FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ተወያይቷል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በውይይቱ ላይ የሠራዊቱን አመራሮች ጨምሮ የዞኑና የወረዳ አመራሮች የከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ ሃይሎች የተሳተፉ ሲሆን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ስለዞኑ ሁኔታ እንዲሁም የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት ስለከተማው አጠቃላይ አሁናዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ለኮማንድ ፖስቱ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥና የማእከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዋና ሳብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ለዞኑ ህዝብ ሰላም ሠራዊቱ ሌሊት ከቀን ያለዕረፍት በሰራው ስራ እና በህዝቡና በዞኑ አመራር ድጋፍ በሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ተሳትፎ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።

አሁን የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ሁላችንም ከትላንትና በላቀ ደረጃ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አሥገንዝበዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በህዝብ ሰላም ንብረትና ህይወት ላይ የዘመተው ፅንፈኛ ኃይል በተገቢው መንገድ በመቀጥቀጡ ከሠራዊታችንና ከፀጥታ ሃይሎች ፊት የሚቆምበት አቅም አጥቶ የተበተነ መሆኑን ገልፀው ቀሪው እና ወንጀለኛው ሀይል ህይወቱን ለማቆየት ብቻ በየሸለቆው እየተሹለከለከ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌሎች የፀጥታ ሃይሎችና ስቪል አመራሮች ከሠራዊቱ ጋር ተጣምረው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን ሀይል ሙሉ በሙሉ ከዞኑ በማጥፋት ለሰላም ናፋቂው ህዝብ የተሟላ ሰላም ማረጋገጥ አለብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሠራዊቱ ከፍተኛ መስዋዕትንት በተገኘው ሰላም አሁን ላይ ለገበሬው መዳበሪያ እየተሰራጨ እና በዞኑ የልማት ስራዎች መቀጠላቸውን ተናግረዋል።

የአማራን ህዝብ እየዘረፈና እየገደለ የአማራ ነፃ አውጭ ነኝ ባይ የደም ፖለቲካ ነጋዴ የሆነው ፅንፈኛው ሃይል ተዳክሞ ምላሱ ብቻ እንደቀረ አውስተው ዘሬም ከሠራዊቱ ጎን በመሆን የቀረውን ሀይል በመመንጠር የዞናቸውን ሰላም ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ አብዱራህማን ሀሰን
ፎቶግራፍ አብዱራህማን ሀሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏129👍7🔥2
የምስራቅ ዕዝ ኮሮች በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኙ የምስራቅ ዕዝ ኢንስፔክሽን አረጋገጠ ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ኢንስፔክሽን ቡድን ኮሮች የታጠቋቸውን ወታደራዊ ትጥቆች እና ወታደራዊ ቁመናን ያካተተ ፍተሻ አድርገዋል። በዚህም ሠራዊቱ ለሚሰጠው ግዳጅ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል ።

የምስራቅ ዕዝ ኢንስፔክሽንና ሴፍቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ኮሎኔል ሱሌይማን መሀመድ  የኢንስፔክሽን ቡድኑ በዕዙ የግዳጅ ቀጠናዎች ያሉ ኮሮች የታጠቋቸውን አጠቃላይ ንብረቶች በሚፈለገው  ልክ ዝግጁነታቸውን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል ።

በምስራቅ ዕዝ የአንድ ኮር ዘመቻ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል በለጠ እውነቴ በበኩላቸው አጠቃላይ ንብረቶች በእንክብካቤ በመያዝ በየደረጃው ያለው አመራርና ተመሪው ተባብሮ በመስራት በተሟላ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ የፍተሻ ቡድኑ ማረጋገጥ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል ።

ዘጋቢ ሀብታሙ ገመቹ
ፎቶግራፍ ሀብታሙ ገመቹ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2210👏9😁4🔥1
የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ለምዕራብ እና ለማዕከላዊ ዕዞች ስታፍ አባላት በሳይበር ምንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ለምዕራብ ዕዝ ስታፍ አባላት ስለ ሳይበር ምንነት፣ የሳይበር ምህዳር፣ የሳይበር ደህንነት፣የቴክኖሎጅ እድገትና የሳይበር ጥቃት፣ ስለሳይበር ጦርነት ፣ ስለሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም፣ስለ ስማርት ስልክ እና ኮምፒዩተር አጠቃቀም እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ስልጠና ሰጥተዋል።

