Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ዝነኛዋ ዘሪቱ ከበደ በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም

ዘሪቱ ከበደ ስለ ልጅነቷ ፣ አስዳደግና የሕይወት መንገድ ዙሪያ በጻፈችው "ከልጅነት እስከ ልጁነት" ግለ ታሪክ መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች እሁድ ታህሳስ 26, 2018 ከምሽቱ 2 እስከ 4 ሠዓት ድረስ ውይይት ያደርጋሉ።

የውይይቱ ሊንክ:

https://news.1rj.ru/str/ethiopia_book_forum_official?livestream=7de0d0284be2d41c86

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
6🔥2👏2😱1
📌 "ሼሙኔ" መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

በሆሄ ምዕራፍ ወርኃዊ የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጆች አዘጋጅነት በደራሲ መስፍን ወንዶሰን  "ሸሙኔ" መጽሐፍ ላይ ቅዳሜ ረፍድ ላይ  ውይይት ይካሄዳል። ይህ መርሐግብር ታህሳስ 25 ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ወመዘክር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በውይይቱ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና መሠረት አበጀ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8
📌ዝነኛዋ ብርቱካን ሚደቅሳ መጽሐፍ ጻፈች

ዝነኛው የፖለቲካ ሰው ብርቱካን ሚደቅሳ "መመለስ የቦጌ ትውስታዎቼ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ልታበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👏148😁8🔥1
📌የአፄ ኃይለሥላሴ ቤተሰባዊ ታሪክ ዘጋቢ ፊልም

የኢትዮጵያን የመጨረሻ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ቤተሰባዊ ታሪክ የሚዘክረው "Grandpa Was an Emperor" የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም በዓድዋ ድል መታሰቢያ መታየት ጀመረ፡፡

ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የሳበው ፊልም፤ የሚያተኩረው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በሆኑት በልዕልት የሺ ካሳ የግል የሕይወት ታሪክ ላይ ነው።

ፊልሙ በቤተመንግስት ውስጥ የነበረውን የልጅነት የቅንጦት ሕይወት፣ በድንገት የተቀየረበትን የ1966ቱን አብዮት፣ እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቿ ለዓመታት በእስርና በስደት ያሳለፉትን መራራ ታሪክ በዝርዝር ይተርካል።

ዘጋቢ ፊልሙን ከሌሎቹ የታሪክ ስራዎች ለየት የሚያደርገው፤ ከዚህ ቀደም ለሕዝብ እይታ ያልበቁና በንጉሣዊው ቤተሰብ የግል ካሜራዎች የተቀረጹ ያልታዩ የቪዲዮ ምስሎችንና ፎቶግራፎችን አካቶ መያዙ ነው ተብሏል።

የታዋቂዋ ሲኒማቶግራፈር ኮንስታንስ ማርክስ ስራ የሆነው ይህ ፊልም፤ በታዋቂዋ ድምፃዊትና ተዋናይት ሲንቲያ ኤሪቮ (Cynthia Erivo) አዘጋጅነት (Executive Producer) ለዕይታ የበቃ ነው።

ፊልሙ በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ የ"Joel Siegel Documentary Award" ሽልማትን ማሸነፉ ይታወሳል።በአሁኑ ወቅት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኙት ሲኒማዎች ለእይታ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
25👏4🙏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌ድምጻዊ ናቲ ኃይሌ መድረክ ላይ ግጥም ጠፋበት

ድምጻዊ ናቲ ኃይሌ ከዓመታት በኃላ ትላንትና አመሻሽ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ከሳምቮድ እና ሔኖክ አበበ ጋር በጋራ የሙዚቃ ኮንሰርቱን አቅርቦ ነበር።

በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ናቲ ኃይሌ የአንጋፋውን ድምጻዊ ንዋይ  ደበበ "ሀገሬን አልረሳም" የተሰኘውን ሙዚቃ መድረክ ላይ በሚያቀርብበት ወቅት ግጥም ሲጠፋበት ታይቷል።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ እንደታዘበው ከሆነ ይህም አጋጣሚ በተለያዩ ሰዎች ዘንድ መነጋገሪያ አድርጓታል። ለምን ግጥሙን በሥርዓቱ አጥንቶ አይዘፍንም? የሚሉ ጥያቄዎች እንዲሁም ያልተዘጋጀበትን በአግባቡ ያላጠናውን ዘፈን ባይዘፈን መልካም ነው  የሚሉ አስተያቶችም ተሰምተዋል።

