትር ቤቱ አዳራሽ አቅም በላይ በመሆኑ በቦታ ጥበት ምክንያት የተመለሳችሁ ክቡራን ተመልካቾቻችንን ከፍተኛ ይቅርታ በቴአትር ቤቱ ሥም እንጠይቃለን" ስለማለቱ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በሌላ በኩል "ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8፡30 ይቀርብ የነበረው ‹‹12ቱ እንግዶች›› ቴአትር  ወደ ቅዳሜ 8፡30 የተዘዋወር ሲሆን  ‹‹ንጉሥ አርማህ›› ቴአትር ዘወትር እሁድ በ8፡30 ለክቡራን ተመልካቾች እንደሚቀርብ በአክብሮት እንገልጻለን" ሲል የመርሐግብር ለወጥ እንዳደረገም ቴአትር ቤቱ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
🙏173
📌"ሣማ ፊልም" ተመረቀ

በደራሲና አዘጋጅ ሞገስ አስራት ተዘጋጅቶ በአድዋ ፊልምስ የቀረበው "ሳማ" ፊልም ትላንት ሰኞ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ተመርቋል።

በፊልሙ ላይም በመሪ ተዋናይነት ሽዋፈራሁ ደሳለኝ ፣ ሙላለም ጌታቸው ፣ ቤዛነሽ አያሌው እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።

ከዚህ ቀደም በተመልካች ተወዳጅነትንና አድናቆትን እንዲሁም በተለያዩ አዋርዶች ላይ በበርካታ ዘርፎች በመታጨትና በመሸለም የሚታወቀውን "ክሱት" የተሰኘ ፊልም በመስራት ለዕይታ ያበቃው አድዋ ፊልምስ ፕሮዳክሽን አሁን ደሞ ሙሉ ቀረፃውን በጉራጌ ዞን ያደረገ "ሣማ" የተሰኘ ፊልምን ለእይታ አብቅቷል።

ፊልሙ በቅርቡ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይቀርባል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ንባብ ለሕይወት" ግዙፉ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ግዙፉ የመጽሐፍ አውደርዕይ "ንባብ ለሕይወት " የመጽሐፍና ንባብ አውደርዕይ ከቀናት በኃላ ሊካሄድ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"ንባብ ለሕይወት" የመጻሕፍት አውደርዕይ ዘንድሮ ከሐምሌ 24 እስከ ሐምሌ 27 2017 ዓ.ም ድረስ ለቀናት መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ውስጥ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።

የንባብ ከሕይወት ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በመተባባር ባዘጋጀው በዚህ አውደርዕይ ላይ በርካታ ደራሲያን በመገኘት መጻሕፋቸውን ያስተዋውቃሉ ተብሏል።

የመጻሕፍት አሳታሚዎችና አከፋፋዮች መጻሕፍትን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ።

በአውደርዕዩ ላይ የመጽሐፍ ምርቃትና ሀሳብ ማንሸራሸሪያ ልዩ ልዩ መድረኮች ተዘጋጅቷል።

የአውደርዕዩ መግቢያ በነፃ ሲሆን ሐሙስ ሐምሌ 24 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ይከፈታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4🔥2
📌የሠርቅ ዳንኤል መጽሐፍ ድጋሚ ሊታተም ነው

የደራሲ ሠርቅ ዳንኤል (ገበና ዳንኤል) ተወዳጅ ድርሰት የሆነውና ከገበያ ጠፍቶ የቆየው "ቆንጆዎቹ" የተሰኘ መጽሐፍ በቅርብ ቀን ድጋሚ ታትሞ ለአንባቢያን እንደሚያቀርብ ኤቨንት ሚዲያ ከአሳታሚው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👏202
ጆኒ ራጋ፣ ሚካኤል በላይነህና ዳዊት መለሠ ተጣምሩ

ድምጻዊያኑ ጆኒ ራጋ፣ ሚካኤል በላይነህ እና ዳዊት መለሠ የተጣምሩበት "ሸክ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ ኮንስርት በዚህ ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ከሙዚቃ ኮንሰርት ራቅ ብሎ የቆየው ጆኒ ራጋ በ"ሸክ" ኮንሰርት በአስዮ ባንድ ታጅቦ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል ተብሏል።

