የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃሙስ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
"የዓለም አካል ናትና ስለ ብሄራዊ ጥቅሟ.."
ከሀገር ተነስቶ ቀጠናን አካሎ አሁናዊ ዓለማዊ እውነታን ያላገናዘበ እይታ ሀገራዊ ህላዌን ለማስጠበቅ ይቸገራል።
የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በውስጥ ብቻ በታጠረ ዙሪያ ገባን በዘነጋ አኳኃን ማስከበር እንደማይቻል ሉላዊዋ ዓለም እያረጋገጠችልን ነው።
በዘመናዊዋ ዓለማችን ዳር ድንበርን በማጠር "አትድረሱብኝ አልደርስባችሁም" በሚል ጨዋነት ከጉዳት መጠበቅ ዘበት ሆኗል። የሀገር ብሄራዊ ጥቅም ያለ ቀጠናዊ ተደጋጋፊነት፣ትብብር ብሎም ሰጥቶ መቀበላዊ ጥምረት ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል።
መርጦ ሰሚ የሆነችው ዓለማችን ስለ ፍትህና ርትዕ ሳይሆን ባፈረጠሙት ከኢኮኖሚ እስከ ወታደራዊ ደንዳና አቅማቸው ዓለምን የሚዘውሩ ሃያላን መልካም ፈቃድ መመራቷ ለክርክር የማይበቃ ሀቅ ነው።
የመካከለኛው ምስራቅ ሰሞነኛው የእስራኤል ፍልስጤም አነጋጋሪ ጦርነት ከብዙ ሃገራት ብሄራዊ ጥቅም ጋር ተሰናስኖ ጉዳዩ አለም-አቀፋዊ መልክ የያዘበትን አመክንዮ በቅጡ ለመረመረ ከጦርነቱ በስተጀርባ አድፋጭ ፍላጎቶች ይገለጡለታል።
የድፍን ዓለም ሚዲያ ካሜራዎች ጋዛ ላይ ተተክለው እንደየ ሀገራቸው ብሄራዊ ፍላጎት ልክ ...ሃራ አራት ሰዓት እያንዳንዷን ጉዳይ ሲተነትኑ፣ተሟጋቾችን በስሜት ሲያከራክሩ፣የሰብዓዊነት ጥያቄዎች ሲዥጎደጎዱ እያየን እየሰማን ነው።
ስለ ሰብዓዊነት ከተነሳ የሱዳን ጉዳይ ስለምን በዚያው ልክ አላነጋገረም? የሱዳናዊያን ሰቆቃ ስለምን "ጆሮ ተነፈገው?" እስኪያስብል በመከራው ልክ አልተጯጯኸም። ሱዳናዊያንም እራሳቸው በራሳቸው በለኮሱት እሳት ፍዳቸውን እያዩ ዓለም በተገቢው መጠን ጆሮ አልሰጥ ያለችበት ነገር ያስተዛዝባልም ያናድዳልም።
ይህ አሳዛኝ እውነታ "ሱዳን እንደዛ እንድትሆን ይፈለጋልን?" የሚል ጥያቄ ቢያስነሳ ነውር አይሆንም።
በአለፍ ገደም ብልጭ በሚያደርጉት የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ የጉልበታሞቹ ሚዲያዎች ከካርቱም እስከዳርፉር ያለውን ቀውስ "እይዋቸው" ለሚል ስላቃቸው የዜና ማዳመቂያቸው ማድረጋቸው ያብከነክናል።
ተወደደም ተጠላ ዓለም መርጦ ሰሚ የመሆኗን ነገር ለመቀበል የሚያስገደድ ጊዜ ላይ እንገኛለን።
ለአፍሪካ ብሎም ለቀጠናችን ምስራቅ አፍሪካ በተለይ ለአፍሪካ ቀንድ.. "የዓለም ዘዋሪዎቹ ምልከታ እንዴት ነው" ብሎ በቅጡ መረዳት ይገባል።
ሀገራት ከውስጣዊ ጥንካሬያቸው ባሻገር እንደየሚገኙበት ጂኦ-ፓለቲካዊ አቀማመጥ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አኳያ ተፈጥሮ ለቀጠናቸው የሰጠቻቸውን በረከት ለየህዝቦቻቸው ጥቅም ማዋል ከቻሉ የሃብት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትና ጥበብ ባለቤት ሆነዋል ማለት ነው።
ይህ ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎቶቻቸውን እንደ ሀገር፤የጋራ ተስፋና መልካም ጸጋ ፈጣሪ ዕድላቸውን በትብብር ማጽናት የሚያስችላቸው አይደፈሬ ሃይል እንደሚሆናቸውም "ሳይታለም የተፈታ ነው።"
ታዲያ ስለምን የአፍሪካ ቀንድ የማያባራ ግጭቶቻቸው በሚቀፈቅፏቸው የረሃብ፣የስደት፣ የኃላቀርነትና የሌሎች እርጥባን ሻችነት መለያ የተለጠፈባቸው ሀገራት መገኛ እንደሆነ ተደርጎ በዓለም እንዲታሰብ ተደረገ?
የአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂክ መሆን ከጸጋ በረከትነቱ ይልቅ ለባለቤቶቹ የቀንዱ ሀገራት ከእርግማን የከፋ ዋጋ አስከፋያቸውና የሰላም እጦት መንስዔያቸው እንደሆነስ ለምን ቀጠለ ለምንስ ሊቆም አልቻለም? ከተባለ ምላሹ "ከውጭ ወደ ቀጠናው በጥንቃቄ እየተጠመቁ የሚላኩ የግጭት ሴራዎች አለማቋረጣቸው ነው።
በቀንዱ ሀገራት ውስጥ የማያባራ እና መልኩን እየለዋወጠ ሳያቋርጥ የሚቀጥል የግጭት ጠመቃ እና የቀውስ አዙሪት ዳከራ ዘዋሪዎቹ እጀ-ረጅምና ሃይ ባይ የሌላቸው የዓለማችን ጉልበታሞች መሆናቸው ደግሞ ነገሩን አወሳስቦ ውሉን አጥፍቶታል።
የባለ ፈርጣማ ጡንቻ ባለቤቶቹ ሃያላን ስጋት ምንጩ የቀንዱ ሀገራት ሰላም ሆነው፤የውስጥ ችግሮቻቸውን ፈትተው ቀጠናዊ ህብረት በመፍጠር እንደ ባለቤትነታቸው ፍትሃዊነትን ባሰፈነ የየራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ባስከበረ ጥምረት መቆራኘት ከቻሉ የሚያሳጣቸውን ወሳኝ ጥቅም ማስላታቸው ነው።
ስለሆነም የቀንዱ ሀገራት የአዙሪት ጉዞ ማባሪያ እንዳይኖረው ተግተው ይሰራሉ።
በዚያ ላይ ደግሞ በየሀገራቱ ውስጥም ከገዛ ሀገራቸውና ወገናቸው ጥቅም ይልቅ ለባዕዳን አዳሪ ህሊና ቢስ የጥቅም ተገዢ ጉዳይ አስፈጻሚዎችም አሏቸውና ይህ ለእነሱ "የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ" ሆኖላቸው ተመችቷቸዋል።
ከዚህ አኳያ ከቀንዱ ሀገራት አንዷ የሆነችው የእኛዋ ኢትዮጵያስ? ይሁንታን የሚቸር ፈቃዳችሁን ከሰጣችሁኝ በሚቀጥለው ጽሁፌ ልመለስ?