📸ቪዲዮውን ይመልከቱ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
😁527👎1🤔1🌚1👀1
📌የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነት ተነሱ

ከተሾሙ 12ተኛ ወራቸውን የያዙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) ከኋላፊነታቸው ተነሱ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የሚያቋቁመው አዋጅ የባለስጣኑ ዋና ዳይሬክተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾም ይደነግጋል።

በዚሁ መሠረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ አቶ ሳምሶንን የሚተኩ ዕጩ ተሿሚ ማቅረባቸውን ሪፖርተር አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤም፣ "ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ ወርቅነህ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ እንዲሾሙ እጠይቃለሁ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ በሥራ ላይ የሚገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ከኋላፊነት የተነሱበትን ምክንያት አይገልጽም።

ወ/ሮ ሐይማኖት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽፈት ቤት በም/ቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ደግሞ በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በዳይሬክተርነት ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በከፍተኛ አዘጋጅነት ያገለገሉ ናቸው።

©️ሪፖርተር ጋዜጣ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
🙉53
📌በላሊበላ የእንግዶች ቁጥር መቀነሱ ተነገረ

የገና በዓልን ለማክበር ላሊበለ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት  የሚያደርጉ ባለሆቴሎች፣ የእንግዶች ቁጥር መቀነስ እንዳሳሰባቸው ተናገሩ፡፡የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ግን ከ12 ሺሕ በላይ ቱሪስቶች መግባታቸውን ገልጿል፡፡

ከኮሮና ወረርሽኝ ቀጥሎ በነበረው የሰሜኑ ጦርነትና በአሁኑም ወቅት በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ባለው ግጭት ወደ ከተማዋ የሚገቡ የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር በመቀነሱ፣ ለሠራተኞች ደመወዝ መክፈል እንዳልቻሉና ያለባቸውን የባንክ ዕዳ ለመክፈል መቸገራቸውን፣ ዘንድሮ ግን ይህ ሁኔታ ካልተለወጠ ለበለጠ ችግር እንደሚዳረጉ በላሊበላ ከተማ የሚገኙ የሆቴልና የሎጅ ባለቤቶች ለሪፖርተር ተናግረዋል።

አንዳንድ የሆቴል ባለቤቶች እንዳሉት ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ከስድስት ወር በፊት የመኝታ ክፍሎቻቸውን ለቱሪስት አስይዘው ይጨርሱ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን በዓሉ ቀናት ቢቀሩትም ምንም ዓይነት እንግዳ አለመቀበላቸውን አስረድተዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4🕊3🙏1
📌ለአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር መንገዶች ይዘጋሉ 

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅም፡- 
👉 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ  የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ
👉 ከቦሌ በጌቱ ኮሜርሻል  ወደ መስቀል  አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል አካባቢ 
👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ
👉 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች  አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ፤ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ
👉 ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር መብራት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያ መስቀለኛ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ  ለገሃር መብራት
👉 ከአምባሳደር  መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት
👉 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግሥት  የሚወስዱ መንገዶች ከታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መርሀ ግብሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ ሲሆን ከዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሚዘጉ መንገዶች ላይ ለረጅም ሆነ ለአጭር ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍1310🕊1
📌ቴዲ አፍሮ በኬንያ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎረቤት ሀገረ ኬንያ ሞምባሳ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ሊያቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የሙዚቃ ኮንሰርቱ በቅርቡ እንደሚከናወን ሰምተናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
111👍3👏1🙏1
📌ገናን በካስማ ቤት ልዩ የበዓል የመዝናኛ ዝግጅት

👉 https://youtu.be/M6CXM_yNjcQ
📌"በከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" መጽሐፍ ላይ ውይይት

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ
መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ቅዳሜ ጥር 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በተጋባዥ እንግዳነት ኢዛና አምደወርቅ (ዶ/ር) ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።
11👍1
📌 ከወጣት ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ቡና እየጠጣችሁ ስለስራ ምታወሩበት መድረክ ሊፈጠር ነው።

( ቅድሚያ ለተመዘገበ መግቢያው በነፃ ነው)

ከ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ኑ ቡና ጠጡ

ከተወዳጁ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ቡና እየጠጣችሁ መስራት የምትፈልጉዋቸውን ስራዎች ከ እሱ ጋር የምታወሩበት እና የምትወያዩበት መድረክ ተዘጋጅቷል።

