FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል- ግብረ-ኃይሉ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቋል፡፡

ግብረ-ኃይሉ ባወጣው መግለጫ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የፀጥታ ሥራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔም በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና የደኅንነት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እንዲሁም የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ለመዲናዋ አስተማማኝ ሰላም መሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል፡፡

አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ÷ ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል ግብረ-ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡

በኢትዮጵያዊ ባህል እንግዶችን በማስተናገድ እና በየትኛውም እቅንስቃሴያቸው ተባባሪ በመሆን ሕዝቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍266🙏6👎2😁2🔥1🤔1
በምስራቅ ሸዋና በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኘው ሰራዊት በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አካሂዷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ  ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

በምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙት የክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሳሊዮን ክብረ ሃሰን ህብረተሰቡ  ከሰራዊታችን ጎን በመሆን እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው የሚያደርጉትን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘም በቄለም ወለጋ ዞን ተሰማርቶ ግዳጁን በመወጣት ላይ የሚገኘው ክፍለ ጦር በጋዋ ቄቤ ወረዳ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መኮንን ቶንጁሬ ሰላምና ፀጥታ ሲደፈርስ በቅድሚያ ተጎጅ የሚሆኑት ሴቶችና ህፃናት በመሆናቸው የወረዳው ማህበረሰብ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ለሰላሙ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ እንደሚገባው ተናግረዋል::

በሰራዊቱና በህዝቡ ጥረት የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ለሰራዊቱ እያደረጉት ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

በውይይቱ ላይ ለሽብር ቡድኑ መረጃ እና የሎጀስቲክ አቅርቦት ሲያቀብሉ የነበሩ  አራት ግለሰቦችም በወረዳው ማህበረሰብ ፊት ይቅርታ ጠይቀው ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ተመልሰዋል ።

የወረዳው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት  በዞኑ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች በተለይም  የጋዋ ቄቤ ወረዳ  በአሸባሪው ቡድን የፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ሆኖ
መቆየቱን አውስተው ሰራዊቱ በአካባቢው ከሰፈረ ጀምሮ ከስጋት ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ዘጋቢ ፍሰሃ ሃይለማሪያምናጥላሁን አለሙ
ፎቶግራፍ ይሁኔ ቢተውና ጥላሁን አለሙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official   
👍279🔥1
የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ያዘጋጀው አውደ ጥናት ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

በዐውደ ጥናቱ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሀገራዊ ባለድርሻ አካላት ሙያዊ ሃሳብ ሊያራምዱ የሚችሉ የየክፍሉ ተወካዮች ተገኝተው ጠቃሚ ግብዓቶችን ማካፈል ችለዋል።

በዐውደ ጥናቱ ማጠቃለያ የተገኙት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጅ ለመታጠቅና በአለማችን ላይ የሚስተዋለውን የሳይበር  ጥቃት ለመከላከል በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት ማድረግ አሥፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተደራጀ አግባብ በአጭር በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሥልጠና ራስን ማብቃት የሚያሥችል መነሻና መድረሻ ያለው ዕቅድ ከነ ችግር ፈችነቱ በማዘጋጀት ብሎም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሃሳብ በመለዋወጥ እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር የሳይበር ደህንነት ስጋትን ማሥቀረት እንደሚቻል አመላክተዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ከዐውደ ጥናቱ የሳይበር ደህንነትን መጠበቅና መከላከል ብሎም የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትን ማሥቀረት የሚያሥችል ግብዓት መሠብሠብ መቻሉን ገልፀዋል።

የክፍሉ ሙያተኞች የተገኘውን ጠቃሚ ምክረ ሃሳብ በመጠቀም ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጅ በመታጠቅ  ከተቋሙ ክፍሎች ጋር ተቀራርቦ በመሠራት እንደተቋም በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚስተዋሉ ስጋቶችን ማሥቀረትና የተቀናጀ ተቋማዊ አሠራር መከተል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ የዐውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች ለሠጡት ሃሳብና አስተያዬት ምስጋና አቅርበው ከተገኘው ጠቃሚ ሃሳብ በመነሳት ክፍሉ የሚጠበቅበትን የቀጣይ ጊዜ ተቋማዊ ሥራ አሁናዊ የአለማችንን የሳይበር ሁኔታ ባገናዘበ አግባብ መሥራት  እንደሚችል አረጋግጠዋል።

ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት ኦዲት ሪፖርት ፣የሳይበር ደህንነት ረቂቅ ፖሊሲ ፣የሳይበር ሀብቶች ደህንነት ስታንዳርድ ፣ የሳይበር ሀብቶች አጠቃቀም መመሪያ ረቂቅ ውይይት የተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍376👎2🔥2🥰1
በመከላከያ ሚኒስቴር ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎችንና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን (ስክራፕ) በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም
👍12😁1