📌አርቲስት ገነት ንጋቱ በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ዙሪያ ያሰራጨችውን ቪዲዮ አነሳች፤ የ"Unsubscribe" ዘመቻም ገጥሟታል
አርቲስት ገነት ንጋቱ የሙያ ባልደረባዋ የሆነውን የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህን ህልፈት ተከትሎ በዩቲዩብ ቻናሏ ላይ አሰራጭታው የነበረውን ቪዲዮ ከገጿ ላይ ማንሳቷ ታወቀ።
አርቲስቷ ቪዲዮውን ለማንሳት የተገደደችው፣ ቪዲዮው የሟቹን ክብር የማይመጥንና ቤተሰቦቹን የሚጎዳ ነው በሚል ከህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ ከበረታባት በኋላ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በሀዘን ወቅት እንዲህ ያሉ መረጃዎችን ለዕይታ ማግኛ (Views) መጠቀም ተገቢ አይደለም በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሰፊ ቁጣ ተቀስቅሷል።
ከቪዲዮው መነሳት ባሻገር፣ ድርጊቱ ያስቆጣቸው በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በአርቲስት ገነት ንጋቱ የዩቲዩብ ቻናል ላይ "Unsubscribe" የማድረግ ዘመቻ መጀመራቸው ታይቷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

👍26❤2
📌አርቲስት ገነት ንጋቱ በይፋ ይቅርታ ጠየቀች
"በትላንትናው እለት በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን ገልጬ ዜና መሰራቴ ይታወቃል::በዚህ ቪዲዮ ላይ ከወዳጄና ጏደኛዬ ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ጋር ያደረጉትን የስልክ ልውውጥ አካትቼለሁ::የእሱን ሃሳብ ጨምሮ ማካተቴ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ቅር አሰኝቷል::
"ቅሬታውም ተገቢ ነው ብዬ ስላመንኩ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ና አድናቂዎቼን ይቅርታ ለመጠየቅ እወዳለሁ:: በድጋሚ እጅግ የምወደው ወንድሜ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ እልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቹ ለወዳጆቹ ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ::ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑሩልን "

👎28❤9👍9🖕2
ቺባን ፕሮፐርቲስ አልፋ ሬዚደንስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል
ቺባን ፕሮፐርቲስ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃ ያለው "አልፋ ሬዚደንስ" የተሰኘ ቅንጡ አፓርትመንት አስተዋወቀ
በሀገራችን የግንባታ ዘርፍ ለ17 ዓመታት ስኬታማ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ቺባን ፕሮፐርቲስ፣ "ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" የተሰኘ የባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃና አገልግሎት የሚሰጥ ቅንጡ (Luxury) አፓርትመንት ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።
ይህ አዲስ አፓርትመንት በሀገሪቱ የሪል ስቴት ልማት ዘርፍ አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ታቅዶ የተገነባ ነው።
ለስምንት ዓመታት ያህል የገበያ ጥናትና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ አሁን ላይ የግንባታው ሂደት ለነዋሪዎች ምቹ ወደሆነ ደረጃ መድረሱ ተገልጿል።
"ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" ነዋሪዎች የቅንጡ ሆቴል አገልግሎትን በቤታቸው እንዲያገኙ በሚያስችል መልኩ የተደራጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን አገልግሎቶች አካቷል፦
ዘመናዊ መገልገያዎች፦ ሰፊ የሆቴል ሎቢ፣ ሬስቶራንት፣ ካፌ፣ የጂም ማዕከል እና በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነ ትልቅ "ኢንፊኒቲ ፑል" (Infinity Pool) በህንጻው አናት ላይ ተገንብቶለታል።
የቤት አማራጮች፦ ከስቱዲዮ እስከ ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በህንጻው አናት ላይ ባለ ሁለት ወለል ግዙፍና ቅንጡ ፔንት ሀውሶችን (Pent-houses) ይዟል።
ጥራትና ደህንነት፦ የቤቶቹ የውስጥ ዲዛይን (Interior) በአውሮፓ ስታንዳርድ በተመረቱ ቁሳቁሶች የተሟላ ነው። በተለይም ከወለል እስከ ኮርኒስ የሚደርሱት መስኮቶች ድምጽና ሙቀት የማይሰርጉ በመሆናቸው ለነዋሪዎች ሰላማዊ ድባብ ይፈጥራሉ።

