Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ገናን በካስማ ቤት ልዩ የበዓል የመዝናኛ ዝግጅት

👉 https://youtu.be/M6CXM_yNjcQ
📌"በከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" መጽሐፍ ላይ ውይይት

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ
መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ቅዳሜ ጥር 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በተጋባዥ እንግዳነት ኢዛና አምደወርቅ (ዶ/ር) ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።
11👍1
📌 ከወጣት ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ቡና እየጠጣችሁ ስለስራ ምታወሩበት መድረክ ሊፈጠር ነው።

( ቅድሚያ ለተመዘገበ መግቢያው በነፃ ነው)

ከ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ኑ ቡና ጠጡ

ከተወዳጁ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ቡና እየጠጣችሁ መስራት የምትፈልጉዋቸውን ስራዎች ከ እሱ ጋር የምታወሩበት እና የምትወያዩበት መድረክ ተዘጋጅቷል።

የራሳችሁን ሥራዎች እንዲሁም ያለውን ልምድ አንድ ለ አንድ በሚፈጠረው መድረክ ላይ ስለሰራቸው ሙዚቃዎች እንዲሁም ቀጣይ ስለሚያስባቸው ስራዎቹ የሚያካፍልበት የ ሲንክ አፕ ቻት ፕሮግራም ሲሆን ይህ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎ ስንል እንጋብዛለን።

📅️️️️ ቀን ፡ ጥር 9
⏰️️️️️️️ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ
📍️️️️ቦታ ፡ ጋዬ ቡና ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ( ካፕስቶን ህንፃ )

🎟️️️️ ትኬት
- ቀድመው ለቆረጡ - በነፃ ( ከነፃ ቡና ጋር )
- መደበኛ - 500 ብር ( ከ ነፃ ቡና ጋር )
- ቪአይፒ - 1000 ብር ( ከነፃ ቡና እና ምግብ ጋር )

ያለን ቦታ ውስን ሰለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ

ትኬትዎን ለመቁረጥ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ👇️️️️️️
https://linktr.ee/SyncUp.chat


ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4👍4❤‍🔥1🔥1🥰1👏1🤔1🤗1
📌ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ቤት ተሰጠው

አንጋፋው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የመኖሪያ ቤት እንደተሰጠው ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው "ቤት እንደሚያስፈልገው ብቻ ሳይሆን እንደሚገባው" በማመን፣ በተለያዩ ግለሰቦችና ወዳጆቹ ሲቀርብ የነበረው ጥያቄና ሲደረግ የነበረው ጥረት ውጤት ማግኘቱ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች አስተላልፈዋል።

የቤት ስጦታ ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታዎች መካከል ታዋቂው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እና የአብዲሳ አጋ ልጅ ኤልያስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡

ይህንን አስደሳች ዜና የደራሲው የቅርብ ወዳጅ ተስፋ በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገጹ (ፌስቡክ) ላይ ባሰፈረው መረጃ ይፋ አድርጓል።

ደራሲው ለሀገር ካበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንፃር ይህ እውቅና እና ድጋፍ የሚገባው መሆኑን ደጋፊዎቹና የጥበብ ቤተሰቦች በደስታ እየገለጹ ይገኛሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
57👍7👏2
'የኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ዝቅተኛ ነው'

ዓለም አቀፉ የትምህርት ተቋም ኢዱኬሽን ፈርስት ይፋ ባደረገው የ2025 የእንግሊዝኛ ብቃት ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ 123 ሀገራት መካከል 65ኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ያስመዘገበችው አማካይ ነጥብ 499 ሲሆን ይህ ነጥብ ሀገሪቱን በሪፖርቱ የቀለም መለያ "ቢጫ" ወይም "Low Proficiency /ዝቅተኛ ብቃት" (450 - 499 ) በሚባለው ምድብ ውስጥ ያስቀምጣታል።

