FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
በምስራቅ ሸዋና በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኘው ሰራዊት በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አካሂዷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ  ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

በምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙት የክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሳሊዮን ክብረ ሃሰን ህብረተሰቡ  ከሰራዊታችን ጎን በመሆን እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው የሚያደርጉትን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘም በቄለም ወለጋ ዞን ተሰማርቶ ግዳጁን በመወጣት ላይ የሚገኘው ክፍለ ጦር በጋዋ ቄቤ ወረዳ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መኮንን ቶንጁሬ ሰላምና ፀጥታ ሲደፈርስ በቅድሚያ ተጎጅ የሚሆኑት ሴቶችና ህፃናት በመሆናቸው የወረዳው ማህበረሰብ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ለሰላሙ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ እንደሚገባው ተናግረዋል::

በሰራዊቱና በህዝቡ ጥረት የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ለሰራዊቱ እያደረጉት ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

በውይይቱ ላይ ለሽብር ቡድኑ መረጃ እና የሎጀስቲክ አቅርቦት ሲያቀብሉ የነበሩ  አራት ግለሰቦችም በወረዳው ማህበረሰብ ፊት ይቅርታ ጠይቀው ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ተመልሰዋል ።

የወረዳው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት  በዞኑ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች በተለይም  የጋዋ ቄቤ ወረዳ  በአሸባሪው ቡድን የፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ሆኖ
መቆየቱን አውስተው ሰራዊቱ በአካባቢው ከሰፈረ ጀምሮ ከስጋት ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ዘጋቢ ፍሰሃ ሃይለማሪያምናጥላሁን አለሙ
ፎቶግራፍ ይሁኔ ቢተውና ጥላሁን አለሙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official   
👍279🔥1
የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ያዘጋጀው አውደ ጥናት ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

በዐውደ ጥናቱ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሀገራዊ ባለድርሻ አካላት ሙያዊ ሃሳብ ሊያራምዱ የሚችሉ የየክፍሉ ተወካዮች ተገኝተው ጠቃሚ ግብዓቶችን ማካፈል ችለዋል።

በዐውደ ጥናቱ ማጠቃለያ የተገኙት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጅ ለመታጠቅና በአለማችን ላይ የሚስተዋለውን የሳይበር  ጥቃት ለመከላከል በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት ማድረግ አሥፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተደራጀ አግባብ በአጭር በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሥልጠና ራስን ማብቃት የሚያሥችል መነሻና መድረሻ ያለው ዕቅድ ከነ ችግር ፈችነቱ በማዘጋጀት ብሎም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሃሳብ በመለዋወጥ እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር የሳይበር ደህንነት ስጋትን ማሥቀረት እንደሚቻል አመላክተዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ከዐውደ ጥናቱ የሳይበር ደህንነትን መጠበቅና መከላከል ብሎም የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትን ማሥቀረት የሚያሥችል ግብዓት መሠብሠብ መቻሉን ገልፀዋል።

የክፍሉ ሙያተኞች የተገኘውን ጠቃሚ ምክረ ሃሳብ በመጠቀም ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጅ በመታጠቅ  ከተቋሙ ክፍሎች ጋር ተቀራርቦ በመሠራት እንደተቋም በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚስተዋሉ ስጋቶችን ማሥቀረትና የተቀናጀ ተቋማዊ አሠራር መከተል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ የዐውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች ለሠጡት ሃሳብና አስተያዬት ምስጋና አቅርበው ከተገኘው ጠቃሚ ሃሳብ በመነሳት ክፍሉ የሚጠበቅበትን የቀጣይ ጊዜ ተቋማዊ ሥራ አሁናዊ የአለማችንን የሳይበር ሁኔታ ባገናዘበ አግባብ መሥራት  እንደሚችል አረጋግጠዋል።

ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት ኦዲት ሪፖርት ፣የሳይበር ደህንነት ረቂቅ ፖሊሲ ፣የሳይበር ሀብቶች ደህንነት ስታንዳርድ ፣ የሳይበር ሀብቶች አጠቃቀም መመሪያ ረቂቅ ውይይት የተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍376👎2🔥2🥰1
በመከላከያ ሚኒስቴር ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎችንና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን (ስክራፕ) በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም
👍12😁1
ክፍለጦሩ እየወሰደ ባለው እርምጃ ፅንፈኛ ሃይሉ እየተበታተነ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮማንዶ እና የአየር ወለድ ዕዝ ክፍለ ጦር በሰሜን ሸዋ ዞን መርሃ ቤቴ ወረዳ በፅንፈኛው ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ የፅንፈኛ ሀይሉ አባላት መመታቱን  የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ማትዮስ ማዴቦ ገልፀዋል፡፡

ከፅንፈኛው ሀይል ብሬን የጦር ሜዳ መነፅርና በርካታ የነብስ ወከፍ መሳሪያ መማረኩንም ተናግረዋል፡፡

ምክትል አዛዡ እንደተናገሩት በአከባቢው እየተሽሎኮሎከ ህዝቡን ሰላም ሲነሳ በነበረው ፅንፈኛ ቡድን ላይ ክፍለጦሩ በወሰደዉ እርምጃ በርካቶች ሲመቱ ቀሪው ሃይል እግሬን አውጭኝ ብሎ ጠፍቷል፡፡

ይህ ቡድን ለጊዜው ከአከባቢው ቢሰወርም በቁጥጥር ስር ከመዋል አያመልጥም ያሉት ሌተናል ኮሎኔል ማትዮስ ማዴቦ ህዝብን እየዘረፉ መኖር ስለማይቻል ተከታትለን የሚገባውን ቅጣት እንሰጠዋለን ብለዋል፡፡

የክፍለጦሩ ዘመቻ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል መኩሪያ ሙሉነህ በበኩላቸው የወረዳው ህዝብ በአሁኑ ወቅት በሠላም ተንቀሳቅሶ የዕለት ተዕለት ኑሮውን እየመራ ከመሆኑም በላይ ለሠራዊቱ ተልእኮ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

የፅንፈኛ ሀይሉ ፀረ-ህዝበኝነቱ እርስ በእርስ እያባላው የመዋጋት አቅሙ ከድቶት በሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ምንም በሌለበት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት በማህበራዊ ሚዲያ ህዝብን ለማደናገር እየጣረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ አብዱራህማን ሀሰን
ፎቶግራፍ አብዱራህማን ሀሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍253🥰2😁1