❤8🤣1
📌"ትስስር " የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ
ስድስት እውቅ ሠዓሊያን ሥራዎቻቸውን በአንድነት ያቀረቡበት "ትስስር" የተሰኘ የሥዕል አውደ-ርዕይ፤ ሐሙስ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።
ይህ ለዐይን ማራኪ የሆኑ ሥራዎች የቀረቡበት አውደ-ርዕይ፤ በመካሄድ ላይ የሚገኘው በአዲስ አበባው እምብርት አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ ውስጥ በሚገኘው አርት ጋለሪ ነው።
በዚህ "ትስስር" በተሰኘው አውርደርዕይ ውስጥ የተሳተፉ ባለሙያዎች የየራሳቸው የሆነ ለየት ያለ የአሳሳል ዘይቤ እና ፍልስፍና ያላቸው ሲሆኑ፣ እነርሱም፦አገኘሁ አዳነ፣ልዕልሰገድ ረታ፣ኡስማን ሀሰን፣ስዩም አያሌው፣ታምራት ሱልጣን እናያሬድ ኦለቪሊያ ናቸው።
አውደ-ርዕዩ እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለተከታታይ አንድ ወር ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል።

❤6👍4
📌የጆኒ ራጋ ጀማው ኮንሰርት ተሰርዟል
የድምጻዊ ጆኒ ራጋ "ጀማው" ኮንሰርት በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት እንደተሰርዘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የተሰረዘው ኮንሰርትም የፊታችን አርብ ጥር 15 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ጆኒ ራጋ ስለጉዳዩ ተከታዩን ብሏል"እስካሁን ትኬት ቆርጣችሁ በመጠበቅ ላይ ያላችሁትን ሁሉ በታላቅ ትህትና ይቅርታ እየጠየቅን በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ጀማው ኮንሰርትን ለመጪው አርብ ጥር 15 ማዘውራችንን ለሁሉም ጀማ እንድታደርሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን"

👏16❤3👍2
📌 "ካሜራ አንፈልግም " የነፃነት ወርቅነህ ቤተሰብ
"ቀረፃም ሆነ የላይቭ ስርጭት ማድረግ የተከለከለ ነው"
ተከታዩ መልዕክት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣የስራ ባልደረቦች፣ የቅርብ እና የሩቅ ዘመዶች ያገኘው መልዕክት ነው።
"በምንወደው ወንድማችን አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የቀብር ሥነሥርዓት ላይ ዩቱበሮች፣ ቲክቶከሮች፣ እንዲሁም በተለያዩ ሚዲያዎች ምንም ዓይነት ቀረፃም ሆነ የላይቭ ስርጭት ማድረግ የተከለከለ ነው" ሲሉ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም "አሁን ልባችን ተሰብሯል የምንፈልገው ሀዘናችንን መወጣት ነው። የእናንተን ካሜራ ግርግር ዛሬን አንፈልግም እባካችሁ እንደ ባህላችን እንደ ወጋችን ሀዘናችንን በሚገባ እንወጣው። ነፃነታችንን አትጋፉ! በጣም ደክሞናል"ብለዋል።

👍53❤16👏10👎2🙏1
📌አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ትራምፕን አስጠነቀቀ
ታዋቂው የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ፣ በአባይ ወንዝ እና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን የኢትዮጵያን ጽኑ አቋም የሚገልጽና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዳዩን እውነታ እንዲረዱ የሚያሳስብ ግልጽ ደብዳቤ አሰራጨ።
ቴዎድሮስ "ፕሬዝዳንት እውነታውን ይረዳ ዘንድ ሼር አድርጉት" በሚል መሪ ቃል ባቀረበው በዚህ በእንግሊዘኛ በቀረበ ደብዳቤ...ተጨማሪውን ያንብቡ:https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/42