ይህ ኮንሰርት ሚካኤል በላይነህ እና ዳዊት መለሠ በዚህ ዓመት ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ የተጣምሩበት ኮንሰርት ነው።ሚኪ እና ዴቭ አስቀድመው በዚህ ዓመት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ሁለት ተከታታይ ኮንሰርቶችን በጥምረት ማቅረባቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8🥰1
📌አራት ዝነኛ ጋዜጠኞች በጥምረት ሚዲያ መሰረቱ

በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ምስረታ እና እድገት የጎላ ድርሻ የነበራቸው 4 የሚድያ ሰዎች ላይፍ ሚድያ በሚል ዩቲዩብ አዳዲስ ይዘትና ሀሣቦችን ሊያቀርቡ እንደሆነ ታወቀ፡፡

ከመጋቢት 1999 ዓ.ም ጀምሮ የፋና 98.1መሥራች ጋዜጠኞች የነበሩት ዘካርያስ ብርሀኑ፣ እፀገነት ለዐቀ ፣ ነቢል መሐመድና ትዕግስት በጋሻው በመጣመር ለዓመታት ያካበቱትን ልምድ በላይፍ ሚድያ እንደሚያካፍሉ ይጠበቃል።

የሚድያ ባለሙያዎቹ ለተወዳጅ ሚድያ እንዳሉት ላይፍ ሚዲያ በተለያዩ የኑሮ ጉዳዮቻችን ግንዛቤ  ለመጨመር የሚተጋ መሰናዶ ነው፡፡

ሀሣቦች በነጻነት ልክ እንደቤተሠብ ለማቅረብ እቅድ መንደፋቸውን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡ውጥናቸውንም ሲያብራሩ"ዘና ብለን በቁምነገር በብዙ መልኩ እውነታን ፣ ልምድን፣ የአቀራረብ ስብጥርንና ስነምግባርን ተላብሰን በማህበረሰብ ትስስር ገፅ የበኩላችንን በጎ አስተዋፅዖና ድርሻ  ለማሳየት የፈጠርነው መድረክ ነው" በማለት ተናግረዋል።

አቅራቢዎቹ በኢትዮጵያ ሚድያ ላይ በአመራርነት፣ በመዝናኛ አዘጋጅነት  በማስታወቂያና በይዘት ፈጠራ ክህሎታቸው ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ ትልቅ አሻራ ያኖሩ ናቸው፡፡

የላይፍ ሚድያ አዘጋጆች  ህይወት ሰፊ ውቅያኖስ መሆኗንበትንሹ በሚጠቅም መልኩ እየጨለፍን ህይወታችንን ለማሻሻል እንተጋለን ሲሉም በጥሩ ይዘት ተመልካችን ለማዝናናት እንደተዘጋጁ ተናግረዋል።

https://youtube.com/channel/UC9gOKO-9ZBdSubvbwZ3e6uw?si=aKKaTdnSRJT-itOs

©️ተወዳጅ ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
13🔥1
📌ዓለም ሲኒማ ሁለተኛ ሲኒማ ቤት ሊከፈት ነው

ለዓመታት የፊልምና ቴአትር ስራዎችን ለታዳሚያን እያቀረበ የቆየው ዓለም ሲኒማ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ወደ አገልግሎት ሊያስገባ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቦሌው ከሚገኘው ሲኒማ ቤቱ ባሻገር  “ዓለም ሲኒማ በመገናኛ " ተብሎ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው ማራቶን ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ አገልግሎት እንደሚሰጥም ሰምተናል።

የመገናኛው ሲኒማ ቤቱም የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 26 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይመረቃል ተብሏል።

ዓለም ሲኒማ ሁለተኛ ቅርጫፉን ሲከፈት በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ላይ ካሉ ሲኒማ ቤቶች ሁለት ቅርንጫፎች ያለሁት ብቸኛው ሲኒማ ቤት ያደርገዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍4
📌የዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት በሦስት ቋንቋዎች ዛሬ ይመረቃሉ፡፡

📖  ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ (ቅጽ ፩)
Neuro Entrepreneur (Vo.1)

📖  የኒዩሮ አመራር ሳይንስ (ቅጽ ፪)
Neuro Leadership Science (Vo.2)

📖  SAAYINSIFII NIWUROO FII HOJII UUMUU

በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅተዋል፡፡

እነዚህ መጻሕፍት በተለይም በወጣቶች ዘንድ የሥራ ፈጠራ መንፈስን በማነሳሳትና የአመራር ብቃትን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

📆  አርብ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም.
⌚️ ከቀኑ 10:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት)
📍በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ራስ መኮንን አዳራሽ (ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት)፣ 6ኪሎ ይመረቃል።