የራሳችሁን ሥራዎች እንዲሁም ያለውን ልምድ አንድ ለ አንድ በሚፈጠረው መድረክ ላይ ስለሰራቸው ሙዚቃዎች እንዲሁም ቀጣይ ስለሚያስባቸው ስራዎቹ የሚያካፍልበት የ ሲንክ አፕ ቻት ፕሮግራም ሲሆን ይህ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎ ስንል እንጋብዛለን።

📅️️️️ ቀን ፡ ጥር 9
⏰️️️️️️️ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ
📍️️️️ቦታ ፡ ጋዬ ቡና ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ( ካፕስቶን ህንፃ )

🎟️️️️ ትኬት
- ቀድመው ለቆረጡ - በነፃ ( ከነፃ ቡና ጋር )
- መደበኛ - 500 ብር ( ከ ነፃ ቡና ጋር )
- ቪአይፒ - 1000 ብር ( ከነፃ ቡና እና ምግብ ጋር )

ያለን ቦታ ውስን ሰለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ

ትኬትዎን ለመቁረጥ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ👇️️️️️️
https://linktr.ee/SyncUp.chat


ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4👍4❤‍🔥1🔥1🥰1👏1🤔1🤗1
📌ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ቤት ተሰጠው

አንጋፋው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የመኖሪያ ቤት እንደተሰጠው ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው "ቤት እንደሚያስፈልገው ብቻ ሳይሆን እንደሚገባው" በማመን፣ በተለያዩ ግለሰቦችና ወዳጆቹ ሲቀርብ የነበረው ጥያቄና ሲደረግ የነበረው ጥረት ውጤት ማግኘቱ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች አስተላልፈዋል።

የቤት ስጦታ ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታዎች መካከል ታዋቂው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እና የአብዲሳ አጋ ልጅ ኤልያስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡

ይህንን አስደሳች ዜና የደራሲው የቅርብ ወዳጅ ተስፋ በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገጹ (ፌስቡክ) ላይ ባሰፈረው መረጃ ይፋ አድርጓል።

ደራሲው ለሀገር ካበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንፃር ይህ እውቅና እና ድጋፍ የሚገባው መሆኑን ደጋፊዎቹና የጥበብ ቤተሰቦች በደስታ እየገለጹ ይገኛሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
57👍7👏2
'የኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ዝቅተኛ ነው'

ዓለም አቀፉ የትምህርት ተቋም ኢዱኬሽን ፈርስት ይፋ ባደረገው የ2025 የእንግሊዝኛ ብቃት ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ 123 ሀገራት መካከል 65ኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ያስመዘገበችው አማካይ ነጥብ 499 ሲሆን ይህ ነጥብ ሀገሪቱን በሪፖርቱ የቀለም መለያ "ቢጫ" ወይም "Low Proficiency /ዝቅተኛ ብቃት" (450 - 499 ) በሚባለው ምድብ ውስጥ ያስቀምጣታል።

ኢትዮጵያ "መካከለኛ" (500 - 549) ተብሎ ከሚጠራው የተሻለ ምድብ ለመግባት የቀራት 1 ነጥብ ብቻ እንደሆነም ኖሮ ሬድዮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ዘገባ የተዘጋጀው በ2024 እ.ኤ.አ. ፈተናውን በወሰዱ 2.2 ሚሊዮን ሰዎች ውጤት ላይ ተመስርቶ ነው።

ሀገራት በዚህ ሪፖርት ለመካተት ቢያንስ 400 ተፈታኞች ሊኖሩት የሚገባ ሲሆን ከኢትዮጵያ ምን ያህል ተፈታኞች እንደተሳተፉ ባይታወቅም በዝርዝሩ መኖሯ ይህንን መስፈርት በማሟላቷ ለመሆኑ አመልካች ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ 28 ሀገራት መካከል 8ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ደቡብ አፍሪካ (602) እና ዚምባብዌ (602) ነጥብ በማምጣት በጣም ከፍተኛ ምድብ ውስጥ የተቀላቀሉ ሀገራት ሲሆኑ ከአፍሪካም መሪዎቹ ናቸው። በተጨማሪም ኬንያ (593) በማምጣት ከፍተኛ (550 - 549) በሚባል የብቃት ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ሪፖርቱ አክሎም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የእንግሊዝኛ ብቃት ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን አዲስ አበባ (522) ነጥብ በማምጣት መካከለኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ መቀሌ (518) እንዲሁም አዳማ (496) ነጥብ አስመዝግበዋል።

