📌ለኢትዮጵያ ፍልስፍና አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ችግሮች ለመፍታት ውይይትና አመክንዮ ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።
ማህበረሰቡ ፍልስፍና ላይ ያለውን አረዳድና የዘርፉን ፋይዳ በሚመለከት የፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ፋሲል መራዊ ከአራዳ ኤፍ.ኤም ጋር በነበራችው ቆይታ እንዳሉት ፥ ከዚህ ቀደም ፍልስፍና ከሃይማኖትና እሴት ጋር የሚቃረን አድርጎ የማሰብ የተሳሳተ አረዳድ መኖሩን ጠቅሰዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ ፍልስፍናዊ ሃሳቦችን ማስተናገድ የሚችል ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
ፍልስፍና ሚና ያለው መሆኑንና ወጣ ካሉ ሃሳቦች ባሻገር የነገ መንገዱን በራሱ ልክ መስፋት የሚችል ጠያቂ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚያግዝም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ሌላኛው የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ይህንን ሃሳብ አጠናክረዋል።
በኢትዮጵያ ፍልስፍና እየዳበረ መምጣቱን የገለፁት ምሁራኑ፥ አንድ ሕዝብ መለወጥ እና መዘመን እንዲችል ሃሳብ መሰረታዊ መሆኑን ብሎም ሃሳብ በሂደት ሲያረጅ ደግሞ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን ማንሳትና የክርክር ባህልን ማዳበር አስፈላጊ ስለመሆኑም ነው ያብራሩት።
©️ዘገባው የአራዳ ኤፍ አም ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

❤13👎2😁2
📌አዲስ ማለዳ ለጋዜጠኞች ማስታወቂያ አውጥቷል
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
1. የሥራ መደብ፡- ሪፖርተር
የትምህርት ደረጃ፡- በጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦት እንዲሁም በተዛማጅ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ት
ልምድ፡- ቢያንስ ከአንድ ዓመት በላይ የሰራ/ች፣ በህትመትና ዲጂታል ሚዲያ ላይ የሰራ/ች ቢሆን ይመረጣል
ብዛት፡- 2
ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት
2. የሥራ መደብ፡- አርታኢ
የትምህርት ደረጃ፡- በጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦት እንዲሁም በተዛማጅ የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ት፡፡ በሌላ ትምህርት መስክ የተማሩ ቢሆንም በሥራ ላይ የቆዩ ከሆነ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ልምድ፡- አራት ዓመትና ከዚያ በላይ፣ በህትመትና በዲጂታል ሚዲያ ላይ የሰራ/ች
ብዛት፡- 1
ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ሆምስ (ከቦሌ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ላይ ከአርጀንቲና ኤምባሲ ጀርባ)
ኢሜይል፡- addismaleda@gmail.com
ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ ባሉት ተከታታይ አምስት የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎን ያስገቡ!

❤5
📌ሴት የሬዲዮ ፕሮግራም አቅራቢ ማስታወቂያ
ዳጉ ኮምኒኬሽን ሴት የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ይፈልጋል::
የትምህርት ዝግጅትና ልምድ ያላችሁ በቴሌግራም ሊንክ @Manaye7450 ላይ ሲቪ መላክ ትችላላችሁ ::
ሔሎኢትዮጵያ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1

❤6
📌አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም እንደተለየ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስታውቋል።
ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር።