በእለቱ
የመጽሐፉ ገምጋሚዎች

👉 ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል
👉 ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ
👉 ዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ
👉 ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
👉 ጋዜጠኛ ሡልጣን መሐመድ ኑር

ወግ አቅራቢ
👉 በኃይሉ ገብረመድህን

የነጻ ሐሳብ ቅምሻ
📌 ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ
📌 ዶ/ር ኤርሲዶ ሌንዶቦ
📌 ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ
📌 ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጃዋሬ

በስራ አመራር እና በስራ ፈጠራ
📌 ኢ/ር ቤጃይ ናይርሽ ናይከር
📌 ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ

ቅምሻ

👉 አበበ ባልቻ
👉 ሀረገወይን አሰፋ
👉 ተፈሪ አለሙ
👉 ሙሉዓለም ታደሰ
👉 አንዱዓለም ተስፋዬ

መድረክ አጋፋሪ

📌 ደራሲና ጋዜጠኛ  አዜብ ወርቁ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8
📌የገጣሚ ጋሻው የኋላሸት /ዘቢደር/ ''ሕይወት እንደ መንገድ'' የተሰኘው አዲስ የግጥም መድብል ተመረቀ

መጽሐፉ በ120 ገፅ የቀረበ ሲሆን  60 ያህል ግጥሞችን ያካተተ ነው።

ግጥሞቹ ለውበት ያደሉ :በቅርጽ እና በቃላት አጠቃቀማቸውም መንፈስን የሚያረኩ ናቸው።

ገጣሚ ጋሻው የኋላሸት ከዚህ ቀደም በአለላ መጽሔት በምክትል አዘጋጅነትና በአምደኝነት ሰርቷል። እንዲሁም በዓባይ ቴሌቪዥንም በፕሮዲዩሰርነት አገልግሏል።

ጋሻው/ዘቢደር/ ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ በስነ-ጹሑፍ ዘርፍ ሰፊ ጊዜውን ያሳለፈ ነው።

በራያ አለማጣ አርብ ምሽት የስነ-ጹሑፍ ክበብ እንዲሁም በራያ ዋጃ-ጥሙጋ ሀይስኩል የኪነ-ጥበብ ተሳትፎው የጎላ ነበር።

ከዚህ ቀደም "የነፍስ እኩያሞች" በተሰኘ የ11 ደራሲያን ስብስብ ልብ-ወለድ መጽሐፍ ላይ ሁለት አጫጭር የልብ ወለድ ስራዎቹ የተካተቱለት ደራሲ ነው።

ወደ ፊትም የህትመት ጊዚያቸውን የሚጠብቁ የረዥም እና የአጫጭር ልብ ወለድ መጽሐፍትም አጠናቋል።

''ሕይወት እንደ መንገድ'' የተሰኘው  የግጥም መድብል ዛሬ ሐምሌ 25 በዋልያ መፅሐፍ ገጣሚያን : ደራሲያንና የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።

መጽሐፉን ለገሀር አካባቢ በሚገኙ በጃዕፋርና በሌሎች የመፃሕፍቶ መደብሮች እንዲሁም 6ኪሎ በሚገኘው ኦሮማይ የመጽሐፍ መደብር ያገኙታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
5🥰4
📌ድምጻዊ ይሁኔ በላይ እውቅና ሊሰጠው ነው

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለታዋቂው የባሕል ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ይሁኔ በላይ "ለኢትዮጵያ የባሕል ሙዚቃ ጥበብ እድገት ላበረከተው አስተዋጽኦ" የእውቅና ሽልማት (Recognition Certification Award ) ይሰጣል።

ይሁኔ በላይ በነገው ዕለት በግለታሪኩ ዙሪያ ጽፎ ለንባብ ያበቃውን መጽሐፍ ለማስመረቅና የእውቅና ሽልማቱን ለመቀበል ዛሬ ረፋድ ውቢቷ ባሕር ዳር ገብቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
9👏3👍1
📌መዓዛ ወርቁ እንግዳ የሆነችበት ልዩ ዝግጅት የፊታችን ሰኞ በአሜሪካ ኤምባሲ ሊካሄድ ነው

(መግቢያው በነፃ ነው)