🤣90😁19👍11❤5👏4👎2🥰1🤡1
📌የነፃነት ወርቅነህ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነት የቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በድንገት ላጣነው አርቲስት ነፃነት ወርቅነት ሽኝት ከለቀስተኞች ከ2000 በላይ የአበባ ጉንጉን መቅረቡን የኢቢኤሱ ተወዳጁ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነት የቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በድንገት ላጣነው አርቲስት ነፃነት ወርቅነት ሽኝት ከለቀስተኞች ከ2000 በላይ የአበባ ጉንጉን መቅረቡን የኢቢኤሱ ተወዳጁ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
💔26😭7❤2🕊1
አልጄሪያዊያን አይሾው ስፒድን ደብድበው አባረዋል
አሜሪካዊው ዩቲዩበር ስፒድ ወደ አልጄሪያ አምርቶ ያልጠበቀው ነገር ገጥሞታል።
ስፒድ በአልጄሪያ ጨዋታ ለመመልከት ስታዲየም የገባ ቢሆንም ደጋፊዎች በቁሳቁስ.. ተጨማሪውን ያንብቡ:https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/44

😁36❤6💔4👏2
📌በኮዬ ፈጬ የከተራ በዓልን ሲያስተባበሩ የነበሩ 4 ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ
በሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የፋንታ መድኃኔዓለም ደብር የጥምቀት ከተራ በዓልን ሲያከብሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ አራት ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
ወጣቶቹ በበዓሉ ላይ እያገለገሉ እያለ ባጋጠመ የኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህንኑ መርዶ ተከትሎ፣ ለሐዋርያዊ አገልግሎት በጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ አመራሮች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
ሀገረ ስብከቱ ባስተላለፈው የሐዘን መግለጫ "ወጣት ልጆቻችን በበዓል ዕለት ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታላቅ ሐዘን ፈጥሮብናል" ሲሉ ገልጸዋል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ፣ ለወጣቶቹም ነፍስ ዕረፍትን እንዲሰጥ ጸሎት አድርገዋል።
በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ ሲሆን፣ ክስተቱ በምዕመናንና በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤንና ሐዘንን ፈጥሯል።

😢28❤4😭2
📌"ሞትን እንደ ገቢ፣ ሐዘንን እንደ ካሜራ ማሞቂያ"
የመቅደስ ደበሳይ አነጋጋሪ ጽሑፍ
ታዋቂዋ የፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ደበይሳ፣ በወቅታዊ የሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያላትን ትዝብት በማካፈል የአባይ ቴሌቪዥንን አርአያነት ያለው ተግባር አደነቀች።
ጋዜጠኛዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባስተላለፈችው መልእክት፣ በዘመናችን "ሞትን እንደ ገቢ፣ ሐዘንን እንደ ካሜራ ማሞቂያ እንዲሁም የሞት ስርጭትን እንደ ብቸኛ ገቢ" የሚቆጥሩ አካላት መበራከታቸውን በምሬት ገልጻለች።
ይህ ንግግሯ በበርካታ የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቶ እየተጋራ ይገኛል።
መቅደስ ደበይሳ ይህን አስተያየት የሰጠችው፣ አባይ ቴሌቪዥን ሕይወቱ ላለፈው ድንቅ የጥበብ ሰው ነፃነት ወርቅነህ የሰጠውን ክብር ተከትሎ ነው።
ጣቢያው በታዋቂው አርቲስት ህልፈት ምክንያት "በእሁድ የዝግጅት ክፍለ ጊዜያችን ምንም ዓይነት የደስታ ፕሮግራም አይተላለፍም" ሲል መወሰኑን ለፕሮግራም አቅራቢዋ በስልክ ማሳወቁን ጽፋለች።
ይህ የጣቢያው ውሳኔ ከገንዘብ ትርፍ ይልቅ ለሰው ልጅ ክብርና ለጥበብ ሰው የታየ ሙያዊ ስነ-ምግባር መሆኑን መቅደስ ገልጻለች።