😭94😢17😱9❤2🤯2
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የህይወት ታሪክ
አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በተለይም በኮሜዲ ትወና እና በቴሌቭዥን አቀራረብ ዘርፍ እጅግ ተወዳጅ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዱ ነበር። የእርሱ ድንገተኛ ህልፈት እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና ነው።
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የህይወት ታሪክ
እዚህ አዲስ አበባ ፒያሳ አከባቢ በ1975 አመተ ምህርት ተወልዶ ያደገው ነጻነት ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ የህይወት ጥሪውን ለይቶ በማወቅ ለሚወደው የትያትር እና ጥበብ ራሱን የሰጠ እና በዚህም ለከፍተኛ ደረጃ የደረሰ አርቲስት ነበር፡፡
ተዋናይ፣ ኮሜዲያን፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በኢትዮጵያ የፊልም እና የቴሌቭዥን ታሪክ ውስጥ የራሱን ልዩ የሆነ የአቀራረብ ስልት እና የትወና ጥበብ በማሳየት የሚታወቅ ባለሙያ ነበር።
ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ.... ተጨማሪውን ያንብቡ https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/38

😭7❤4
📌 ነጻነት ወርቅነህ ዛሬ ጠዋት
ነጻነት ዛሬ ጠዋት ወደ ስራ ሊሄድ እየለባበሰ ነበረ። ህመም ሲሰማው ጓደኛውን ጠርቶት ወደ ICMC ሆስፒታል ሄዱ። መንገድ ላይ እያለም ህመሙ እየባሰበት ነበረ። ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ምሳ ሰዓት ገደማ አረፈ። ፖሊሶች በሆስፒታሉ ተገኝተው ሙያዊ የምርመራ ስራቸውን አከናውነዋል።
አሌልቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅበሩኝ
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በሕይወት እያለ ሲሞት አሌልቱ ጊዮርጊስ ከአያቱ አጠገብ ቀብሩ እንዲፈጸም እንደሚፈልግ ለወዳጆቹ ደጋግሞ ይናገር የነበረ ሲሆን ያለፈው ሳምንትም አሌልቱ ጊዮርጊስ በመሄድ ቤተክርስቲያኒቱን የማሳደስ ስራ ስለማከናወን ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግሮ መመለሱ ተሰምቷል።
ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው ባለቤቱ እና የልጆቹ እናት እሁድ ጠዋት ከአሜሪካ አዲስ አበባ የምትገባ ሲሆን በዚያው ሰዓት ስርዓተ ቀብሩ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
©️ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

😢31❤15💔2
በሀዘን ምክንያት አልበሙ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል
የልጅ ተመስገን መለሰ "ኢቲዲኤም ቢትስ" የሙዚቃ አልበም ዛሬ ጥር 8 ከምሽቱ 12:00 ላይ እንደሚለቀቅ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ድንገተኛ ሀዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ አስታውቀዋል።
አዘጋጆቹ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል"በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ጥልቅ ሀዘን ስለተሰማን ዛሬ ማታ ጥር 8 ሊለቀቅ የነበረው የETDM Beats የልጅ ተመስገን መለሰ አልበም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን በትህትና እናሳውቃለን። ለቤተሰቡ እና ለመላው አድናቂዎቹ መፀናናትን እንመኛለን"።

❤19👍2
📌አርቲስት ገነት ንጋቱ ከፍተኛ ትችት ቀረበባት
ታዋቂዋ አርቲስት ገነት ንጋቱ፣ የሞያ ባልደረባዋ የሆነውን የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህን ህልፈት ተከትሎ በዩቲዩብ ቻናሏ ባሰራጨችው ዘገባ ምክንያት ከህዝብ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ እየደረሰባት ይገኛል።
አርቲስት ገነት ንጋቱ በዩቲዩብ ቻናሏ፣ የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህን ህልፈት አስመልክቶ ቪዲዮ ለቃለች።
በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚገኙ ተከታታዮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የሚከተሉትን ትችቶች ሰንዝረዋል፦
በቪዲዮው ላይ የምታሳየው እጅግ የበረታ ለቅሶና ድርጊት "ለካሜራ ተብሎ የተሰራ (Acting)" እንጂ እውነተኛ ሀዘን አይመስልም የሚሉ አስተያየቶች በስፋት ተሰንዝረዋል።
የሞያ ስነ-ምግባር ጉድለት: "በጓደኛ ሞት ትርፍ ለማግኘት መሞከር ነውረኝነት ነው" በሚል ብዙዎች ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
የዩቲዩብ ገቢ (Monetization): በሀዘን ሰዓት ማስታወቂያዎችን የያዙ ረጅም ቪዲዮዎችን መልቀቋ፣ ጉዳዩን ከሰው ልጅ ስሜት ይልቅ ወደ ንግድ የቀየረችው አስመስሎባታል።
የክብር መሸርሸር: አርቲስቷ ቀደም ሲል የነበራትን ክብርና ዝና በዚህ ድርጊቷ እየቀነሰችው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች አስገንዝበዋል።
አርቲስት ገነት ንጋቱ ለቀረቡባት ትችቶች እስካሁን የሰጠችው ዝርዝር ምላሽ ባይኖርም፣ ይህ ክስተት በኢትዮጵያ የዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪዎች መካከል "የእይታ ብዛት (Views) ወይስ የሞያ ስነ-ምግባር?" የሚለውን ክርክር ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጎታል።
©️Fast mereja

