FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.56K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

በምዕራብ ሸዋ ዞን እየተንቀሳቀስ በህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የቆየው አሻባሪው የሸኔ ቡድን ተደመሰሰ።

በምዕራብ ሸዋ ዞን እየተንቀሳቀሰ በህዝብ ላይ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሲያደርስ የቆየው አሸባሪው የሸኔ ቡድን በክፍለ ጦሩ የሠራዊት አባላት መመታቱን የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ እንዳለው ገልፀዋል።

ምክትል አዛዡ እንደተናገሩት አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥ በቡድን በመደራጀት ማህበረሰቡን በማገትና በማስፈራራት ገንዘብና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን እየቀማና እያሰቃየ መቆየቱን ገልፀው አሁን የክፈለ ጦሩ አባላት ይህን ሃይል በገባበት እየገቡ ከመቅጣት በዘለለ ከማህበረሰቡ ዘርፎት የነበረውን ንብረት ማሥመለስ መቻላቸውን አሥረድተዋል።

ሻምበል ይመር ዘገዬ በበኩላቸው በጀልዱ ወረዳ ሶስት አጎራባች ቀበሌዎች ማለትም በኡርጋ፣ኤልኬ እና ዳዋ በተባሉ ቀበሌዎች በርካታ የሸኔ አባላትን መምታት መቻሉን ገልፀው 64 የብሬን ጥይት፣ ከ300 መቶ በላይ የክላሽ ጥይት ከማህበረሰቡ የተዘረፈ 19 የቀንድ ከብቶችን እና 21 ፍየሎችና ከህክምና ቁሳቁስ ጋር ማሥመለስ መቻሉን ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍቃዱ ቡዙነህ
ፎቶግራፍ ደረጀ ኤልያስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍122
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

"የቆምነው ለሠንደቅ ዓላማ እና ለኢትዮጵያ ነው" ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

በባሕር ዳር ከተማ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ  ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ጄኔራል መኮንኖች በተገኙበት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የተገኙት የሰሜን ምዕራብ እዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መከላከያውም ሰላም እንዲኖር ይፈልጋል ብለዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት  የሚዋጋው ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሕዝበ ሰላም መሆኑንም ተናግረዋል።  የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ  ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ስለ ሰላም መሥራት እንደሚገባውም ገልፀዋል። እኛ የእናንተ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነንም ብለዋል። 

የኢትዮጵያ ሠራዊት ደግሞ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ተንቀሳቅሶ ለሕዝብ ሰላም ይሠራል ያሉት አዛዡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ ሰላም እና አንድነት ሲባል የሚሞት በመሆኑ ሕዝቡ ለሰላም ሊሠራ ይገባዋልም ብለዋል ።

የራስ ሃሳብን ብቻ የሚያራምድ እና ሌሎችን የማይቀበል አካሄድ ሀገር የሚያፈርስ መኾኑንም ገልጸዋል። ለማንም ሳናዳላ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሕዝብ ሰላም እንሰራለንም ብለዋል። በሰላማዊ መንገድ የመጣውን እንቀበላለን ነው ያሉት። እኛ የሀገር ሉዓላዊነት ጠባቂዎች ነንም ብለዋል።

"የቆምነው ለሠንደቅ ዓላማ እና ለኢትዮጵያ ነው" ያሉት ሌተናል ጄኔራሉ  እውነትን እያወጡ ለሀገር ሰላም መቆም እንደሚገባም አመላክተዋል።  በሰላማዊ መንግድ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ሰከን ብሎ በማሰብ ክልሉን ወደ ሰላም መመለስ ይገባል ያሉት ደግሞ የሰሜን ምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሙሉዓለም አድማሱ ናቸው

ሜጄር ጀኔራል ሙሉዓለም ሰራዊቱ ለአማራ ሕዝብ ታላቅ ክብር አለው ብለዋል። በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ  ሕዝብ ነው ያሉት ሜጀር ጄኔራል ሙሉዓለም በአልተገባ መንገድ ሕዝብ ማወናበድ ሕዝብን ለመከራ እንደሚዳርግ አመላክተዋል።

የሕዝብን መከራ ለማቃለል እውነትን መሠረት በማድረግ መነጋገር ይገባልም ነው ያሉት። ለሀገርና ለሕዝብ መስዋዕት የከፈለን ሠራዊት መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር እንደማይገባም አሳስበዋል።

ጥያቄዎች አሉ ጥያቄዎችን የሚመለከተው አካል ይመልስ ነገር ግን ሀቅ ላይ ተመስርተን ሰላም መፍጠር አለብን ነው ያሉት። አንድነት መፍጠር እና በሀቅ በመሥረት ጥያቄዎችን መፍታት ይገባል ብለዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍176🔥1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

     "የዓለም አካል ናትና ስለ ብሄራዊ ጥቅሟ.."