ኢትዮጵያ "መካከለኛ" (500 - 549) ተብሎ ከሚጠራው የተሻለ ምድብ ለመግባት የቀራት 1 ነጥብ ብቻ እንደሆነም ኖሮ ሬድዮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ዘገባ የተዘጋጀው በ2024 እ.ኤ.አ. ፈተናውን በወሰዱ 2.2 ሚሊዮን ሰዎች ውጤት ላይ ተመስርቶ ነው።

ሀገራት በዚህ ሪፖርት ለመካተት ቢያንስ 400 ተፈታኞች ሊኖሩት የሚገባ ሲሆን ከኢትዮጵያ ምን ያህል ተፈታኞች እንደተሳተፉ ባይታወቅም በዝርዝሩ መኖሯ ይህንን መስፈርት በማሟላቷ ለመሆኑ አመልካች ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ 28 ሀገራት መካከል 8ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ደቡብ አፍሪካ (602) እና ዚምባብዌ (602) ነጥብ በማምጣት በጣም ከፍተኛ ምድብ ውስጥ የተቀላቀሉ ሀገራት ሲሆኑ ከአፍሪካም መሪዎቹ ናቸው። በተጨማሪም ኬንያ (593) በማምጣት ከፍተኛ (550 - 549) በሚባል የብቃት ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ሪፖርቱ አክሎም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የእንግሊዝኛ ብቃት ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን አዲስ አበባ (522) ነጥብ በማምጣት መካከለኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ መቀሌ (518) እንዲሁም አዳማ (496) ነጥብ አስመዝግበዋል።

©️tikvahethmagazine

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👎103👍3😁3👏2
📌ቀነኒ አዱኛ ተገድላለች እንጂ ራሷን አላጠፋችም ሲል ታላቅ ወንድሟ ተናገረ

የታናሽ ወንድማቸው ሊበን አዱኛ ደህንነትም አደጋ ላይ መውደቁን ገልጿል።

የቀነኒ አዱኛ አሳዛኝ የህልፈት ዜና አሁንም መላውን ህዝብ እያስቆጣ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ታላቅ ወንድሟ ለማ አዱኛ ላለፉት ቀናት ይዞት የነበረውን ዝምታ በመስበር እጅግ ዘግናኝና ልብ የሚሰብሩ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

ለማ አዱኛ በሰጠው ምስክርነት፣ እህቱ ቀነኒ በምንም አይነት ሁኔታ ራሷን ለመጉዳት ፍላጎትም ሆነ ሀሳብ እንዳልነበራት ገልጾ፣ አስከሬኗን ቤት ውስጥ በተመለከተበት ወቅት ህይወቷ እንዲያልፍ የተደረገው እዚያው እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል።

ለማ እንደሚለው ከሆነ፣ የቀነኒ አስከሬን በያኔት ሆስፒታል በኩል አልፎ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ሲወሰድ ቤተሰቦች ሳያዩት በምስጢር ሊቀበር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ እሱ ግን በጉልበት ሳጥኑን ከፍቶ ለመመልከት በቻለበት ወቅት እህቱ ላይ ምንም አይነት ጭረት ወይም የተሰበረ አጥንት አለመኖሩን አረጋግጧል።

​"ለምን እኛ ሳናይ ሊቀብሯት ፈለጉ?" የሚለው ጥያቄ እስካሁን መልስ ያላገኘ ሲሆን፣ የመንግስት አካላት ቤተሰቡ ዝም እንዲል ጫና ሲያደርጉባቸው እንደነበርና አሁን ግን እውነታው ለዓለም ይፋ መሆን ስላለበት ድምፁን ለማሰማት መወሰኑን ለማ አዱኛ አስታውቋል።