❤13👍3
📌ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ ምላሽ ሰጠ
"እኔ መቀረፄን አላውቅም።ሲበዛ ሆዳምነት እና ከተማረ ሰው የማይጠበቅ ነው"
አርቲስት ገነት ንጋቱ፣ የሞያ ባልደረባዋ የሆነውን የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህን ህልፈት ተከትሎ በዩቲዩብ ቻናሏ ባሰራጨችው ዘገባ ምክንያት ከህዝብ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ እየደረሰባት ይገኛል።
አርቲስት ገነት ንጋቱ በዩቲዩብ ቻናሏ፣ የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህን ህልፈት አስመልክቶ ቪዲዮ ለቃለች።
እዚህ ቪዲዮ ላይ ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌን በስልክ ስታነጋገረው ታይታለች።
ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ ስለ ተፈጠረው ነገር ተከታዩን ብሏል "እኔ መቀረፄን አላውቅም።እንደ ቀደመ ወዳጅነታችን ሀዘኗን ልትገልፅ መስሎኝ ሆስፒታል ሆኜ ነው በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ያዋራሁዋት ሲበዛ ብልግናና ሆዳምነት ነው።ከተማረ የማይጠበቅ " ሲል ተናግሯል።

❤12🤔1
📌አርቲስት ገነት ንጋቱ በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ዙሪያ ያሰራጨችውን ቪዲዮ አነሳች፤ የ"Unsubscribe" ዘመቻም ገጥሟታል
አርቲስት ገነት ንጋቱ የሙያ ባልደረባዋ የሆነውን የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህን ህልፈት ተከትሎ በዩቲዩብ ቻናሏ ላይ አሰራጭታው የነበረውን ቪዲዮ ከገጿ ላይ ማንሳቷ ታወቀ።
አርቲስቷ ቪዲዮውን ለማንሳት የተገደደችው፣ ቪዲዮው የሟቹን ክብር የማይመጥንና ቤተሰቦቹን የሚጎዳ ነው በሚል ከህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ ከበረታባት በኋላ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በሀዘን ወቅት እንዲህ ያሉ መረጃዎችን ለዕይታ ማግኛ (Views) መጠቀም ተገቢ አይደለም በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሰፊ ቁጣ ተቀስቅሷል።
ከቪዲዮው መነሳት ባሻገር፣ ድርጊቱ ያስቆጣቸው በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በአርቲስት ገነት ንጋቱ የዩቲዩብ ቻናል ላይ "Unsubscribe" የማድረግ ዘመቻ መጀመራቸው ታይቷል።