👏25❤11👍1👎1
📌ሁለገቡ የጥበብ ሰው ተፈሪ አለሙ ነገ ይከበራል
ለሁለገቡ የጥበብና የሚዲያ ሰው ተፈሪ አለሙ የክብርና የዕውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል።
በብሬማን ፊልም ፕሮዳክሽን እና በፋና ፕላስ ቲቪ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ልዩ የክብር ዝግጅት፤ ነገ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ በፋና ቴሌቪዥን ይተላለፋል።
በዝግጅቱም ላይ ለታላቁ ተዋናይ የክብር ካባ የሚደረብለት ሲሆን፣ እስካሁን በዘርፉ ለሰጣቸው ስራዎችም ተገቢው ምስጋናና ክብር ይቀርብለታል።
አንጋፋው ተዋናይ ተፈሪ አለሙ በበርካታ ፊልሞችና ድራማዎች ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃት በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ የሚወደድና የሚከበር የጥበብ ሰው መሆኑ ይታወቃል።

🔥19❤14👍5👏2
📌የይሁኔ "ዘ-ገሊላ" ሙዚቃ 22 ዓመት ሞላው
ጥር በባተ ከአስረኛው ቀን ጀምሮ ይሁኔ በላይ ያቀነቀነው ዘመን አይሽሬው የ“ዘገሊላ” ሙዚቃ ተደጋግሞ ይደመጣል።
የጥምቀት አከባበርን በሙዚቃው ከባህልና ትውፊቱ ጋር አቆራኝተው አቤል መልካሙ ግጥሙን፣ አስቻለው አየለ ዜማውን፣ ዳዊት ጥላሁን ደግሞ ቅንብሩን ሰርተውታል።
ሙዚቃው ከሃይማኖታዊው አከባበር ፈንጠር ብሎ የሚታየውን ባህላዊ ትርዒት በደንብ የሚያሳይ ነው። የጥምቀት በዓል ሰበብ ሆኗቸው ለተጫጩም ሙዚቃው ድንቅ መዘክር ሆኗል።
የበርካቶቻችን ትዝታ የሆነውና የጥምቀት ሰሞን የቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያዎች የሚቀባበሉት የድምጻዊ ይሁኔ በላይ "ዘ-ገሊላ" ሙዚቃ እድሜን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሲያጣራ ለካ ዘንድሮ ድፍን 22 ዓመት ሞልቶታል።
"ወርዉሬ መታሁት ጥላሽን በእምቧይ፣
ደሞ ባንች በኔ ከልካይ አለን ወይ።
ወደ አንች ስመጣ ተመለስ የሚለኝ፣
ማን ይሆን ወገኛዉ የሚከለክለኝ።
***
ወንዞ አይፈሬዉ ቀሚስ የተሸነሸነዉ፣
ትፍትፉ መቀነት ወገቧን የዞረዉ፣
ልቤን በጉንፏ አዉሎ አሳደረዉ።
***
እንኳን ዛጎል ማርዳዉ አምባሩም መስቀሉ፣
ሽርብት አደሬ ማተብሽ ድንግሉ፣
አንችን ለማሳመር መች አነሰ ባሉ።"

❤36👏2🔥1🎉1
📌"በኢትዮጵያ 309 ፍቃድ ያላቸው ሚዲያዎች አሉ"
በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህጋዊ መንገድ ፈቃድና ምዝገባ አግኝተዉ የሚንቀሳቀሱ የብሮድካስት፣ የበይነ መረብ፣ የህትመት እና የዉጭ መገናኛ ብዙኃን ቁጥር 309 እንደደረሰ ተነገረ።
በዚህም መሰረት 175 የብሮድካስት፣ 20 የህትመት፣ 35 የዉጭ ሚዲያ ክሮስፖንዳንት፣ 73 የበይነመረብ፣ አምስት የክፍያ ኢንተርኔት ብሮድካስት፣ አንድ ነፃ የኢንተርኔት ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በባለሥልጣኑ ምዝገባ እና ፈቃድ አግኝተዉ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ኖር ሬድዮ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 254ቱ በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 55ቱ ደግሞ በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል።
በባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራትም ለ39 የመገናኛ ብዙኃን በፍቃድና ክትትል ዘርፍ የፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገልግሎት እንደተሰጠም ሰምተናል።