ከሀገር ተነስቶ ቀጠናን አካሎ አሁናዊ ዓለማዊ እውነታን ያላገናዘበ እይታ ሀገራዊ ህላዌን ለማስጠበቅ ይቸገራል።

የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በውስጥ ብቻ በታጠረ ዙሪያ ገባን በዘነጋ አኳኃን ማስከበር እንደማይቻል ሉላዊዋ ዓለም እያረጋገጠችልን ነው።

በዘመናዊዋ ዓለማችን ዳር ድንበርን በማጠር "አትድረሱብኝ አልደርስባችሁም" በሚል ጨዋነት ከጉዳት መጠበቅ ዘበት ሆኗል። የሀገር ብሄራዊ ጥቅም ያለ ቀጠናዊ ተደጋጋፊነት፣ትብብር ብሎም ሰጥቶ መቀበላዊ ጥምረት ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል።

መርጦ ሰሚ የሆነችው ዓለማችን ስለ ፍትህና ርትዕ ሳይሆን ባፈረጠሙት ከኢኮኖሚ እስከ ወታደራዊ ደንዳና አቅማቸው ዓለምን የሚዘውሩ ሃያላን መልካም ፈቃድ መመራቷ ለክርክር የማይበቃ ሀቅ ነው።

የመካከለኛው ምስራቅ ሰሞነኛው የእስራኤል ፍልስጤም አነጋጋሪ ጦርነት ከብዙ ሃገራት ብሄራዊ ጥቅም ጋር ተሰናስኖ ጉዳዩ አለም-አቀፋዊ መልክ የያዘበትን አመክንዮ በቅጡ ለመረመረ ከጦርነቱ በስተጀርባ አድፋጭ ፍላጎቶች ይገለጡለታል።

የድፍን ዓለም ሚዲያ ካሜራዎች ጋዛ ላይ ተተክለው እንደየ ሀገራቸው ብሄራዊ ፍላጎት ልክ ...ሃራ አራት ሰዓት እያንዳንዷን ጉዳይ ሲተነትኑ፣ተሟጋቾችን በስሜት ሲያከራክሩ፣የሰብዓዊነት ጥያቄዎች ሲዥጎደጎዱ እያየን እየሰማን ነው።

ስለ ሰብዓዊነት ከተነሳ የሱዳን ጉዳይ ስለምን በዚያው ልክ አላነጋገረም?  የሱዳናዊያን ሰቆቃ ስለምን "ጆሮ ተነፈገው?" እስኪያስብል በመከራው ልክ አልተጯጯኸም። ሱዳናዊያንም እራሳቸው በራሳቸው በለኮሱት እሳት ፍዳቸውን እያዩ ዓለም በተገቢው መጠን ጆሮ አልሰጥ ያለችበት ነገር ያስተዛዝባልም ያናድዳልም።

ይህ አሳዛኝ እውነታ "ሱዳን እንደዛ እንድትሆን ይፈለጋልን?" የሚል ጥያቄ ቢያስነሳ ነውር አይሆንም።

በአለፍ ገደም ብልጭ በሚያደርጉት የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ የጉልበታሞቹ ሚዲያዎች ከካርቱም እስከዳርፉር ያለውን ቀውስ "እይዋቸው" ለሚል ስላቃቸው የዜና ማዳመቂያቸው ማድረጋቸው ያብከነክናል።

ተወደደም ተጠላ ዓለም መርጦ ሰሚ የመሆኗን ነገር ለመቀበል የሚያስገደድ ጊዜ ላይ እንገኛለን።

ለአፍሪካ ብሎም ለቀጠናችን ምስራቅ አፍሪካ በተለይ ለአፍሪካ ቀንድ.. "የዓለም ዘዋሪዎቹ ምልከታ እንዴት ነው" ብሎ በቅጡ መረዳት ይገባል።

ሀገራት ከውስጣዊ ጥንካሬያቸው ባሻገር እንደየሚገኙበት ጂኦ-ፓለቲካዊ አቀማመጥ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አኳያ ተፈጥሮ ለቀጠናቸው የሰጠቻቸውን በረከት ለየህዝቦቻቸው ጥቅም ማዋል ከቻሉ የሃብት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትና ጥበብ ባለቤት ሆነዋል ማለት ነው።

ይህ ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎቶቻቸውን እንደ ሀገር፤የጋራ ተስፋና መልካም ጸጋ ፈጣሪ ዕድላቸውን በትብብር ማጽናት የሚያስችላቸው አይደፈሬ ሃይል እንደሚሆናቸውም "ሳይታለም የተፈታ ነው።"

ታዲያ ስለምን የአፍሪካ ቀንድ የማያባራ ግጭቶቻቸው በሚቀፈቅፏቸው የረሃብ፣የስደት፣ የኃላቀርነትና የሌሎች እርጥባን ሻችነት መለያ የተለጠፈባቸው ሀገራት መገኛ እንደሆነ ተደርጎ በዓለም እንዲታሰብ ተደረገ?