👍26❤2
📌አርቲስት ገነት ንጋቱ በይፋ ይቅርታ ጠየቀች
"በትላንትናው እለት በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን ገልጬ ዜና መሰራቴ ይታወቃል::በዚህ ቪዲዮ ላይ ከወዳጄና ጏደኛዬ ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ጋር ያደረጉትን የስልክ ልውውጥ አካትቼለሁ::የእሱን ሃሳብ ጨምሮ ማካተቴ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ቅር አሰኝቷል::
"ቅሬታውም ተገቢ ነው ብዬ ስላመንኩ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ና አድናቂዎቼን ይቅርታ ለመጠየቅ እወዳለሁ:: በድጋሚ እጅግ የምወደው ወንድሜ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ እልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቹ ለወዳጆቹ ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ::ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑሩልን "

👎28❤9👍9🖕2
ቺባን ፕሮፐርቲስ አልፋ ሬዚደንስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል
ቺባን ፕሮፐርቲስ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃ ያለው "አልፋ ሬዚደንስ" የተሰኘ ቅንጡ አፓርትመንት አስተዋወቀ
በሀገራችን የግንባታ ዘርፍ ለ17 ዓመታት ስኬታማ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ቺባን ፕሮፐርቲስ፣ "ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" የተሰኘ የባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃና አገልግሎት የሚሰጥ ቅንጡ (Luxury) አፓርትመንት ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።
ይህ አዲስ አፓርትመንት በሀገሪቱ የሪል ስቴት ልማት ዘርፍ አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ታቅዶ የተገነባ ነው።
ለስምንት ዓመታት ያህል የገበያ ጥናትና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ አሁን ላይ የግንባታው ሂደት ለነዋሪዎች ምቹ ወደሆነ ደረጃ መድረሱ ተገልጿል።
"ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" ነዋሪዎች የቅንጡ ሆቴል አገልግሎትን በቤታቸው እንዲያገኙ በሚያስችል መልኩ የተደራጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን አገልግሎቶች አካቷል፦
ዘመናዊ መገልገያዎች፦ ሰፊ የሆቴል ሎቢ፣ ሬስቶራንት፣ ካፌ፣ የጂም ማዕከል እና በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነ ትልቅ "ኢንፊኒቲ ፑል" (Infinity Pool) በህንጻው አናት ላይ ተገንብቶለታል።
የቤት አማራጮች፦ ከስቱዲዮ እስከ ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በህንጻው አናት ላይ ባለ ሁለት ወለል ግዙፍና ቅንጡ ፔንት ሀውሶችን (Pent-houses) ይዟል።
ጥራትና ደህንነት፦ የቤቶቹ የውስጥ ዲዛይን (Interior) በአውሮፓ ስታንዳርድ በተመረቱ ቁሳቁሶች የተሟላ ነው። በተለይም ከወለል እስከ ኮርኒስ የሚደርሱት መስኮቶች ድምጽና ሙቀት የማይሰርጉ በመሆናቸው ለነዋሪዎች ሰላማዊ ድባብ ይፈጥራሉ።

❤8🤣1
📌"ትስስር " የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ
ስድስት እውቅ ሠዓሊያን ሥራዎቻቸውን በአንድነት ያቀረቡበት "ትስስር" የተሰኘ የሥዕል አውደ-ርዕይ፤ ሐሙስ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።
ይህ ለዐይን ማራኪ የሆኑ ሥራዎች የቀረቡበት አውደ-ርዕይ፤ በመካሄድ ላይ የሚገኘው በአዲስ አበባው እምብርት አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ ውስጥ በሚገኘው አርት ጋለሪ ነው።
በዚህ "ትስስር" በተሰኘው አውርደርዕይ ውስጥ የተሳተፉ ባለሙያዎች የየራሳቸው የሆነ ለየት ያለ የአሳሳል ዘይቤ እና ፍልስፍና ያላቸው ሲሆኑ፣ እነርሱም፦አገኘሁ አዳነ፣ልዕልሰገድ ረታ፣ኡስማን ሀሰን፣ስዩም አያሌው፣ታምራት ሱልጣን እናያሬድ ኦለቪሊያ ናቸው።
አውደ-ርዕዩ እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለተከታታይ አንድ ወር ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል።