©️tikvahethmagazine

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👎103👍3😁3👏2
📌ቀነኒ አዱኛ ተገድላለች እንጂ ራሷን አላጠፋችም ሲል ታላቅ ወንድሟ ተናገረ

የታናሽ ወንድማቸው ሊበን አዱኛ ደህንነትም አደጋ ላይ መውደቁን ገልጿል።

የቀነኒ አዱኛ አሳዛኝ የህልፈት ዜና አሁንም መላውን ህዝብ እያስቆጣ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ታላቅ ወንድሟ ለማ አዱኛ ላለፉት ቀናት ይዞት የነበረውን ዝምታ በመስበር እጅግ ዘግናኝና ልብ የሚሰብሩ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

ለማ አዱኛ በሰጠው ምስክርነት፣ እህቱ ቀነኒ በምንም አይነት ሁኔታ ራሷን ለመጉዳት ፍላጎትም ሆነ ሀሳብ እንዳልነበራት ገልጾ፣ አስከሬኗን ቤት ውስጥ በተመለከተበት ወቅት ህይወቷ እንዲያልፍ የተደረገው እዚያው እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል።

ለማ እንደሚለው ከሆነ፣ የቀነኒ አስከሬን በያኔት ሆስፒታል በኩል አልፎ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ሲወሰድ ቤተሰቦች ሳያዩት በምስጢር ሊቀበር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ እሱ ግን በጉልበት ሳጥኑን ከፍቶ ለመመልከት በቻለበት ወቅት እህቱ ላይ ምንም አይነት ጭረት ወይም የተሰበረ አጥንት አለመኖሩን አረጋግጧል።

​"ለምን እኛ ሳናይ ሊቀብሯት ፈለጉ?" የሚለው ጥያቄ እስካሁን መልስ ያላገኘ ሲሆን፣ የመንግስት አካላት ቤተሰቡ ዝም እንዲል ጫና ሲያደርጉባቸው እንደነበርና አሁን ግን እውነታው ለዓለም ይፋ መሆን ስላለበት ድምፁን ለማሰማት መወሰኑን ለማ አዱኛ አስታውቋል።

ሌላው እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ፣ እውነቱን አውጥቷል በሚል የታናሽ ወንድማቸው ሊበን አዱኛ ደህንነት አደጋ ላይ መውደቁ ነው። ሊበን "ሚስጥር አውጥተሃል" በሚል የማስፈራሪያ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን ለማ ገልጾ፣ በወንድሙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ስጋቱን ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😭597🤔2😢2🕊1😡1
አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ህይወት ማለፍ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የባለቤቱ ወ/ሮ አስቴር አየለ እና የአቶ ይታየው ምትኬ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገብ በፍርድ ቤት ተዘግቷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ማክሰኞ ታህሳስ 28 ቀን ባዋለው ችሎት፣ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል። ፍርድ ቤቱ "ከዚህ በኋላ በዚህ መዝገብ ላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፍቀድ አይቻልም" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ቢዘጋም፣ የሟች ባለቤት ወ/ሮ አስቴር አየለ እና አቶ ይታየው ምትኬ አሁንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ይህንን ተከትሎ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች፣ ደንበኞቻቸው የምርመራ መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ በእስር መቆየታቸው ህገ-ወጥ ነው በማለት "አካልን ነጻ የማውጣት" አቤቱታ ለፍርድ ቤት ማስገባታቸው ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ከዚህ ቀደም ባጋጠመው የጋንግሪን ህመም ምክንያት የቀኝ እግሩን ያጣ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በድብርት እና ከሰዎች በመራቅ "ዋካንዳ" በተባለ ሆቴል ውስጥ ያርፍ ነበር። ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ሆቴል ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን፣ ከወራት በኋላ ቤተሰቦቹ በጋዜጠኛው አሟሟት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው መግለጻቸውንና ሚዲያዎችም "ቀጥተኛ ምስክር አለ" ብለው መዘገባቸውን ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል።