በአስቻለው ሌንጫ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
👍40❤12🔥2👏1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም እና የፀጥታ ዲፓርትመንት ፋይናንስ ሃላፊ በሚስተር ሰሊጂ ባንጊ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከልን ጎበኘ፡፡
ቡድኑን ጨምሮ የማዕከሉ ከፍተኛ አመራሮች በሱማሊያ ሰላም ማስከበር ያሰማሩ ሀገሮች ለሰራዊቶቻቸው ለሚከፍሏቸው ወርሀዊ እና የካሳ ክፍያ በሚመለከት እንዲሁም ኦዲትን በተመለከተ ለሁለት ቀናት የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡
የመከላከያ ሰላም ማከበር ማዕከል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መነንግስቴ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሠራዊት በማሰማራት ውጤታማ የሰላም ማስከበር ግዳጅ እየተወጣች መሆኗን ገልፀው የአውሮፓ ህብረት እና የአባል ሀገራቱ የማያቋርጥ የፋይናንስ ድጋፍ ሰራዊቱ በሶማሊያ የተሰጠውን አስቸጋሪ ግዳጅ መፈፀም አስችሎታል ብለዋል፡፡
በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊቱ ሳይታክት አልሻባብን በማጥፋት በርካታ ተልእኮዎችን በመወጣት ምሳሌ መሆን ችሏል ያሉት አዛዡ ልዑካን ቡድኑ ለሰራዊቱ የሚከፈል የሽልማት ገንዘብ እና የካሳ ክፍያዎችን በወቅቱ ክፍያ ለህብረቱ ፋይናስ በኩል እንዲፈፀም መፍትሄ የሚያሥፈልገው በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም እና ፀጥታ ዲፓርትመንት ፋይናስ ሀላፊ ሚስተር ሰሊጂ ባንጊ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ አሚሶም አትሚስ ተልዕኮ ሰላምን በማረጋጋት ለከፈሉት መስዋዕትነት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአሚሶም/ አትሚስ ለተሰማሩ የሰላም አስከባሪ አባላት አስፈላጊውን ዶክሜንት በማሟላት አሰራሩን የተከተለ ወቅቱን የጠበቀ ክፍያ እንደሚፈጽሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማእከል የውል ስምምነት እናሲኦኢ ክፍያ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል መሀሙድ ሻፊ በበኩላቸው በጋራ ውይይቱ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ እ.ኤ.አ ከጥር 01 ቀን 2015 ጀምሮ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ተሰማርተው የተሰው እና የቆሰሉ የሰራዊት አባላት በተሻለ መልኩ እና በተቀናጀ የጊዜ ገደቡን በጠበቀ መልኩ ወርሃዊ ክፍያ እና ካሳ ክፍያዎች ለመፈፀም በቀረበው ሰነድ መግባባት ላይ መደረሱን ቡድን መሪው ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ ግርማቸው አብርሀ
ፎቶግራፍ ሜቲ ጌታቸው

❤21👍17
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ከሀገር በቀሉ ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ ጋር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረመ።
የፊርማ ስነ ስርዓቱን በአየር ኃይል በኩል ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከልና የክለቡ የቦርድ ፕሬዘዳንት የፈረሙ ሲሆን ኩባንያውን በመወከል ስራ አስኪያጁ አቶ ሀብተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ፈርመዋል።
ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳሉት የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ በሀገሪቱ እግር ኳስ ቀደምት ታሪክ ያለው ገናና የእግር ኳስ ክለብ እንደነበረ አውስተው ተቋሙ ከሪፎርሙ ወዲህ ክለቡን ከፈረሰበት እንደ አዲስ በማቋቋም ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መድረክ ዳግም እንዲመለስ በትኩረት መሰራቱን ጠቁመዋል።
ያለህዝብና ተቋማት ድጋፍ ስፖርቱን ማሳደግ እንደማይቻል የተናገሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያው ከቡድናችን ጋር በትብብር ለመስራት በመወሰኑ በአየር ኃይል እና በቦርዱ ስም አመስግነዋል።
የዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀበተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ኩባንያቸው መቻልን ጨምሮ ለሌሎች በፕሪምዬር ሊጉና በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደሩ ለሚገኙ ቡድኖች የማሊያ ስፖንሰር በማድረግ በአጋርነት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው አሁን ደግሞ በሀገሪቱ እግር ኳስ ታላቅ ስምና ዝና ካለው ከአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ጋር በትብብር ለመስራት ሲወስን ታላቅ ኩራት የሚሰማቸው መሆኑንም ገልፀዋል።
ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ ዮናስ ጌታቸው

👍10❤4
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የነፃይቱ ሀገር ወጥቶ አደር የኢትዮጵያ ወታደር !!