❤7
📌ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተሸጠ
ከአዲስአበባ ቀደምት ዘመናዊ ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነው ዋቢ ሸበሌ በዛሬው ዕለት ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተሽጧል።
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።
አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትዉልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ ለተሳታፊዎች ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ መሆኑን ሚድሮክ ኢትዮጵያ አስታውቋል ።
ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በ1960 ዓም ስራ መጀመሩ ይታወሳል። ሆቴሉ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ላለፈው የልዑል መኮንን ልጆች የገቢምንጭ እንዲሆን ንጉስ ሃይለስላሴ ማስገንባታቸው ይነገራል ።
ሆቴሉን ደርግ ከወረሰው በኋላ በዘመነ ኢህአዴግ ለእነ ልዑል በዕደማርያም መኮንን መመለሱ ይታወሳል ።
©️ስዩም ፍቃዱ ( ሁሉ አዲስ)

❤21🤔6👍4🔥2👎1
📌ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ማስታወቂያ አውጥቷል
ሚዲያው ሪፖርተር ይፈልጋል!
የኢትዮጵያ ኢንሳይደር አሳታሚ የሆነው ሀቅ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን፤ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
በዚህም ተፈላጊ የሥራ መስኮች ፦
1. ሪፖርተር (አዲስ አበባ)
- በጋዜጠኝነት ወይም በተመሳሳይ የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ እና 1 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት።
- አማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መናገር የሚችል/የምትችል።
2. ሪፖርተር (ባህር ዳር)

- ባህር ዳር ከተማ የሚኖር/የምትኖር።
3. ሪፖርተር (ድሬዳዋ ወይም ሀረር)
- በጋዜጠኝነት ወይም በተመሳሳይ የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ እና 1 ዓመት የስራ ያለው/ላት።
- ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የአካባቢው ቋንቋዎችን መናገር መቻል ተመራጭነት አለው።
4. ኦዲዮ ቪዥዋል ኤዲተር
በኢንፎግራፊክስ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና የወሰደ/ች እና ቢያንስ የ1 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት።
በምርጫ ዘገባዎች ላይ ቀደምት ልምድ ያላቸው አመልካቾች በከፍተኛ ሁኔታ ይበረታታሉ።
አመልካቾች የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን (CV) በ recruitment@ethiopiainsider.com ኢሜይል አድራሻ መላክ ይጠበቅባችኋል።

❤8
📌ታዋቂዋ የውበት ባለሙያ ትርሀስ (ቴሪ) አረፈች
በኢትዮጵያ የውበትና የፀጉር ስታይል ዘርፍ ስሟ በጉልህ የሚነሳውና በቅርብ ወዳጆቿ "ቴሪ" በሚል ቅጽል ስም የምትታወቀው የውበት ባለሙያ ትርሀስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰማ።
ባለሙያዋ በአዲስ አበባ ደንበል ሲቲ ሴንተር "ሞሮኮ ባዝ" (Morocco Bath) የተሰኘውን ዘመናዊ የውበት መጠበቂያ ማዕከል በመክፈትና ዘመናዊ የፀጉር አሰራርና የሜካፕ ጥበብን በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት ባለሙያዎች መካከል አንዷ ነበረች።

💔14😢3❤2🕊1
📌የኢትዮጵያ ሰርክስ ቡድን በፈረንሳይ ድል ቀናው
በየኔነህ ተስፋዬ ማናጀርነት እና በአሰልጣኝ ክብሮም ወልደሳሙኤል የሚመራው "ትሩፕ ኮልፌ" (የቢጣ ሰርከስ ቡድን) በፈረንሳይ በተካሄደው 48ኛው የሞንቴ ካርሎ ዓለም አቀፍ የሰርከስ ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ እንደሆነ ኖር ሬድዮ ዘግቧል።
የዓለማችን ታዋቂ የሰርከስ አርቲስቶች የሚሳተፉበት ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ክብረ በዓል ላይ ቡድኑ ያስመዘገበው ድል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ትልቅ ኩራት ሆኗል።በዚህ ፌስቲቫል ላይ ትሩፕ ኮልፌ ያገኘው የብር ሜዳሊያ፣ የኢትዮጵያን የሰርከስ ጥበብ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ያደረገ ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