ሌላው እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ፣ እውነቱን አውጥቷል በሚል የታናሽ ወንድማቸው ሊበን አዱኛ ደህንነት አደጋ ላይ መውደቁ ነው። ሊበን "ሚስጥር አውጥተሃል" በሚል የማስፈራሪያ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን ለማ ገልጾ፣ በወንድሙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ስጋቱን ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😭597🤔2😢2🕊1😡1
አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ህይወት ማለፍ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የባለቤቱ ወ/ሮ አስቴር አየለ እና የአቶ ይታየው ምትኬ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገብ በፍርድ ቤት ተዘግቷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ማክሰኞ ታህሳስ 28 ቀን ባዋለው ችሎት፣ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል። ፍርድ ቤቱ "ከዚህ በኋላ በዚህ መዝገብ ላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፍቀድ አይቻልም" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ቢዘጋም፣ የሟች ባለቤት ወ/ሮ አስቴር አየለ እና አቶ ይታየው ምትኬ አሁንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ይህንን ተከትሎ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች፣ ደንበኞቻቸው የምርመራ መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ በእስር መቆየታቸው ህገ-ወጥ ነው በማለት "አካልን ነጻ የማውጣት" አቤቱታ ለፍርድ ቤት ማስገባታቸው ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ከዚህ ቀደም ባጋጠመው የጋንግሪን ህመም ምክንያት የቀኝ እግሩን ያጣ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በድብርት እና ከሰዎች በመራቅ "ዋካንዳ" በተባለ ሆቴል ውስጥ ያርፍ ነበር። ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ሆቴል ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን፣ ከወራት በኋላ ቤተሰቦቹ በጋዜጠኛው አሟሟት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው መግለጻቸውንና ሚዲያዎችም "ቀጥተኛ ምስክር አለ" ብለው መዘገባቸውን ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል።

ከሁለት ወራት በፊት ፖሊስ ወ/ሮ አስቴርን፣ አቶ ይታየው ምትኬን እና የሆቴሉን ባለቤት በቁጥጥር ስር አውሎ የነበረ ሲሆን፣ የሆቴሉ ባለቤት ቀደም ብለው መለቀቃቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😢75🤔2😱1🕊1
📌የአዲስ አበባ ከተማ ቤተመፅሐፍቶች ለ810 ሺህ አንባቢ አገልግሎት ሰጥተዋል ተባለ

በተያዘው 2018 ግማሽ ዓመት ለ 810 ሺህ አንባቢያን የከተማዋ ቤተመፅሐፍቶች አገልግሎት መስጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልጿል።

አሁን ላይ ባለው የመፅሐፍት ዋጋ ንረትና የብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ አንድን መፅሐፍ እስከ 67 ሺህ ብር ድረስ ቢሮው እገዛ ነው ሲሉ በቢሮው የቤተ መፅሐፍት ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ መኮንን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ከዓመታዊ በጀቱ ከፍተኛውን በጀት ለመፅሐፍት ግዢ እንደሚያውልም ገልጸዋል።

በከተማዋ 82 የሕዝብ ቤተመፅሐፍቶች መኖራቸውን ገልፀው ተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ መፅሐፍት ቤቶችን ለማስገንባት በጀት ተመድቦ ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ባለፈ ነዋሪዎች በሚበዙባቸው የሸገር ከተማ አካባቢዎች ቤተ መጽሐፍቶችን ለማስፋፋት ጥናቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ሰምተናል።

©️አራዳ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
🙏112
📌ታዋቂው ኬሮግራፈር ተመስገን መለሠ የኢትዮጵያን ባህል ለዓለም የሚያስተዋውቅ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን አጠናቀቀ

ኬሮግራፈር ተመስገን መለሠ (ልጅ ተመስገን) 17 ብሔር ብሔረሰቦችን የዳሰሰ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊቀርብ እንደሆነ እውቁ ብሏል።

በዳንስ ጥበብ ዘርፍ "የተመስገን ልጆች" የተሰኘውን ቡድን በማቋቋምና በቅርቡም "ንህነ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በማብቃት የሚታወቀው ባለሙያው፤ አሁን ደግሞ በሙዚቃው ዘርፍ አዲስ ፈጠራ ይዞ ብቅ ብሏል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለት ይህ "ኢቲዲኤም ቢትስ" አልበም፣ የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ የሙዚቃ ቅኝቶች ከዘመናዊ የሙዚቃ ዘውጎች ጋር በማዋሃድ የተሰራ ነው።

