FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ከሀገር በቀሉ ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ ጋር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረመ።

የፊርማ ስነ ስርዓቱን በአየር ኃይል በኩል ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከልና የክለቡ የቦርድ ፕሬዘዳንት የፈረሙ ሲሆን ኩባንያውን በመወከል ስራ አስኪያጁ አቶ ሀብተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ፈርመዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳሉት የአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ በሀገሪቱ እግር ኳስ ቀደምት ታሪክ ያለው ገናና የእግር ኳስ ክለብ እንደነበረ አውስተው ተቋሙ ከሪፎርሙ ወዲህ ክለቡን ከፈረሰበት እንደ አዲስ በማቋቋም ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መድረክ ዳግም እንዲመለስ በትኩረት መሰራቱን ጠቁመዋል።

ያለህዝብና ተቋማት ድጋፍ ስፖርቱን ማሳደግ እንደማይቻል የተናገሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያው ከቡድናችን ጋር በትብብር ለመስራት በመወሰኑ በአየር ኃይል እና በቦርዱ ስም አመስግነዋል።

የዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባኒያ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀበተ ስላሴ ገብረ ክርስቶስ ኩባንያቸው  መቻልን ጨምሮ ለሌሎች በፕሪምዬር ሊጉና በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደሩ ለሚገኙ ቡድኖች የማሊያ ስፖንሰር በማድረግ በአጋርነት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው አሁን ደግሞ በሀገሪቱ እግር ኳስ ታላቅ ስምና ዝና ካለው ከአየር ኃይል ንብ የእግር ኳስ ክለብ ጋር በትብብር ለመስራት ሲወስን ታላቅ ኩራት የሚሰማቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ ዮናስ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍104
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የነፃይቱ ሀገር ወጥቶ አደር የኢትዮጵያ ወታደር !!

ወታደር የተሠራ አእምሮ የተገነባ ማንነት ያለው ዜጋ ነው። የያዘውን ሃላፊነት በሚገባ የሚረዳ በምንም ምክንያት ተልዕኮውን የማይጎዳ ምግባረ ሠናይ የሀገሩ ታማኝ አገልጋይ ነው።

የኢትዮጵያ ወታደር ደግሞ በአኩሪ የነፃነት ታሪክ፣ የህዝቦቿ የአሸናፊነት ስነልቦና፣ ሀገርን ከራሱም በላይ የመውደድ ሃብት ተኮትኩቶ ያደገ ነው። በነዚህ ወርቃማ እሴቶች ላይ ወታደራዊ ሳይንስ እና ዕውቀት አስተሳሰብ እና ክህሎት ሲጨመርበት ሀገሩን ባለማስደፈር በዓለም ግንባር ቀደም ሆኖ ሠላም በማስከበር ደጋግሞ ብቃቱን ጥራቱን ስኬቱን አሳይቷል።

የኢትዮጵያ ወታደር ለድካም ፊት አይሰጥም።ረሃብና ጥምን የሚቋቋምበት፤ በቆላ ደጋና በረሃ ሐላፊነትን ጠንቅቆ ውብ አድርጎ የመወጣት ብቃት ከሌላው ማህበረሰብ ይለያል።

የኢትዮጵያ ወታደር ለእረፍት ቀጠሮ አይዝም።ሃያ አራት ሠዓታት ይሠራል። ላብ ደም አስፈላጊ ከሆነ ውድ ህይወቱን ወዶ ይገብራል።በዚህም ሠንደቅ ዓላማውን በሀገሩ ምድር ከፍ አድርጎ ይሠቅላል። የሀገሩን ሉዓላዊነት ያስከብራል።ህዝቡን ያኮራል። ይሄ ተግባሩ ወደ ትውልድም ይሻገራል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ወታደር የነፃይቱ ምድር ወጥቶ አደር ነውና።

በፈይሳ ናኔቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18👍9😁2🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

መርማሪ ቦርዱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያየ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ከዚህ ቀደም ሰጥቶ በነበረው ምክረ ሃሳብ አተገባበር ዙሪያ ውይይት ማድረጉን ገለጸ። 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከዕዙ ጋር ያደረገውን ውይይት በማስመልከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።    

መርማሪ ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፥ በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። 