❤6👍4
📌የጆኒ ራጋ ጀማው ኮንሰርት ተሰርዟል
የድምጻዊ ጆኒ ራጋ "ጀማው" ኮንሰርት በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት እንደተሰርዘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የተሰረዘው ኮንሰርትም የፊታችን አርብ ጥር 15 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ጆኒ ራጋ ስለጉዳዩ ተከታዩን ብሏል"እስካሁን ትኬት ቆርጣችሁ በመጠበቅ ላይ ያላችሁትን ሁሉ በታላቅ ትህትና ይቅርታ እየጠየቅን በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ጀማው ኮንሰርትን ለመጪው አርብ ጥር 15 ማዘውራችንን ለሁሉም ጀማ እንድታደርሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን"

👏16❤3👍2
📌 "ካሜራ አንፈልግም " የነፃነት ወርቅነህ ቤተሰብ
"ቀረፃም ሆነ የላይቭ ስርጭት ማድረግ የተከለከለ ነው"
ተከታዩ መልዕክት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣የስራ ባልደረቦች፣ የቅርብ እና የሩቅ ዘመዶች ያገኘው መልዕክት ነው።
"በምንወደው ወንድማችን አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የቀብር ሥነሥርዓት ላይ ዩቱበሮች፣ ቲክቶከሮች፣ እንዲሁም በተለያዩ ሚዲያዎች ምንም ዓይነት ቀረፃም ሆነ የላይቭ ስርጭት ማድረግ የተከለከለ ነው" ሲሉ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም "አሁን ልባችን ተሰብሯል የምንፈልገው ሀዘናችንን መወጣት ነው። የእናንተን ካሜራ ግርግር ዛሬን አንፈልግም እባካችሁ እንደ ባህላችን እንደ ወጋችን ሀዘናችንን በሚገባ እንወጣው። ነፃነታችንን አትጋፉ! በጣም ደክሞናል"ብለዋል።

👍53❤16👏10👎2🙏1
📌አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ትራምፕን አስጠነቀቀ
ታዋቂው የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ፣ በአባይ ወንዝ እና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን የኢትዮጵያን ጽኑ አቋም የሚገልጽና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዳዩን እውነታ እንዲረዱ የሚያሳስብ ግልጽ ደብዳቤ አሰራጨ።
ቴዎድሮስ "ፕሬዝዳንት እውነታውን ይረዳ ዘንድ ሼር አድርጉት" በሚል መሪ ቃል ባቀረበው በዚህ በእንግሊዘኛ በቀረበ ደብዳቤ...ተጨማሪውን ያንብቡ:https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/42

🤣90😁19👍11❤5👏4👎2🥰1🤡1
📌የነፃነት ወርቅነህ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነት የቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በድንገት ላጣነው አርቲስት ነፃነት ወርቅነት ሽኝት ከለቀስተኞች ከ2000 በላይ የአበባ ጉንጉን መቅረቡን የኢቢኤሱ ተወዳጁ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የአርቲስት ነፃነት ወርቅነት የቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በድንገት ላጣነው አርቲስት ነፃነት ወርቅነት ሽኝት ከለቀስተኞች ከ2000 በላይ የአበባ ጉንጉን መቅረቡን የኢቢኤሱ ተወዳጁ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
💔26😭7❤2🕊1
አልጄሪያዊያን አይሾው ስፒድን ደብድበው አባረዋል
አሜሪካዊው ዩቲዩበር ስፒድ ወደ አልጄሪያ አምርቶ ያልጠበቀው ነገር ገጥሞታል።
ስፒድ በአልጄሪያ ጨዋታ ለመመልከት ስታዲየም የገባ ቢሆንም ደጋፊዎች በቁሳቁስ.. ተጨማሪውን ያንብቡ:https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/44