ወታደር የተሠራ አእምሮ የተገነባ ማንነት ያለው ዜጋ ነው። የያዘውን ሃላፊነት በሚገባ የሚረዳ በምንም ምክንያት ተልዕኮውን የማይጎዳ ምግባረ ሠናይ የሀገሩ ታማኝ አገልጋይ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር ደግሞ በአኩሪ የነፃነት ታሪክ፣ የህዝቦቿ የአሸናፊነት ስነልቦና፣ ሀገርን ከራሱም በላይ የመውደድ ሃብት ተኮትኩቶ ያደገ ነው። በነዚህ ወርቃማ እሴቶች ላይ ወታደራዊ ሳይንስ እና ዕውቀት አስተሳሰብ እና ክህሎት ሲጨመርበት ሀገሩን ባለማስደፈር በዓለም ግንባር ቀደም ሆኖ ሠላም በማስከበር ደጋግሞ ብቃቱን ጥራቱን ስኬቱን አሳይቷል።
የኢትዮጵያ ወታደር ለድካም ፊት አይሰጥም።ረሃብና ጥምን የሚቋቋምበት፤ በቆላ ደጋና በረሃ ሐላፊነትን ጠንቅቆ ውብ አድርጎ የመወጣት ብቃት ከሌላው ማህበረሰብ ይለያል።
የኢትዮጵያ ወታደር ለእረፍት ቀጠሮ አይዝም።ሃያ አራት ሠዓታት ይሠራል። ላብ ደም አስፈላጊ ከሆነ ውድ ህይወቱን ወዶ ይገብራል።በዚህም ሠንደቅ ዓላማውን በሀገሩ ምድር ከፍ አድርጎ ይሠቅላል። የሀገሩን ሉዓላዊነት ያስከብራል።ህዝቡን ያኮራል። ይሄ ተግባሩ ወደ ትውልድም ይሻገራል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ወታደር የነፃይቱ ምድር ወጥቶ አደር ነውና።
በፈይሳ ናኔቻ

❤18👍9😁2🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
መርማሪ ቦርዱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያየ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ከዚህ ቀደም ሰጥቶ በነበረው ምክረ ሃሳብ አተገባበር ዙሪያ ውይይት ማድረጉን ገለጸ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከዕዙ ጋር ያደረገውን ውይይት በማስመልከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
መርማሪ ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፥ በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
በዚህም በአማራ ክልል በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በሸዋሮቢት፣ በኮምቦልቻና ከክልሉ ውጪም በአዲስ አበባና በአዋሸ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በመጎብኘት በወቅቱ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።
በጉብኝቱም የተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጡን በወቅቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም በሲዳማ ክልል አፖስቶ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች አሉ የሚል ጥቆማ ደርሶት ቦታው ድረስ በመሄድ ባደረገው ማጣራት ምንም አይነት ተጠርጣሪ አለማግኘቱን መግለጹም የሚታወስ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ ተዘዋውሮ በተመለከተውና ተጠርጣሪዎቹ ባነሷቸው ሃሳቦች ዙሪያ ከዕዙ ጋር ባደረገው ውይይት ምክረ ሀሳቦችን መስጠቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አዝመራው አንዴሞ በዛሬው ዕለት በሰጡት መገለጫ አንስተዋል።
በመግለጫቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ የተጠርጣሪዎችን አያያዝ በጎበኘበት ወቅት ወደ ማዕከል ያልተወሰዱ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን መመልከቱንና ይህንንም ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ገልጾ እንደነበር አስታውሰዋል።