አልበሙ በአጠቃላይ የ17 ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዘመናዊ ቢቶች ጋር አቀናጅቶ የያዘ ሲሆን፣ በውስጡም 13 የተለያዩ ትራኮችን አካትቷል።

ከእነዚህም መካከል ለሁለቱ ሙዚቃዎች የቪዲዮ ስራቸውን ማጠናቀቁ ታውቋል።በሙዚቃ ቪዲዮ አዘጋጅነት ሰውመሆን ይስማው ተሳትፏል።

የአልበሙ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን እምቅ የባህል የሙዚቃ ሀብት ለዓለም አቀፉ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ማስተዋወቅና የባህል ውክልናን ማሳየት እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ አልበም በመጪው አርብ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም የሙዚቃ ማሰራጫዎች ለሙዚቃ አድማጮች እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
11👍3
📌ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ በመዲናችን !

የአፍሪካን የፈጠራ ጥበብ ከዓለም አቀፍ የፋሽን ኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት ግንባር ቀደም የሆነው "ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ" (HAFW) 15ኛው ዝግጅት ከጥር 5 እስከ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (January 13-17, 2026) በአዲስ አበባ ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል እንደሚያካሄድ ተገልጿል።

​ባለፉት 15 ዓመታት መድረኩ ከ250 በላይ አህጉራዊ ብራንዶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ከ1,000 በላይ ሞዴሎችና ከ200 በላይ ዲዛይነሮች የሥራ ዕድልና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ድልድይ ሆኗል።

የዝግጅቱ መስራች ማህሌት ተክለማርያም በዓለም አቀፉ የፋሽን መረጃ ማዕከል "BOF 500" (Class of 2025) ውስጥ ተካታ ዕውቅና ማግኘቷ ለዘንድሮው ዝግጅት ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል። 

​የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን እና ሩሲያ የተውጣጡ አንጋፋና ጀማሪ ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ። 

በ"ጉዞ ቴክኖሎጂስ" አማካኝነት በቨርቹዋል ሪያሊቲ (VR) የታገዘ የፋሽን ትርዒት ለዕይታ ይቀርባል። የፋሽን ዘርፍ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ስላለው የ31 ቢሊዮን ዶላር ተፅዕኖ በባለሙያዎች የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።

​ዝግጅቱ "ለነገው" (Lenegew) ከተሰኘውና አስቸጋሪ ሕይወት ያሳለፉ ሴቶችን ከሚደግፍ ፕሮጀክት ጋር በመሆን የልገሳና የምክር አገልግሎት መርሐግብር ይኖረዋል።

​በመዝጊያ ዕለቱ የሀገር ውስጥ የጥበብ ውጤቶች፣ የውበት መጠበቂያዎችና የቤት ውስጥ ዲኮሮች ለሽያጭ የሚቀርቡበት የገበያ መድረክ ይዘጋጃል።

​ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
6👍3
📌 አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ እና ቲክቶከሮቹ

ታዋቂውና አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፣ በተለያዩ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አማካኝነት ክብሩን የሚነኩ ጥቃቶች እየተሰነዘሩበት መሆኑ ቅሬታን እየፈጠረ ይገኛል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አርቲስቱ የታክሲ ወረፋ ላይ ተሰልፎ ወይም በእግሩ ሲጓዝ የሚያሳዩ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን በማንሳት ወደ ማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) የመጫን አዝማሚያ በስፋት እየታየ እንደሆነ ኖር ሬድዮ ያሰባሰበው መረጃ ያመለክታል።

እነዚህ ምስሎች በሚለቀቁበት የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ውስጥም፣ አርቲስቱን ዝቅ የሚያደርጉና ስብእናውን የሚነኩ ስድቦች በብዛት እንደሚሰነዘሩ ተስተውሏል።

ይህንን ድርጊት በጽኑ የተቃወሙት የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያው ሄኖክ ናሁሰናይ፣ "እባካችሁ አርቲስቱን ተዉት" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሄኖክ ባሰፈሩት ጽሑፍ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል። አርቲስቱ እንደማንኛውም ዜጋ በሰላም ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።