የመከላከያ ሳይበር ኤንተለጀንት ዳይሬክተር ኮሎኔል ኢስማኤል አብደላ  የስልጠናው አላማ የዕዙ አባላት ሳይበር መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲይዙ እና በሶሻል ሚዲያ በኩል የሳይበር ተጋላጭነትን ለመከላከል ሶሻል ሚዲያን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሎኔል ኢስማኤል  ፣የራሳችንን እና የተቋሙን መልዕክት ለማይመለከተው ሰው አሳልፎ አለመስጠት፣ የፃሃፊዎችን ኮምፒውተሮች ከኢንተርኔት ውጭ ማድረግ፣ በየስራ ቦታችን በምንጠቀማቸው ዲቫይሶች ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን ስናይ ለሚመለከተው አካል መስጠት፣ ስልክ እና ኮምፒዩተር ላይ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት፣ወድቀው የተገኙ ፍላሾችንና ሃርድ ዲስኮችን አለመጠቀም ከሳይበር ጥቃት መከላከያ መንገዶች መካከል እንደሚጠቀሱ  አብራርተዋል።

የመከላከያ ሳይበር  ኦፕሬሽን ክስተት ምላሽ ሰጪ ኤክስፐርት ሻምበል ይርጋለም ሃይሉ  በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሃገራት ለህልውናቸው ካሏቸው ታላላቅ የተቋም አውዶች መካከል ሳይበር ግንባር ቀደም እየሆነ የመጣ ግዙፍ ምህዳር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የግንዛቤ ሥልጠናው በማዕከላዊ ዕዝ ሲሰጥ ተቋማዊ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሰራዊቱን ግንዛቤ ማሳደግ ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን የመከላከያ ሳይበር መከላከል ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ሀላፊ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ንጋቱ በቀለ ገልፀዋል።

የሳይበር ጥቃት በሀገራችን ትላልቅ ተቋማት እና ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በተደጋጋሚ ተሞክሮ ማክሸፍ መቻሉን የገለፁት ከፍተኛ መኮንኑ፤ እንደተቋም የሚፈጠሩ መሰል ድርጊቶችን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

የመከላከያ ሳይበር መከላከል ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ኤርሚያስ መለሰ በበኩላቸው፤ የሳይበር አመጣጥ እና እድገት በአለማችን ላይ እጅግ የፈጠነና የአለምን የጦርነት አውድ እየመራ እንደሚገኝ ጠቁመው  እንደኛ ሀገር ደግሞ የሰራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም በማጉደፍ በተልዕኮው ላይ ግልፀኝነት እንዳይኖረው በመፈለግ  ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው ቡድኖች እየተሰራበት ነው ብለዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማና መሃመድ አህመድ
ፎቶግራፍ አከለ አባተና መሃመድ አህመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍20🔥1
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ክፍለ-ጦር የፅንፈኛዉን ቡድን በመደምሰስ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መማረኩን አስታውቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ ቀበሌ የክፍለጦሩ ሠራዊት በወሠደው እርምጃ ቡድኑን መደምሰስና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ መማረክ መቻሉን የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ለዉጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ማሞ ተናግረዋል።

ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ  የፅንፈኛውን ቡድን 04 ክላሽ ፣  02 ቱርክ ሽጉጥ ፣  01 ኤስኬስ መሳሪያ ፣ 172 የክላሽ ጥይት ፣ እና የጭስ ቦምብ መማረኩን ምክትል አዛዡ አብራርተዋል።

እንደ ሠራዊት የሀገርና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ፅኑ አላማ ይዘን እስከተነሳን ድረስ ከዚህ እሳቤ በተቃራኒ የሚመጣን ማንኛውንም ቡድን በፅናት በመጋፈጥ ሰላምን የማስፈን ሃላፊነታችንን በብቃት ለመወጣት ምንግዜም ዝግጁ ነን ሲሉ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፈንታሁን ንጉስ
ፎቶግራፍ  ፈንታሁን ንጉስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2516👎5👏1
የተጀመሩትን በመጨረስና አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን፦

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት ከመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡  ቀደም ሲል የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር አብረሃም በላይ ከዚህ በፊት  ሲመሩት የቆዩት ተቋም የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስል እንደነበር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ 

ከመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ተቋሙን በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ የተጠሪ ክፍል የስራ ሃላፊዎች ብዙ ነገር ለመቀየር እና ተቋሙን በለውጥ ጎዳና ለማራመድ የሚተጉ አመራሮች መሆናቸውን ገልፀው ቀጣይ የተጀመሩትን ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ስራዎችን ከኢንጂነር አይሻ ጋር ሆነው እንደሚሠሩ እምነታቸውን ገልፀዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከጥቅምት 2011 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ተቋሙን በሀላፊነት የመሩ ሲሆን በቆይታቸው መከላከያ የሰላም ዘብ፤ የሃገር  ዋልታ እና ማገር በመሆኑ ይህንን ተቋም በሀላፊነት ለመምራት እድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በፊት በተቋሙ የነበራቸው ቆይታ አጭር መሆኑን አሁን ላይ በርካታ ለውጦች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጂነር አይሻ የተጀመሩትን በመጨረስ አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም እስካሁን መከላከያን በሚኒስትርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የስራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ኢንጂነር አይሻ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶ ግራፍ  ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2817