በሌላ በኩል የተጠርጣሪዎች የምርመራ ሂደት መፋጠን እንዳለበት ለዕዙ ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን ጠቅሰው፥ ከዕዙ ጋር በተደረገ ውይይትም ተጠርጣሪዎች ወደ ማዕከል መሰብሰባቸው እንደተገለጸላቸው ጠቁመዋል፡፡
በዚህም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው ከተያዙ 4 ሺህ 116 መካከል እስከ አሁን በሁለት ዙር 2 ሺህ 424 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።
ቀሪዎቹ 1 ሺህ 692 ተጠርጣሪዎች በሶስተኛ ዙር የተሃድሶ ስልጠና ወስደው የሚቀላቀሉ መሆኑንና የተጠርጣሪዎች የምርመራ ሂደት እየተፋጠነ እንደሚገኝ ከዕዙ ጋር ባደረጉት ውይይት መረዳታቸውን አውስተዋል።
ቦርዱ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የተመለከተውን ጉዳይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባሻገር ለየኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ምክረ ሃሳብ መስጠቱንም አስታውሰዋል፡፡
በዚህ ረገድ ያለው አፈጻጸም መልካም መሆኑ በዕዙ በኩል መገለጹን ጠቅሰው ቦርዱ በቀጣይ በየአካባቢው ተዘዋውሮ ምልከታ በማድረግ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በሌላ መልኩም የአማራ ክልል አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ከዕዙ ጋር ባደረጉት ውይይት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረዳታቸውን ነው የገለጹት።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በቀጣይ ጉብኝቱ ወደ ተለያዩ ቦታዎች በማምራት የቀሩ ተጠርጣሪዎችን ሁኔታ የሚመለከት መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል።

👍16❤3🔥1🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
"ተስፋዋን በመርጦ ሰሚ የሩቅ ባዕዳን አላደረገችም።"
የአፍሪካ ቀንዷ ኢትዮጵያ የሀገራዊ ስብራትና የሁለንተናዊ ዕድገት ዋነኛ ማነቆዎች ናቸው ያለቻቸውን ዋና ዋና ችግሮችን መለየቷና ችግሮቹ የፈጠሯቸውን ህመሞች አክማ ለማዳን ቆርጣ መነሳቷ አዲስና ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ መግለጧን የሚያመላክት ነው።
ከእነዚህም መካከል ሀገራዊ ተቋማትን ማንም እየመጣ የሚያፈርስ የሚሰራቸው ሳይሆን፥ልክ እንደ ሀገር ሁሉ በጽኑ መሠረት ላይ ተገንብተው በቀጣይነት እያደጉ እየተመነደጉ የኢትዮጵያ መለያ ምልክት፣የዜጎች አለኝታና ኩራት፣የሀገረ-መንግስት አቅምና ጉልበት ሆነው ትውልድ በክብር የሚቀባበላቸው እንዲሆኑ አሰቻይ ጅማሩ ፈጥሮ የመቀጠሉ ተግባር ይበል የሚሰኝ ነው።
ለአንድ ሀገርና ህዝብ በእጅጉ ወሳኝ፣የብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሳኪያ ሃይል፣የህልውና ማስጠበቂያና የዜጎች መኩሪያ መመኪያ ተቋማት መካከል የመከላከያ ተቋም ዋነኛው ነው ሊባል የሚችል ነው።
ታዲያ አሁን ኢትዮጵያ እየገነባች የምትገኘው የመከላከያ ሃይል ዘመኑን ያገናዘበና ሀገራዊ እውነታን ያመሳከረ፣ አውዶችን ያሟላ፣መርሁን ሀገር ባስቀደመ እምነት በፕሮፌሽናሊዝም ዲሲፕሊን ያደረገ፣አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂ አፈራሽ ትጥቆችን ያነገበ፣ የኢትዮጵያዊ መገለጫ የሆነውን እሴት ተላብሶ ሙሉ ልብ የታጠቀ በኢትዮጵያ ልክ የተለቀ የመከላከያ ሃይል በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ ይገኛል።