እርዳታ ያልጠየቀንና እጁን ለልመና ያልዘረጋን ሰው፣ ምስሉን ያለፈቃዱ በመልቀቅ "ለመለመኛ" ማዋል ተገቢ አይደለም።

አርቲስቱን በማህበራዊ ሚዲያ ለባለጌ ተሳዳቢዎች መጋለጥ የለበትም የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
25😭8👍3💔3👎1
📌ልጅ ተመስገን ስለ ፀጉር ስታይሉ ምላሽ ሰጠ

ታዋቂው ኬሮግራፈር ልጅ ተመስገን "ኢቲዲኤም ቢትስ" የተሰኘ አዲስና ልዩ የሙዚቃ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል።

ነገር ግን ከአልበሙ ዜና በበለጠ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የአርቲስቱ የፀጉር ስታይል ነው። ከኖር ሬድዮ አዘጋጆች ስለ ፀጉር አቆራረጡ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ በእጅጉ ልብ የሚነካና የኢትዮጵያዊነት ኩራትን ያሳየ ነበር።

ብዙዎች ይህንን የፀጉር ስታይል እንደ አዲስና ዘመናዊ ፋሽን ቢመለከቱትም ልጅ ተመስገን ግን ፀጉሩ የባዕድ ሳይሆን በጎጃም "ጉትዬ" ተብሎ የሚጠራው ባህላዊ የፀጉር አቆራረጥ መሆኑን ገልጿል።

​በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የራሱ ስያሜ ቢኖረውም በተለይ በጎጃም ልጆች ዘንድ የሚዘወተረው ይህ "ጉትዬ" ጥንታዊ የባህል መገለጫ ነው።

አርቲስቱ በዘመናዊ አቆራረጥ ፋንታ ይህንን የመረጠው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቡን ለማሳየት ሲንቀሳቀስ ሙዚቃውን ብቻ ሳይሆን የሀገሩን የፀጉር ስታይልና ባህላዊ እሴቶችንም ጭምር ለማስተዋወቅ በማለም እንደሆነ ተናግሯል።

ይህ ድርጊቱ ለባህል ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አክብሮት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ለዘመናዊው ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

​ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁2414👏12👎2
📌የአንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ አነጋጋሪ ምላሽ

አንጋፋው ድምጻዊ እና የዜማ ደራሲ ነዋይ ደበበ፣ በቅርቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ስላወጣው ነጠላ ዜማ እና ከዓመታት በፊት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት አውጥቶት ስለነበረው የለቅሶ ዜማ አዳዲስና አነጋጋሪ አስተያየቶችን ሰጥቷል።

ነዋይ በአርትስ ቲቪ ከአርቲስት አዳነች ወልደ ገብርኤል ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ፣ ለ120 ሚሊዮን ህዝብ ክብር እና እንደ አንድ የጥበብ ሰው ለአባይ ግድብ ለመዝፈን ስላልቻለ፣ በ3 እና 4 ቀናት ውስጥ የተቀናበረ አዲስ ስራ ለምረቃው ማድረሱን ተናግሯል። ስራው በፍጥነት የተሰራ ቢሆንም በጥራት ለበዓሉ መድረሱን የገለጸው ድምጻዊው፣ ለዚህ ስራውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ምስጋና እንዳቀረቡለት ገልጿል።

በሌላ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲሞቱ ስለዘፈነው የለቅሶ ዜማ ሲጠየቅ፣ "ሰው ይቅርና ወፍም ሲሞት ኢትዮጵያዊ ያለቅሳል" በማለት ባህሉን ያስታወሰው ነዋይ፤ ሆኖም ለዚያ ዘፈን የኢትዮጵያን ህዝብ መልሶ ይቅርታ እንደጠየቀ አረጋግጧል።