❤22❤🔥2🥰1👏1
📌የራሱን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያከናወነው ብራዚላዊ
በብራዚል ኩሪቲባ ከተማ የሚኖር አንድ ግለሰብ የጓደኞቹንና የዘመዶቹን ታማኝነት ለመፈተን ሲል የራሱን የሐሰት ሞት አውጆ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ማከናወኑ መነጋገሪያ ሆኗል።
ባልታዛር ሌሞስ የተባለው የ60 ዓመት ግለሰብ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ለሕክምና ሆስፒታል መግባቱን የሚገልጽ ፎቶግራፍ ከለጠፈ ከጥቂት ቀናት በኋላ "ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" የሚል የሐሰት ዜና አሰራጨ ...ተጨማሪውን ያንብቡhttps://news.1rj.ru/str/NorRadio1

😁11❤4👍1🖕1
📌 የ10 ሚሊዮን ብር ቼክ ለጥሎሽ ተሰጠ
(አነጋጋሪው የጥሎሽ ሥነሥርዓት )
ከሰሞኑ የተከናወነ አንድ የጥሎሽ ሥነ-ሥርዓት በቅንጦቱና በስጦታዎቹ ውድነት የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ መነጋገሪያ ሆኗል።
ሙሽራው አቤል ለሙሽሪት የአብስራ ሀብታሙ ያበረከቷቸው ስጦታዎች የሀብትና የፍቅር መገለጫ ተደርገው ተወስደዋል።
ለሙሽሪት ከተበረከቱት ስጦታዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ያጌጠ እና ሙሉ የቤትና የግል መገልገያዎችን የያዘ ተሽከርካሪ፣ የዓለም አቀፍ ብራንድ ልብሶችና ሽቶዎች የሞሉባቸው ዘመናዊ ሻንጣዎች እንዲሁም ውድ የወርቅ ጌጣጌጦች ይገኙበታል።
ይሁን እንጂ የዕለቱ ትልቁ መነጋገሪያ የሆነው ሙሽራው ለሙሽሪት የሰጣት የ10 ሚሊዮን ...ተጨማሪውን ያንብቡ https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/49

😁18❤16💩5😱2🥴2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌የቀጥታ ስርጭት ዘገባውን በወፍ ታጅቦ ያከናወነው የፋና ሪፖርተር
የፋና ቴሌቪዥን ሪፖርተር ምራዑል ከድር የቀጥታ ስርጭት ዘገባ በማቅረብ ላይ እያለ፣ አንዲት ወፍ ትከሻው ላይ አርፋ ዘገባውን አብራው ማጠናቀቋን ኖር ሬድዮ ዘግቧል።
ሪፖርተሩ ለተመልካቾች መረጃ ለማድረስ ሙሉ ትኩረቱን ካሜራው ላይ አድርጎ ባለበት ቅጽበት፣ ወፏ ትከሻው ላይ አርፋ ለደቂቃዎች ቆይታለች።
ምራዑል ይህንን ልዩ አጋጣሚ ሲገልጽ "ቀጥታ ዘገባዬ አልተቋረጠም፣ ድምፄም አላስደነገጣትም፤ አእምሮዬ ከወፏ ጋር እያወራ አንደበቴ ግን መረጃ ማድረሱን ቀጥሏል" ብሏል።
"ሰው ጋር መግባባት በከበደበት በዚህ ጊዜ ከወፍ ጋር ተግባብቼ የቀጥታ ዘገባዬን ጨረስኩ" በማለትም በሙያው ያጋጠመውን ይህን ብርቅዬ ክስተት በደስታ ገልጾታል።
ዘገባው የኖር ሬድዮ ነው
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1

❤33😁6👍4🔥3🕊3🗿3