😁36❤6💔4👏2
📌በኮዬ ፈጬ የከተራ በዓልን ሲያስተባበሩ የነበሩ 4 ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ
በሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የፋንታ መድኃኔዓለም ደብር የጥምቀት ከተራ በዓልን ሲያከብሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ አራት ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
ወጣቶቹ በበዓሉ ላይ እያገለገሉ እያለ ባጋጠመ የኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህንኑ መርዶ ተከትሎ፣ ለሐዋርያዊ አገልግሎት በጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ አመራሮች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
ሀገረ ስብከቱ ባስተላለፈው የሐዘን መግለጫ "ወጣት ልጆቻችን በበዓል ዕለት ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታላቅ ሐዘን ፈጥሮብናል" ሲሉ ገልጸዋል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ፣ ለወጣቶቹም ነፍስ ዕረፍትን እንዲሰጥ ጸሎት አድርገዋል።
በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ ሲሆን፣ ክስተቱ በምዕመናንና በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤንና ሐዘንን ፈጥሯል።

😢28❤4😭2
📌"ሞትን እንደ ገቢ፣ ሐዘንን እንደ ካሜራ ማሞቂያ"
የመቅደስ ደበሳይ አነጋጋሪ ጽሑፍ
ታዋቂዋ የፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ደበይሳ፣ በወቅታዊ የሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያላትን ትዝብት በማካፈል የአባይ ቴሌቪዥንን አርአያነት ያለው ተግባር አደነቀች።
ጋዜጠኛዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባስተላለፈችው መልእክት፣ በዘመናችን "ሞትን እንደ ገቢ፣ ሐዘንን እንደ ካሜራ ማሞቂያ እንዲሁም የሞት ስርጭትን እንደ ብቸኛ ገቢ" የሚቆጥሩ አካላት መበራከታቸውን በምሬት ገልጻለች።
ይህ ንግግሯ በበርካታ የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቶ እየተጋራ ይገኛል።
መቅደስ ደበይሳ ይህን አስተያየት የሰጠችው፣ አባይ ቴሌቪዥን ሕይወቱ ላለፈው ድንቅ የጥበብ ሰው ነፃነት ወርቅነህ የሰጠውን ክብር ተከትሎ ነው።
ጣቢያው በታዋቂው አርቲስት ህልፈት ምክንያት "በእሁድ የዝግጅት ክፍለ ጊዜያችን ምንም ዓይነት የደስታ ፕሮግራም አይተላለፍም" ሲል መወሰኑን ለፕሮግራም አቅራቢዋ በስልክ ማሳወቁን ጽፋለች።
ይህ የጣቢያው ውሳኔ ከገንዘብ ትርፍ ይልቅ ለሰው ልጅ ክብርና ለጥበብ ሰው የታየ ሙያዊ ስነ-ምግባር መሆኑን መቅደስ ገልጻለች።

👏25❤11👍1👎1
📌ሁለገቡ የጥበብ ሰው ተፈሪ አለሙ ነገ ይከበራል
ለሁለገቡ የጥበብና የሚዲያ ሰው ተፈሪ አለሙ የክብርና የዕውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል።
በብሬማን ፊልም ፕሮዳክሽን እና በፋና ፕላስ ቲቪ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ልዩ የክብር ዝግጅት፤ ነገ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ በፋና ቴሌቪዥን ይተላለፋል።
በዝግጅቱም ላይ ለታላቁ ተዋናይ የክብር ካባ የሚደረብለት ሲሆን፣ እስካሁን በዘርፉ ለሰጣቸው ስራዎችም ተገቢው ምስጋናና ክብር ይቀርብለታል።
አንጋፋው ተዋናይ ተፈሪ አለሙ በበርካታ ፊልሞችና ድራማዎች ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃት በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ የሚወደድና የሚከበር የጥበብ ሰው መሆኑ ይታወቃል።

🔥19❤14👍5👏2