ከሁለት ወራት በፊት ፖሊስ ወ/ሮ አስቴርን፣ አቶ ይታየው ምትኬን እና የሆቴሉን ባለቤት በቁጥጥር ስር አውሎ የነበረ ሲሆን፣ የሆቴሉ ባለቤት ቀደም ብለው መለቀቃቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😢75🤔2😱1🕊1
📌የአዲስ አበባ ከተማ ቤተመፅሐፍቶች ለ810 ሺህ አንባቢ አገልግሎት ሰጥተዋል ተባለ

በተያዘው 2018 ግማሽ ዓመት ለ 810 ሺህ አንባቢያን የከተማዋ ቤተመፅሐፍቶች አገልግሎት መስጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልጿል።

አሁን ላይ ባለው የመፅሐፍት ዋጋ ንረትና የብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ አንድን መፅሐፍ እስከ 67 ሺህ ብር ድረስ ቢሮው እገዛ ነው ሲሉ በቢሮው የቤተ መፅሐፍት ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ መኮንን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ከዓመታዊ በጀቱ ከፍተኛውን በጀት ለመፅሐፍት ግዢ እንደሚያውልም ገልጸዋል።

በከተማዋ 82 የሕዝብ ቤተመፅሐፍቶች መኖራቸውን ገልፀው ተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ መፅሐፍት ቤቶችን ለማስገንባት በጀት ተመድቦ ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ባለፈ ነዋሪዎች በሚበዙባቸው የሸገር ከተማ አካባቢዎች ቤተ መጽሐፍቶችን ለማስፋፋት ጥናቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ሰምተናል።

©️አራዳ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
🙏112
📌ታዋቂው ኬሮግራፈር ተመስገን መለሠ የኢትዮጵያን ባህል ለዓለም የሚያስተዋውቅ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን አጠናቀቀ

ኬሮግራፈር ተመስገን መለሠ (ልጅ ተመስገን) 17 ብሔር ብሔረሰቦችን የዳሰሰ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊቀርብ እንደሆነ እውቁ ብሏል።

በዳንስ ጥበብ ዘርፍ "የተመስገን ልጆች" የተሰኘውን ቡድን በማቋቋምና በቅርቡም "ንህነ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በማብቃት የሚታወቀው ባለሙያው፤ አሁን ደግሞ በሙዚቃው ዘርፍ አዲስ ፈጠራ ይዞ ብቅ ብሏል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለት ይህ "ኢቲዲኤም ቢትስ" አልበም፣ የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ የሙዚቃ ቅኝቶች ከዘመናዊ የሙዚቃ ዘውጎች ጋር በማዋሃድ የተሰራ ነው።

አልበሙ በአጠቃላይ የ17 ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዘመናዊ ቢቶች ጋር አቀናጅቶ የያዘ ሲሆን፣ በውስጡም 13 የተለያዩ ትራኮችን አካትቷል።

ከእነዚህም መካከል ለሁለቱ ሙዚቃዎች የቪዲዮ ስራቸውን ማጠናቀቁ ታውቋል።በሙዚቃ ቪዲዮ አዘጋጅነት ሰውመሆን ይስማው ተሳትፏል።

የአልበሙ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን እምቅ የባህል የሙዚቃ ሀብት ለዓለም አቀፉ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ማስተዋወቅና የባህል ውክልናን ማሳየት እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ አልበም በመጪው አርብ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም የሙዚቃ ማሰራጫዎች ለሙዚቃ አድማጮች እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
11👍3
📌ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ በመዲናችን !

የአፍሪካን የፈጠራ ጥበብ ከዓለም አቀፍ የፋሽን ኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት ግንባር ቀደም የሆነው "ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ" (HAFW) 15ኛው ዝግጅት ከጥር 5 እስከ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (January 13-17, 2026) በአዲስ አበባ ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል እንደሚያካሄድ ተገልጿል።

​ባለፉት 15 ዓመታት መድረኩ ከ250 በላይ አህጉራዊ ብራንዶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ከ1,000 በላይ ሞዴሎችና ከ200 በላይ ዲዛይነሮች የሥራ ዕድልና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ድልድይ ሆኗል።

የዝግጅቱ መስራች ማህሌት ተክለማርያም በዓለም አቀፉ የፋሽን መረጃ ማዕከል "BOF 500" (Class of 2025) ውስጥ ተካታ ዕውቅና ማግኘቷ ለዘንድሮው ዝግጅት ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል። 

​የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን እና ሩሲያ የተውጣጡ አንጋፋና ጀማሪ ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ። 