ይቅርታ የጠየቀበትን እና የሚቆጨውን ምክንያት ሲያስረዳም፣ "አሰብን ለካ፣ በአደራ ያስረከቡት እሳቸው መሆኑ አሁን ነው በደንብ እየገባኝ የመጣው" ብሏል። በተለይም የቀይ ባህር ጉዳይ እንደሚቆጨው ሲገልጽ፣ "ቀይ ባህርን የሚያክል ትልቅ ሀብት ግመል ይጠጣበት ብለው ሰጥተዋል የሚለውን በወቅቱ ብረዳ ኖሮ እና ውስጤ ቢኖር ኖሮ፣ ያን ዜማ አላወጣውም ነበር" ሲል በቁጭት ተናግሯል።

ድምጻዊው አክሎም፣ ለተለያዩ ድምጻዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን፣ እስካሁን ለሰዎች የሰጣቸው ዘፈኖች ቁጥር 150 እንደሚደርሱም ጠቁሟል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁16👎84🗿4🤬1
📌ዝነኛው የማስታወቂያ ባለሞያ ከህክምና መልስ

ተወዳጁ የማስታወቂያ ባለሙያና አርቲስት ዘላለም ኮራባቸው በቱርክ ሀገር ሲከታተል የነበረውን የህክምና እርዳታ አጠናቆ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

ኖር ሬድዮ ከቅርብ ወዳጆቹ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ አርቲስቱ በገጠመው የጤና እክል ምክንያት በቱርክ ሀገር ለሁለት ሳምንታት ያህል የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በቆይታው የተደረገለት ህክምና በስኬት መጠናቀቁ ታውቋል።

አርቲስቱ ወደ ሀገሩ ሲመለስ በወዳጅ ዘመዶቹ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፣ ትላንት ቅዳሜም በመኖሪያ ቤቱ የምሳ ግብዣ ተካሂዷል።

ባለአስገምጋሚ ድምፁ ዘላለም ኮራባቸው የኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ ማስታወቂያዎችን በመስራት ይታወቃል። በተጨማሪም በተለያዩ ፊልሞችና ተከታታይ ድራማዎች ላይ በተዋናይነት ተሳትፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
6👍2🙏2
📌የሮቤል ሚደቅሳ "እንደ ቀልድ" ሙዚቃ ቪዲዮ

"ከበር አፍ" በተሰኘው የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙ የአድናቂዎቹን ቀልብ መሳብ የቻለው ድምጻዊ ሮቤል ሚደቅሳ፣ በአልበሙ ውስጥ ለተካተተውና ከፍተኛ ተወዳጅነት ላገኘው "እንደ ቀልድ" ለተሰኘው ስራው የሙዚቃ ቪዲዮ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልእክት፣ አድናቂዎቹ ሙዚቃውን በቪዲዮ እንዲያቀርብላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁት እንደነበር አስታውሷል።

"የመጀመሪያው ሰርፕራይዝ!" ሲል የጀመረው ሮቤል፣ የቪዲዮ ስራው ተጠናቆ ለተመልካች የሚቀርብበት ቀን መቆረጡን በደስታ ገልጿል።

እንደ ድምጻዊው ገለጻ፣ "እንደ ቀልድ" የፊታችን ማክሰኞ ጥር 5 ለህዝብ እይታ ይበቃል። ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ ከአልበሙ ውስጥ የሚወጣ የመጀመሪያው ምስላዊ ስራ በመሆኑ በአድናቂዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።

የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር ዮናታን መስፍን ነው።

ሮቤል ሚደቅሳ በቅርቡ ለአድማጮች ባቀረበው "ከበር አፍ" አልበሙ በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ መልካም የሚባል አቀባበል እንዳገኘ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
14👍2
📌አፍሪማን ቬሮኒካ አዳነ፣ሀዲንቆ፣ ዊሀ  አሸነፉ

በታላቁ አህጉራዊ የሙዚቃ ሽልማት መላ አፍሪካ የሙዚቃ አዋርድ (AFRIMA 2025) ላይ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ደማቅ ድል አስመዘገቡ።

በዚህ ደማቅ የሽልማት ስነስርዓት ላይ ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነሀዲስ አለማየሁ (ሀዲንቆ) እና ዊሀ በየተሰማሩባቸው የሙዚቃ ዘርፎች አሸናፊ መሆናቸው ተረጋግጧል።