በዚህም በአማራ ክልል በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በሸዋሮቢት፣ በኮምቦልቻና ከክልሉ ውጪም በአዲስ አበባና በአዋሸ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በመጎብኘት በወቅቱ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። 

በጉብኝቱም የተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጡን በወቅቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም በሲዳማ ክልል አፖስቶ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች አሉ የሚል ጥቆማ ደርሶት ቦታው ድረስ በመሄድ ባደረገው ማጣራት ምንም አይነት ተጠርጣሪ አለማግኘቱን መግለጹም የሚታወስ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ ተዘዋውሮ በተመለከተውና ተጠርጣሪዎቹ ባነሷቸው ሃሳቦች ዙሪያ ከዕዙ ጋር ባደረገው ውይይት ምክረ ሀሳቦችን መስጠቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አዝመራው አንዴሞ በዛሬው ዕለት በሰጡት መገለጫ አንስተዋል።

በመግለጫቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ የተጠርጣሪዎችን አያያዝ በጎበኘበት ወቅት ወደ ማዕከል ያልተወሰዱ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን መመልከቱንና ይህንንም ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ገልጾ እንደነበር አስታውሰዋል።

በሌላ በኩል የተጠርጣሪዎች የምርመራ ሂደት መፋጠን እንዳለበት ለዕዙ ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን ጠቅሰው፥ ከዕዙ ጋር በተደረገ ውይይትም ተጠርጣሪዎች ወደ ማዕከል መሰብሰባቸው እንደተገለጸላቸው ጠቁመዋል፡፡ 

በዚህም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው ከተያዙ 4 ሺህ 116 መካከል እስከ አሁን በሁለት ዙር 2 ሺህ 424 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።
 
ቀሪዎቹ 1 ሺህ 692 ተጠርጣሪዎች በሶስተኛ ዙር የተሃድሶ ስልጠና ወስደው የሚቀላቀሉ መሆኑንና የተጠርጣሪዎች የምርመራ ሂደት እየተፋጠነ እንደሚገኝ ከዕዙ ጋር ባደረጉት ውይይት መረዳታቸውን አውስተዋል።

ቦርዱ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የተመለከተውን ጉዳይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባሻገር ለየኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ምክረ ሃሳብ መስጠቱንም አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ረገድ ያለው አፈጻጸም መልካም መሆኑ በዕዙ በኩል መገለጹን ጠቅሰው ቦርዱ በቀጣይ በየአካባቢው ተዘዋውሮ ምልከታ በማድረግ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ መልኩም የአማራ ክልል አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ከዕዙ ጋር ባደረጉት ውይይት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረዳታቸውን ነው የገለጹት።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በቀጣይ ጉብኝቱ ወደ ተለያዩ ቦታዎች በማምራት የቀሩ ተጠርጣሪዎችን ሁኔታ የሚመለከት መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍163🔥1🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አርብ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

"ተስፋዋን በመርጦ ሰሚ የሩቅ ባዕዳን አላደረገችም።"

የአፍሪካ ቀንዷ ኢትዮጵያ የሀገራዊ ስብራትና የሁለንተናዊ ዕድገት ዋነኛ ማነቆዎች ናቸው ያለቻቸውን ዋና ዋና ችግሮችን መለየቷና ችግሮቹ የፈጠሯቸውን ህመሞች አክማ ለማዳን ቆርጣ መነሳቷ  አዲስና ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ መግለጧን የሚያመላክት ነው።

ከእነዚህም መካከል ሀገራዊ ተቋማትን ማንም እየመጣ የሚያፈርስ የሚሰራቸው ሳይሆን፥ልክ እንደ ሀገር ሁሉ በጽኑ መሠረት ላይ ተገንብተው በቀጣይነት እያደጉ  እየተመነደጉ የኢትዮጵያ መለያ ምልክት፣የዜጎች አለኝታና ኩራት፣የሀገረ-መንግስት አቅምና ጉልበት ሆነው ትውልድ በክብር የሚቀባበላቸው እንዲሆኑ አሰቻይ ጅማሩ ፈጥሮ የመቀጠሉ ተግባር ይበል የሚሰኝ ነው።

ለአንድ ሀገርና ህዝብ በእጅጉ ወሳኝ፣የብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሳኪያ ሃይል፣የህልውና ማስጠበቂያና የዜጎች መኩሪያ መመኪያ ተቋማት መካከል የመከላከያ ተቋም ዋነኛው ነው ሊባል የሚችል ነው።