በ"ጉዞ ቴክኖሎጂስ" አማካኝነት በቨርቹዋል ሪያሊቲ (VR) የታገዘ የፋሽን ትርዒት ለዕይታ ይቀርባል። የፋሽን ዘርፍ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ስላለው የ31 ቢሊዮን ዶላር ተፅዕኖ በባለሙያዎች የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።

​ዝግጅቱ "ለነገው" (Lenegew) ከተሰኘውና አስቸጋሪ ሕይወት ያሳለፉ ሴቶችን ከሚደግፍ ፕሮጀክት ጋር በመሆን የልገሳና የምክር አገልግሎት መርሐግብር ይኖረዋል።

​በመዝጊያ ዕለቱ የሀገር ውስጥ የጥበብ ውጤቶች፣ የውበት መጠበቂያዎችና የቤት ውስጥ ዲኮሮች ለሽያጭ የሚቀርቡበት የገበያ መድረክ ይዘጋጃል።

​ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
6👍3
📌 አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ እና ቲክቶከሮቹ

ታዋቂውና አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፣ በተለያዩ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አማካኝነት ክብሩን የሚነኩ ጥቃቶች እየተሰነዘሩበት መሆኑ ቅሬታን እየፈጠረ ይገኛል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አርቲስቱ የታክሲ ወረፋ ላይ ተሰልፎ ወይም በእግሩ ሲጓዝ የሚያሳዩ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን በማንሳት ወደ ማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) የመጫን አዝማሚያ በስፋት እየታየ እንደሆነ ኖር ሬድዮ ያሰባሰበው መረጃ ያመለክታል።

እነዚህ ምስሎች በሚለቀቁበት የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ውስጥም፣ አርቲስቱን ዝቅ የሚያደርጉና ስብእናውን የሚነኩ ስድቦች በብዛት እንደሚሰነዘሩ ተስተውሏል።

ይህንን ድርጊት በጽኑ የተቃወሙት የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያው ሄኖክ ናሁሰናይ፣ "እባካችሁ አርቲስቱን ተዉት" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሄኖክ ባሰፈሩት ጽሑፍ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል። አርቲስቱ እንደማንኛውም ዜጋ በሰላም ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።

እርዳታ ያልጠየቀንና እጁን ለልመና ያልዘረጋን ሰው፣ ምስሉን ያለፈቃዱ በመልቀቅ "ለመለመኛ" ማዋል ተገቢ አይደለም።

አርቲስቱን በማህበራዊ ሚዲያ ለባለጌ ተሳዳቢዎች መጋለጥ የለበትም የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
25😭8👍3💔3👎1
📌ልጅ ተመስገን ስለ ፀጉር ስታይሉ ምላሽ ሰጠ

ታዋቂው ኬሮግራፈር ልጅ ተመስገን "ኢቲዲኤም ቢትስ" የተሰኘ አዲስና ልዩ የሙዚቃ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል።

ነገር ግን ከአልበሙ ዜና በበለጠ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የአርቲስቱ የፀጉር ስታይል ነው። ከኖር ሬድዮ አዘጋጆች ስለ ፀጉር አቆራረጡ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ በእጅጉ ልብ የሚነካና የኢትዮጵያዊነት ኩራትን ያሳየ ነበር።

ብዙዎች ይህንን የፀጉር ስታይል እንደ አዲስና ዘመናዊ ፋሽን ቢመለከቱትም ልጅ ተመስገን ግን ፀጉሩ የባዕድ ሳይሆን በጎጃም "ጉትዬ" ተብሎ የሚጠራው ባህላዊ የፀጉር አቆራረጥ መሆኑን ገልጿል።

​በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የራሱ ስያሜ ቢኖረውም በተለይ በጎጃም ልጆች ዘንድ የሚዘወተረው ይህ "ጉትዬ" ጥንታዊ የባህል መገለጫ ነው።

አርቲስቱ በዘመናዊ አቆራረጥ ፋንታ ይህንን የመረጠው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቡን ለማሳየት ሲንቀሳቀስ ሙዚቃውን ብቻ ሳይሆን የሀገሩን የፀጉር ስታይልና ባህላዊ እሴቶችንም ጭምር ለማስተዋወቅ በማለም እንደሆነ ተናግሯል።

ይህ ድርጊቱ ለባህል ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አክብሮት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ለዘመናዊው ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

​ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁2414👏12👎2