የአፍሪካ ቀንድ  ስትራቴጂክ መሆን ከጸጋ በረከትነቱ ይልቅ ለባለቤቶቹ የቀንዱ ሀገራት ከእርግማን የከፋ ዋጋ አስከፋያቸውና የሰላም እጦት መንስዔያቸው እንደሆነስ ለምን ቀጠለ ለምንስ ሊቆም አልቻለም? ከተባለ ምላሹ "ከውጭ ወደ ቀጠናው በጥንቃቄ እየተጠመቁ የሚላኩ የግጭት ሴራዎች አለማቋረጣቸው ነው።

በቀንዱ ሀገራት ውስጥ የማያባራ እና መልኩን እየለዋወጠ ሳያቋርጥ የሚቀጥል የግጭት ጠመቃ እና የቀውስ አዙሪት ዳከራ ዘዋሪዎቹ እጀ-ረጅምና ሃይ ባይ የሌላቸው የዓለማችን ጉልበታሞች መሆናቸው ደግሞ ነገሩን አወሳስቦ ውሉን አጥፍቶታል።

የባለ ፈርጣማ ጡንቻ ባለቤቶቹ ሃያላን ስጋት ምንጩ የቀንዱ ሀገራት ሰላም ሆነው፤የውስጥ ችግሮቻቸውን ፈትተው ቀጠናዊ ህብረት በመፍጠር እንደ ባለቤትነታቸው ፍትሃዊነትን ባሰፈነ የየራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ባስከበረ ጥምረት መቆራኘት ከቻሉ የሚያሳጣቸውን ወሳኝ ጥቅም ማስላታቸው ነው።

ስለሆነም የቀንዱ ሀገራት የአዙሪት ጉዞ ማባሪያ እንዳይኖረው ተግተው ይሰራሉ።

በዚያ ላይ ደግሞ በየሀገራቱ ውስጥም ከገዛ ሀገራቸውና ወገናቸው ጥቅም ይልቅ ለባዕዳን አዳሪ ህሊና ቢስ የጥቅም ተገዢ ጉዳይ አስፈጻሚዎችም አሏቸውና ይህ ለእነሱ "የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ" ሆኖላቸው ተመችቷቸዋል።

ከዚህ አኳያ ከቀንዱ ሀገራት አንዷ የሆነችው የእኛዋ ኢትዮጵያስ?  ይሁንታን የሚቸር ፈቃዳችሁን ከሰጣችሁኝ በሚቀጥለው ጽሁፌ ልመለስ?

በአስቻለው ሌንጫ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍4012🔥2👏1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም እና የፀጥታ ዲፓርትመንት ፋይናንስ ሃላፊ በሚስተር ሰሊጂ ባንጊ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከልን ጎበኘ፡፡

ቡድኑን ጨምሮ የማዕከሉ ከፍተኛ አመራሮች በሱማሊያ ሰላም ማስከበር ያሰማሩ ሀገሮች ለሰራዊቶቻቸው ለሚከፍሏቸው ወርሀዊ እና የካሳ ክፍያ  በሚመለከት እንዲሁም ኦዲትን በተመለከተ ለሁለት ቀናት የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

የመከላከያ ሰላም ማከበር ማዕከል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መነንግስቴ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሠራዊት በማሰማራት ውጤታማ የሰላም ማስከበር ግዳጅ እየተወጣች መሆኗን ገልፀው   የአውሮፓ ህብረት እና የአባል ሀገራቱ የማያቋርጥ  የፋይናንስ ድጋፍ ሰራዊቱ በሶማሊያ የተሰጠውን አስቸጋሪ ግዳጅ  መፈፀም አስችሎታል ብለዋል፡፡

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊቱ ሳይታክት አልሻባብን በማጥፋት በርካታ ተልእኮዎችን በመወጣት ምሳሌ መሆን ችሏል ያሉት አዛዡ ልዑካን ቡድኑ ለሰራዊቱ የሚከፈል የሽልማት ገንዘብ እና የካሳ ክፍያዎችን በወቅቱ ክፍያ ለህብረቱ ፋይናስ በኩል እንዲፈፀም መፍትሄ የሚያሥፈልገው በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ 