ታዲያ አሁን ኢትዮጵያ እየገነባች የምትገኘው የመከላከያ ሃይል ዘመኑን ያገናዘበና ሀገራዊ እውነታን ያመሳከረ፣ አውዶችን ያሟላ፣መርሁን ሀገር ባስቀደመ እምነት በፕሮፌሽናሊዝም ዲሲፕሊን ያደረገ፣አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂ አፈራሽ ትጥቆችን ያነገበ፣ የኢትዮጵያዊ መገለጫ የሆነውን እሴት ተላብሶ ሙሉ ልብ የታጠቀ በኢትዮጵያ ልክ የተለቀ የመከላከያ ሃይል በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ ይገኛል።

ይህ ሀይል ከረጅም ጊዜ አንጻር ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና አለም- አቀፋዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ በተተነተነ ጭብጥ ዘላቂ ግንባታውን በከፍተኛ ጥራት እየከወነ ይገኛል።

ከአጭር ጊዜ አኳያ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ኮሶ ከተጣባት የባዕዳን ሴራ አኳያ የውስጥ ተላላኪና በወገን ደም ትርፍ አስይ ባንዳዎች እዚህም እዚያም የሚለኳኮሱ እሳቶችን ማጥፋትና የለኳሾቹን ምንጭ የማድረቅ አሁናዊ ተልዕኮውን በድል እየተወጣቸው ወደ ተሟላ ሰላም የሚያስጉዝ ጥርጊያን እያመቻቸ ነው።

ከዚህ አንጻርም ኢትዮጵያ ስትፈልግ ብቻ መርጣ የምትሰማውን ዓለም ተስፋ አድርጋ ሳይሆን በገዛ እራሷ እጅ በምትከውነው ሀገር የመገንባት ሂደት ትውልድ አኩሪና በተከታታይ ውርርስ የሚዘልቅ የታላቅነት መም ላይ እራሷን ለስኬት ሩጫ አዘጋጅታለች።

ከዘመናት ህመም ተፈውሶ፣ፈተናዎችን በድል ጥሶ፣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሳካት ማረጋገጥ የሚያስችልን ብርቱነት እነጻዋም ያለዕረፍት የቀጠለ ሲሆን አጓጊ ውጤቶችም ከወዲሁ የተስፋ ነጸብራቃቸውን ማንሰራፋት ጀምረዋል።
     
አሁንም ፈተናዎች አሉ።አሁንም በውስጥ ዳከራ ዕድሜ እንድንፈጅ የማይማስ ስር የማይበጠስ ቅጠል ላይኖር ይችላል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ ከውስጥ ወደ ውጭ ተመልክታ ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎቷን አስጠብቃ የሚገባትን ማግኘት የሚያስችል አቅምና ሞራል ያላት፣በፍትሃዊነት የምታምን፣በታሪኳም ለራሷ ጥቅም ስትል ማንንም ወርራ የማታውቅ፣ሲነኳትም ዝም የማትል በእውነትና በእምነት ልዕልና ከፍ ባለ ሞራል የምታስብ የምታምንም ናት።

በትብብር፣በተደጋጋፊነት፣በጋራ ተጠቃሚነትም ኢትዮጵያ በሚገባ ታምናለችና ሩቅ ካሉቱ ቱጃርና ጉልበታሞች ይልቅ የቅርብ ቅርብ ተጎራባቾቿን አጥብቃ የምትወድ የምታከብር  ከራሷም ባሻገር ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣የጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት በሃላፊነት የምትንቀሳቀስ ይህንን በተግባር ያረጋገጠችም ናት።

የኢትዮጵያ ውጥን ተሳክቶ፣የቀንዱ ሃገራትም በራሳቸው መንገድ ስለጋራ ጥቅምና አብሯዊ ዕድገት የበኩላቸውን አድርገው የቀንዱ መልክ በፍካትና በአስገራሚ ውበት የሚቀይሩበት መልካም ዕድል እንዳይወግግ ብዙ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል።

ይህ ግን እንደነበረ ሊቀጥል አይችልም።በተለዋዋጯ አለማችን የማይታሰቡ የነበሩ ሲሆኑ ደጋግመን አይተናል።የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጦርነት፣ረሃብ ስደትና ኃላቀርነት ጨለማ ታሪክ መዘጋቱ አይቀሬ ነው።የአፍሪካ ቀንድ ስቃይ ማብቂያ ጊዜ ይመጣል።