ይህ ሀይል ከረጅም ጊዜ አንጻር ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና አለም- አቀፋዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ በተተነተነ ጭብጥ ዘላቂ ግንባታውን በከፍተኛ ጥራት እየከወነ ይገኛል።
ከአጭር ጊዜ አኳያ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ኮሶ ከተጣባት የባዕዳን ሴራ አኳያ የውስጥ ተላላኪና በወገን ደም ትርፍ አስይ ባንዳዎች እዚህም እዚያም የሚለኳኮሱ እሳቶችን ማጥፋትና የለኳሾቹን ምንጭ የማድረቅ አሁናዊ ተልዕኮውን በድል እየተወጣቸው ወደ ተሟላ ሰላም የሚያስጉዝ ጥርጊያን እያመቻቸ ነው።
ከዚህ አንጻርም ኢትዮጵያ ስትፈልግ ብቻ መርጣ የምትሰማውን ዓለም ተስፋ አድርጋ ሳይሆን በገዛ እራሷ እጅ በምትከውነው ሀገር የመገንባት ሂደት ትውልድ አኩሪና በተከታታይ ውርርስ የሚዘልቅ የታላቅነት መም ላይ እራሷን ለስኬት ሩጫ አዘጋጅታለች።
ከዘመናት ህመም ተፈውሶ፣ፈተናዎችን በድል ጥሶ፣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሳካት ማረጋገጥ የሚያስችልን ብርቱነት እነጻዋም ያለዕረፍት የቀጠለ ሲሆን አጓጊ ውጤቶችም ከወዲሁ የተስፋ ነጸብራቃቸውን ማንሰራፋት ጀምረዋል።
አሁንም ፈተናዎች አሉ።አሁንም በውስጥ ዳከራ ዕድሜ እንድንፈጅ የማይማስ ስር የማይበጠስ ቅጠል ላይኖር ይችላል።
ነገር ግን ኢትዮጵያ ከውስጥ ወደ ውጭ ተመልክታ ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎቷን አስጠብቃ የሚገባትን ማግኘት የሚያስችል አቅምና ሞራል ያላት፣በፍትሃዊነት የምታምን፣በታሪኳም ለራሷ ጥቅም ስትል ማንንም ወርራ የማታውቅ፣ሲነኳትም ዝም የማትል በእውነትና በእምነት ልዕልና ከፍ ባለ ሞራል የምታስብ የምታምንም ናት።
በትብብር፣በተደጋጋፊነት፣በጋራ ተጠቃሚነትም ኢትዮጵያ በሚገባ ታምናለችና ሩቅ ካሉቱ ቱጃርና ጉልበታሞች ይልቅ የቅርብ ቅርብ ተጎራባቾቿን አጥብቃ የምትወድ የምታከብር ከራሷም ባሻገር ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣የጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት በሃላፊነት የምትንቀሳቀስ ይህንን በተግባር ያረጋገጠችም ናት።
የኢትዮጵያ ውጥን ተሳክቶ፣የቀንዱ ሃገራትም በራሳቸው መንገድ ስለጋራ ጥቅምና አብሯዊ ዕድገት የበኩላቸውን አድርገው የቀንዱ መልክ በፍካትና በአስገራሚ ውበት የሚቀይሩበት መልካም ዕድል እንዳይወግግ ብዙ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል።
ይህ ግን እንደነበረ ሊቀጥል አይችልም።በተለዋዋጯ አለማችን የማይታሰቡ የነበሩ ሲሆኑ ደጋግመን አይተናል።የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጦርነት፣ረሃብ ስደትና ኃላቀርነት ጨለማ ታሪክ መዘጋቱ አይቀሬ ነው።የአፍሪካ ቀንድ ስቃይ ማብቂያ ጊዜ ይመጣል።
ትብብር ተደጋጋፊነት፣ትምምን፣ሰጥቶ መቀበል፣ችግር መሞላላት ለቀጠናው ሀገራት የምርጫ ብቻ ጉዳይ ሳይሆን ተያይዞ ለማደግና የቀጠናውን የብርሃን ዘመን ለማብሰር ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል።
ኢትዮጵያ መርጣ የምትሰማ ዓለም ላይ ሳይሆን በብዙ ትስስሮሽ አጠገቧ ባሉ እሷን መሳዮች ጋር ተባብራ፣ ተደጋግፋ በፍቅር መስራት ቀዳሚ ምርጫዋ ካደረገች ሰነባብታለች።እናም የውስጥ የቤት ስራዋን ከቅርብ የጉርብትና ወዳጅነት ጋር በፍቅር አዛምዳ ተያይዞ የማደጊያ እውነትን በእጇ ይዛለች።
አዋጩ መንገድ ይህ ነውና እውነት ተከታዮች እንደሚበዙ አያጠራጥርም።

❤23👍17