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም እና ፀጥታ ዲፓርትመንት ፋይናስ ሀላፊ ሚስተር ሰሊጂ ባንጊ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ አሚሶም አትሚስ ተልዕኮ ሰላምን በማረጋጋት ለከፈሉት መስዋዕትነት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአሚሶም/ አትሚስ ለተሰማሩ የሰላም አስከባሪ አባላት አስፈላጊውን ዶክሜንት በማሟላት አሰራሩን የተከተለ ወቅቱን የጠበቀ ክፍያ እንደሚፈጽሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማእከል የውል ስምምነት እናሲኦኢ ክፍያ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል መሀሙድ ሻፊ በበኩላቸው በጋራ ውይይቱ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ እ.ኤ.አ ከጥር 01 ቀን 2015 ጀምሮ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ተሰማርተው የተሰው እና የቆሰሉ የሰራዊት አባላት በተሻለ መልኩ እና በተቀናጀ የጊዜ ገደቡን በጠበቀ መልኩ ወርሃዊ  ክፍያ እና ካሳ ክፍያዎች ለመፈፀም በቀረበው ሰነድ መግባባት ላይ መደረሱን ቡድን መሪው ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ግርማቸው አብርሀ
ፎቶግራፍ ሜቲ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍17
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ከሀገር በቀሉ ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ ጋር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረመ።

የፊርማ ስነ ስርዓቱን በአየር ኃይል በኩል ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከልና የክለቡ የቦርድ ፕሬዘዳንት የፈረሙ ሲሆን ኩባንያውን በመወከል ስራ አስኪያጁ አቶ ሀብተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ፈርመዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳሉት የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ በሀገሪቱ እግር ኳስ ቀደምት ታሪክ ያለው ገናና የእግር ኳስ ክለብ እንደነበረ አውስተው ተቋሙ ከሪፎርሙ ወዲህ ክለቡን ከፈረሰበት እንደ አዲስ በማቋቋም ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መድረክ ዳግም እንዲመለስ በትኩረት መሰራቱን ጠቁመዋል።

ያለህዝብና ተቋማት ድጋፍ ስፖርቱን ማሳደግ እንደማይቻል የተናገሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያው ከቡድናችን ጋር በትብብር ለመስራት በመወሰኑ በአየር ኃይል እና በቦርዱ ስም አመስግነዋል።

የዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀበተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ኩባንያቸው  መቻልን ጨምሮ ለሌሎች በፕሪምዬር ሊጉና በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደሩ ለሚገኙ ቡድኖች የማሊያ ስፖንሰር በማድረግ በአጋርነት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው አሁን ደግሞ በሀገሪቱ እግር ኳስ ታላቅ ስምና ዝና ካለው ከአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ጋር በትብብር ለመስራት ሲወስን ታላቅ ኩራት የሚሰማቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ ዮናስ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍104
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የነፃይቱ ሀገር ወጥቶ አደር የኢትዮጵያ ወታደር !!

ወታደር የተሠራ አእምሮ የተገነባ ማንነት ያለው ዜጋ ነው። የያዘውን ሃላፊነት በሚገባ የሚረዳ በምንም ምክንያት ተልዕኮውን የማይጎዳ ምግባረ ሠናይ የሀገሩ ታማኝ አገልጋይ ነው።

የኢትዮጵያ ወታደር ደግሞ በአኩሪ የነፃነት ታሪክ፣ የህዝቦቿ የአሸናፊነት ስነልቦና፣ ሀገርን ከራሱም በላይ የመውደድ ሃብት ተኮትኩቶ ያደገ ነው። በነዚህ ወርቃማ እሴቶች ላይ ወታደራዊ ሳይንስ እና ዕውቀት አስተሳሰብ እና ክህሎት ሲጨመርበት ሀገሩን ባለማስደፈር በዓለም ግንባር ቀደም ሆኖ ሠላም በማስከበር ደጋግሞ ብቃቱን ጥራቱን ስኬቱን አሳይቷል።

የኢትዮጵያ ወታደር ለድካም ፊት አይሰጥም።ረሃብና ጥምን የሚቋቋምበት፤ በቆላ ደጋና በረሃ ሐላፊነትን ጠንቅቆ ውብ አድርጎ የመወጣት ብቃት ከሌላው ማህበረሰብ ይለያል።

የኢትዮጵያ ወታደር ለእረፍት ቀጠሮ አይዝም።ሃያ አራት ሠዓታት ይሠራል። ላብ ደም አስፈላጊ ከሆነ ውድ ህይወቱን ወዶ ይገብራል።በዚህም ሠንደቅ ዓላማውን በሀገሩ ምድር ከፍ አድርጎ ይሠቅላል። የሀገሩን ሉዓላዊነት ያስከብራል።ህዝቡን ያኮራል። ይሄ ተግባሩ ወደ ትውልድም ይሻገራል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ወታደር የነፃይቱ ምድር ወጥቶ አደር ነውና።

በፈይሳ ናኔቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18👍9😁2🥰1