አርቲስቶቹ በአህጉሪቱ በሚገኙ ሶስት የተለያዩ የሙዚቃ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ለዚህ ክብር የበቁ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና እያሳየ ያለውን እድገት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

ቬሮኒካ አዳነ፣ ሀዲንቆ እና ዊሀ ባስመዘገቡት የላቀ የፈጠራ ስራና ባላቸው ተሰጥኦ የአፍሪካን ታላላቅ ሙዚቀኞች በመብለጥ ሽልማቱን በእጃቸው አስገብተዋል።

ይህ ድል የኢትዮጵያን የጥበብ ስራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይበልጥ ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የኪነጥበብ ባለሙያዎች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
19🔥9
📌በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሰርጉ ተሰረዘ

በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የተሰማውና ብዙዎችን ያነጋገረው የሰርግ ታሪክ፣ በወጪ ብዛት ሳይሆን በፍጻሜው አስደናቂነት መነጋገሪያ ሆኗል።

ሁሉም ነገር ተሰናድቶ፣ የሰርግ አዳራሹ አሸብርቆ፣ ምግብና መጠጡ ሞልቶ የተጠበቀው ሰርግ፣ በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ኖር ሬድዮ ታሪኩን እንዲህ ይነግራችኋል ለዓመታት በትውውቅ የቆዩትና ሙሽራው በውጭ ሀገር የሚኖረው እነዚህ ጥንዶች፣ ጋብቻቸውን ለመፈጸም የለፋ ወጪ አውጥተው ነበር።

ለምሳሌ ያህል ለክትፎ ብቻ 450 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (Advance) ተከፍሎ ነበር። ዲኮሩም ከትናንትናው ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተሰርቶ አልቋል።

​ነገር ግን በሰርጉ ዋዜማና በዕለቱ በተፈጠረ አለመግባባት ነገሮች ተበላሹ። ሙሽሪት "ከጋብቻ በፊት የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን" የሚል ጥያቄ ታነሳለች። ሙሽራው በበኩሉ ይህንን ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም ወይም ጊዜው አልፈቀደም ተብሏል።

በዚህ መሃል "ሙሽራው ከዚህ በፊት ትዳር ነበረው፣ አምስት ልጆችም አሉት" የሚሉ ወሬዎችና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸው ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። ሽማግሌዎች ገብተው ለማስማማት ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል።

​በመጨረሻም በሰርጉ ቀን ሙሽራውና ሚዜዎቹ ዘንጠው ተዘጋጅተው ቢጠብቁም፣ ሙሽሪት ግን "አልመጣም" በማለት ቀረች።

ተጋባዥ እንግዶችም አንዳንዶቹ ጉዳዩን ሰምተው ሳይመጡ ቀርተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወጪ የፈሰሰበት ይህ ሰርግ፣ ሙሽራው ብቻውን ከሚዜዎቹ ጋር በባዶ አዳራሽ ፎቶ ተነስቶ ወደ ቤቱ በመመለሱ ተጠናቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁2813👍10🤔4👏3💔2🤷2
📌ዝነኛው አይሾው ስፒድ አዲስ አበባ ገባ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ዝነኛው አሜሪካዊ ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ገብቷል።

ዩቲዩበሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ተከትሎም የቀጥታ ሥርጭት (Livestream) እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተዘዋወረ በሚያደርጋቸው አዝናኝና አስገራሚ የቀጥታ ሥርጭቶቹ የሚታወቀው አይሾው ስፒድ (IShowSpeed)፤ ከሰዓታት በኋላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደሚደርስ በገጹ ጽፏ ነበር።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👍10👎83
📌ኮምሽነር ሌሊሴ ዱጋ የክብር አምባሳደር ሆነዋል

ኮምሽነር ሌሊሴ ዱጋ የኢትዮጵያ የሕፃናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ማኅበር የክብር አምባሳደር ሆነዋል።