የCreator lab ዝግጅት አዘጋጆች የቴያትር  እና የፊልም ደራሲ እና አዘጋጅ  የሆነችው  መዓዛ ወርቁን በእንግድነት ጋብዘዋል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ስለድርሰት እና ዝግጅት እንዲሁም የራሷን የሕይወት ተሞክሮ ለእናንተ ታካፍላለች። ስለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ደራሲ እና አዘጋጅ  የመሆን ፍላጎት ያላችሁ፤ እንዲሁም በሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።


📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ (ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ሰኞ ሀምሌ 28 ፣ 2017 ዓ.ም

🕗 ሰዓት: ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግቢያ: በነፃ

አቅራቢ፦ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ

📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA


ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
5
📌"ኪሳራም ሥራ ነው" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው ከፈለኝ ሐይሉ ያሳተሙት "የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ "ኪሳራም ሥራ ነው" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) በይፋ ተመርቋል።

በኢትዮጵያ ያለው የንግድ ስርዓት በዘርፉ ለተሰማሩ የንግድ አካላት በአሳሪ ቢሮክራሲና በሌሎች ምክንያቶች መታሰሩ፤ ንግድ በኢትዮጵያ እድገቱ በታሰበው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል።

የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት ንግድ በማያውቁ የመንግስት ሃላፊዎች መመራቱ ዘርፉ በሚገባው ልክ እንዳያድግ ስለማድረጉ በመጽሐፉ ዙሪያ ውይይት በተደረገበት በዚሁ መድረክ ላይ ተነግሯል።

በውይይቱ የተለያዩ የፋይናንስ እና ቢዝነስ ባለሙያዎች፣ ኢንተርፕርነሮች እና በርካታ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤ መፀሐፉ ውስጥ በተመረጡ ሃሳቦች ዙሪያ ሙያዊ እይታቸውን አጋርተዋል።

የንግድ ስርዓት፣ የፋይናንስ ፍሰት እና የግብር ስርዓት በኢትዮጵያ ያለው መልክ ከሳይንሱ እና አጠቃላይ የዘፈቀደ  አካሄዶች ያላቸው መልክ ምን ይመስላል የሚለው ተዳሶበታል።

@አሐዱ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8👍1🥰1
📌የአራዳ ፖስታ ቤት ህንጻ የፈጠራ ማዕከል ሆነ

ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው እና “አራዳ ፖስታ ቤት” እየተባለ የሚጠራው ታሪካዊው የኢትዮ ፖስታ ህንጻ፣ ወጣቶችን ለማሳተፍ እና ፈጠራን ለማነቃቃት ወደሚያስችል የፈጠራ ማዕከልነት መቀየሩ ተሰምቷል።

ይህ ታሪካዊ ህንጻ፣ ወደ 1900ዎቹ የሚጠጋ ታሪክ ያለው ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘመናዊ ፖስታ ቤት ነበር። አሁን ደግሞ የከተማ ልማት ፍላጎት እና አዲስ ቦታን ለመጠቀም በሚደረገው ጥረት፣ "Creative Hub Ethiopia" የተሰኘው ድርጅት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የቦታውን አስተዳደር በመረከብ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎችን እና ተግባራትን እያስተዋወቀ መሆኑ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የዚህ ማዕከል ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በወጣቶች በሚመራው የፈጠራ ዘርፍ ማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።

©️ Capital

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
9😢6👎1
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1/6236
👍84
📌 "እንዳለሁ አበራለሁ" መጽሐፍ ሐሙስ ይመረቃል

በደራሲ ማክዳ አርሺ ተጽፎ፣ በታዋቂው ደራሲና ገጣሚ በውብ አማርኛ በግጥም የተቀናበረው፣ ስለ ኦቲዝም ግንዛቤን የሚያስጨብጠው "እንዳለሁ አበራለሁ" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ግቢ ውስጥ ይመረቃል።

ስለ ኦቲዝም ያለንን ግንዛቤ በጋራ በምናሳድግበት በዚህ ልዩ መድረክ ላይ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
3
📌መቅረዝ ሥነኪን ሐሙስ ይካሄዳል

መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
1🥰1
📌"የወዲያነሽ" መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

በአንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የተዘጋጀውና በቅርቡ በድጋሚ የታተመው "የወዲያነሽ"መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ይመረቃል።

ወዳጆቹና አክባሪዎቹ በሚገኙበት በልዩ መርሐግብር ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍127
📌ደራሲ ደመወዝ ጎሽሜ እንግዳ የሆነበት መሰናዶ!

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "አዲስቱ እየሩሳሌም" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት የመጽሐፉ ጸሐፊ ደመወዝ ጎሽሜ ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍9👏4🙏21