ትብብር ተደጋጋፊነት፣ትምምን፣ሰጥቶ መቀበል፣ችግር መሞላላት ለቀጠናው ሀገራት የምርጫ ብቻ ጉዳይ ሳይሆን ተያይዞ ለማደግና የቀጠናውን የብርሃን ዘመን ለማብሰር ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል።

ኢትዮጵያ መርጣ የምትሰማ ዓለም ላይ ሳይሆን በብዙ ትስስሮሽ አጠገቧ ባሉ እሷን መሳዮች ጋር ተባብራ፣ ተደጋግፋ በፍቅር መስራት ቀዳሚ ምርጫዋ ካደረገች ሰነባብታለች።እናም የውስጥ የቤት ስራዋን ከቅርብ የጉርብትና ወዳጅነት ጋር በፍቅር አዛምዳ ተያይዞ የማደጊያ እውነትን በእጇ ይዛለች።

አዋጩ መንገድ ይህ ነውና እውነት ተከታዮች እንደሚበዙ አያጠራጥርም።

በአስቻለው ሌንጫ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23👍17
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን  2016 ዓ.ም

በትራፊክ አደጋ የሚከሠተውን የሠው ህይወት እና የንብረት ውድመት ለመቀነስ ስልጠና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት በተሽከርካሪና ነዘቅ አገልግሎት ቡድን ለአሽከርካሪዎች እና ለነዘቅ ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የጠቅላይ መምሪያው ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ታደሰ መኩሪያ ከበጀት ዓመቱ የጠቅላይ መምሪያው እቅዶች አንዱ የሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደነበር ጠቁመው፤ ከዘመናዊ ሠራዊት መገለጫዎች ጋር ተያይዞ ወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም የሥራ ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን መሥጠት ለማንኛውም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የአሽከርካሪዎችን እና የነዘቅ ሙያተኞችን ሙያዊ አቅም ለማሣደግ ብሎም ተቋሙ በሚፈልገው የአሠራር አግባብ ልክ መሥራት እንዲችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስልጠና መሠጠቱ ወሳኝም ጠቃሚም እንደሆነ አክለዋል።

የጠቅላይ መምሪያው ጠቅላላ አገልግሎት የፋይናንስ ዳይሬክተር  ኮሎኔል ግርማ ታደሰ በበኩላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ  በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣውን በሰው እና በንብረት ላይ ውድመት እና አደጋ እየፈጠረ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ብሎም አሽከርካሪዎች በሰው ህይወትና ንብረት ጉዳት ሳያደርሱ  በጥንቃቄ ሙያዊ ግዴታዎችን እንዲወጡ ለማሥቻል ስልጠናው  ችግር ፈች መሆኑን አብራርተዋል።

የመከላከያ ጠቅላላ አገልግሎት የተሽከርካሪ እና ነዘቅ አገልግሎት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ለገሠ ድንቁ በክፍሉ ከተያዘው እቅድ አንዱ የአቅም ማጎልበቻ አጫጫጭር ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች መስጠት በመሆኑ በቴክኒክ እና የተሽከርካሪ ደህንነት አጠባበቅ ፣በመንገድ ደንብ መተላለፍ፣ በኢንሹራንስ እና አደጋ መከላከል እና በመሳሰሉት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና  መሰጠቱን ገልፀዋል።

ስልጠናውን የሠጡት  ሻለቃ አንዱአለም አበበ በበኩላቸው ክፍሉ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ያላቸውን እውቀት ለሰልጣኞች በማካፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የአሽከርካሪነት እና ተያያዥ ሙያዎች በቀጥታ ከሰው ህይወትና ከንብረት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በሀገራችንም ይሁን በተቋማችን ያለውን የትራፊክ አደጋ በመቀነሱ በኩል አጫጭር ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል።

ሰልጣኞች ስልጠናው ከነበራቸው አቅም ላይ ተደማሪ እውቀት ያገኙበት ለቀጣይ ሥራቸው ይበልጥ የሚያግዛቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ እና ሰሚራ ሃይሉ
ፎቶግራፍ ብርቱካን ረጋሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
12👍7