በኢትዮጵያችን በየዓመቱ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት በካንሰር በሽታ ይጠቃሉ።ይሁን እንጂ ወደ ሕክምና ማዕከላት መጥተው ሕክምና የሚያገኙት ሕፃናት ቁጥር ከ2 ሺህ አይበልጥም።

በአደጉ ሀገራት የሕፃናት ካንሰር ታማሚዎች የመዳን ምጣኔ ከ85% በላይ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን በምርመራ መዘግየት፤ በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው የግንዛቤ ውስንነት፣ በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች እጥረት፣ ምክንያት ውጤቱ አሁንም እጅግ ዝቅተኛ ነው።

ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የተቀናጀ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት 35 መደበኛ አባላትን እና ከ150 በላይ ተባባሪ አባላትን ይዞ ጥር 4 2018 ዓ.ም "የኢትዮጵያ የሕፃናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ማኅበር" በይፋ ተመስርቷል።

በዚህ የማኀበሩ ምስረታ ማብሰሪያ ዝግጅት ላይም በከፍተኛ የስራ ኃላፊ ደረጃ የጤና ሁኔታ ለሕዝብ ማጋራት ባልተለመደበት ማኅበረሰብ ውስጥ የካንሰር ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ፎቷቸውን ጭምር አያይዘው በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩትና በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው የሰንበቱት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ ህክምናቸውን ከሚከታተሉበት ጆርዳን አማን በቪዲዮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኮሚሸነሯ በመልዕክታቸው"አላስፈላጊ ስቃይን የምናስቆምበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጻፍ አለብን" ያሉ ሲሆን በተጨማሪም የዚህ ማኅበር የክብር አምባሳደር በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
8👏4👍3😢1
📌የድምጻዊ ዮናታን ንብረት አዲስ ሙዚቃ ሊለቅ ነው

በፋና ላምሮት የድምፃውያን ውድድር ላይ በነበረው የላቀ ብቃት የሚታወቀው ድምፃዊ ዮናታን ንብረት፤ "እድሜ ላንቺ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃውን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ።

ድምጻዊ ዮናታን "እድሜ ላንቺ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ የፊታችን አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሕዝብ እንደሚደርስ ገልጿል።

ለረጅም ጊዜ ከሙዚቃ አፍቃሪያን እይታ ርቆ የቆየው ድምፃዊው፤ ቆይታው ጥራት ያላቸውን ሥራዎች ለማቅረብ በሚደረግ ዝግጅት መሆኑን ጠቅሶ ለደጋፊዎቹ ይቅርታን ጠይቋል።

በዚህ አዲስ የሙዚቃ ሥራ ላይ በግጥም ኑረዲን ኢሳ በዜማ አበበ ብርሃኔ በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ ተሳትፈውበታል።

ድምፃዊው ይህንን ሥራውን ተከትሎ ሌሎች ተከታታይ የሙዚቃ ሥራዎችን ለታዳሚ ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
20
📌 አይሾው ስፒድ ድንገተኛ ህመም ገጠመው

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ዝነኛው አሜሪካዊ ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ የኢትዮጵያን ባህል ለማጣጣም ጥሬ ስጋ በልቶና ወፍራም ቡና ጠጥቶ ወደ ጭፈራው እንደገባ  ድንገተኛ ህመም ገጥሞታል።ይህንንም ከ200ሺ በላይ ሰዎች በቀጥታ ስርጭት ተመልክተዋል።

ያ ሁሉ ጉልበትና ወኔ አንድ ላይ ተደማምሮ ስፒድን አቅም ያሳጣው ሲሆን፣ ለትንሽ ጊዜ ራሱን ሊስት (Faint ሊያደርግ) እንደነበር ተናግሯል።

​ስፒድ ሁኔታውን ሲገልፅ "እንደዚህ አይነት ስሜት ገጥሞኝ አያውቅም፤ ለትንሽ ፌንት በልቼ ነበር!" በማለት የኢትዮጵያ ምግብና ሙዚቃ ጉልበት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መስክሯል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁20😨42👌1