FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ለምዕራብ እና ለማዕከላዊ ዕዞች ስታፍ አባላት በሳይበር ምንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ለምዕራብ ዕዝ ስታፍ አባላት ስለ ሳይበር ምንነት፣ የሳይበር ምህዳር፣ የሳይበር ደህንነት፣የቴክኖሎጅ እድገትና የሳይበር ጥቃት፣ ስለሳይበር ጦርነት ፣ ስለሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም፣ስለ ስማርት ስልክ እና ኮምፒዩተር አጠቃቀም እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ስልጠና ሰጥተዋል።

የመከላከያ ሳይበር ኤንተለጀንት ዳይሬክተር ኮሎኔል ኢስማኤል አብደላ  የስልጠናው አላማ የዕዙ አባላት ሳይበር መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲይዙ እና በሶሻል ሚዲያ በኩል የሳይበር ተጋላጭነትን ለመከላከል ሶሻል ሚዲያን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሎኔል ኢስማኤል  ፣የራሳችንን እና የተቋሙን መልዕክት ለማይመለከተው ሰው አሳልፎ አለመስጠት፣ የፃሃፊዎችን ኮምፒውተሮች ከኢንተርኔት ውጭ ማድረግ፣ በየስራ ቦታችን በምንጠቀማቸው ዲቫይሶች ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን ስናይ ለሚመለከተው አካል መስጠት፣ ስልክ እና ኮምፒዩተር ላይ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት፣ወድቀው የተገኙ ፍላሾችንና ሃርድ ዲስኮችን አለመጠቀም ከሳይበር ጥቃት መከላከያ መንገዶች መካከል እንደሚጠቀሱ  አብራርተዋል።

የመከላከያ ሳይበር  ኦፕሬሽን ክስተት ምላሽ ሰጪ ኤክስፐርት ሻምበል ይርጋለም ሃይሉ  በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሃገራት ለህልውናቸው ካሏቸው ታላላቅ የተቋም አውዶች መካከል ሳይበር ግንባር ቀደም እየሆነ የመጣ ግዙፍ ምህዳር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የግንዛቤ ሥልጠናው በማዕከላዊ ዕዝ ሲሰጥ ተቋማዊ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሰራዊቱን ግንዛቤ ማሳደግ ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን የመከላከያ ሳይበር መከላከል ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ሀላፊ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ንጋቱ በቀለ ገልፀዋል።

የሳይበር ጥቃት በሀገራችን ትላልቅ ተቋማት እና ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በተደጋጋሚ ተሞክሮ ማክሸፍ መቻሉን የገለፁት ከፍተኛ መኮንኑ፤ እንደተቋም የሚፈጠሩ መሰል ድርጊቶችን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

የመከላከያ ሳይበር መከላከል ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ኤርሚያስ መለሰ በበኩላቸው፤ የሳይበር አመጣጥ እና እድገት በአለማችን ላይ እጅግ የፈጠነና የአለምን የጦርነት አውድ እየመራ እንደሚገኝ ጠቁመው  እንደኛ ሀገር ደግሞ የሰራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም በማጉደፍ በተልዕኮው ላይ ግልፀኝነት እንዳይኖረው በመፈለግ  ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው ቡድኖች እየተሰራበት ነው ብለዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማና መሃመድ አህመድ
ፎቶግራፍ አከለ አባተና መሃመድ አህመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍20🔥1
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ክፍለ-ጦር የፅንፈኛዉን ቡድን በመደምሰስ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መማረኩን አስታውቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ ቀበሌ የክፍለጦሩ ሠራዊት በወሠደው እርምጃ ቡድኑን መደምሰስና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ መማረክ መቻሉን የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ለዉጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ማሞ ተናግረዋል።

ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ  የፅንፈኛውን ቡድን 04 ክላሽ ፣  02 ቱርክ ሽጉጥ ፣  01 ኤስኬስ መሳሪያ ፣ 172 የክላሽ ጥይት ፣ እና የጭስ ቦምብ መማረኩን ምክትል አዛዡ አብራርተዋል።

እንደ ሠራዊት የሀገርና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ፅኑ አላማ ይዘን እስከተነሳን ድረስ ከዚህ እሳቤ በተቃራኒ የሚመጣን ማንኛውንም ቡድን በፅናት በመጋፈጥ ሰላምን የማስፈን ሃላፊነታችንን በብቃት ለመወጣት ምንግዜም ዝግጁ ነን ሲሉ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፈንታሁን ንጉስ
ፎቶግራፍ  ፈንታሁን ንጉስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2516👎5👏1
የተጀመሩትን በመጨረስና አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን፦

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት ከመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡  ቀደም ሲል የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር አብረሃም በላይ ከዚህ በፊት  ሲመሩት የቆዩት ተቋም የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስል እንደነበር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ 

ከመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ተቋሙን በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ የተጠሪ ክፍል የስራ ሃላፊዎች ብዙ ነገር ለመቀየር እና ተቋሙን በለውጥ ጎዳና ለማራመድ የሚተጉ አመራሮች መሆናቸውን ገልፀው ቀጣይ የተጀመሩትን ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ስራዎችን ከኢንጂነር አይሻ ጋር ሆነው እንደሚሠሩ እምነታቸውን ገልፀዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከጥቅምት 2011 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ተቋሙን በሀላፊነት የመሩ ሲሆን በቆይታቸው መከላከያ የሰላም ዘብ፤ የሃገር  ዋልታ እና ማገር በመሆኑ ይህንን ተቋም በሀላፊነት ለመምራት እድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በፊት በተቋሙ የነበራቸው ቆይታ አጭር መሆኑን አሁን ላይ በርካታ ለውጦች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጂነር አይሻ የተጀመሩትን በመጨረስ አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም እስካሁን መከላከያን በሚኒስትርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የስራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ኢንጂነር አይሻ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶ ግራፍ  ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2817
የማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ ።  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም 

የማዕከላዊ ዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል  ዘውዱ በላይ በአሁኑ ሰዓት ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራባቸው ዞኖች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን ታጣቂዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመደምሰስ ለህዝቦች ሰላም እና ልማት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ የማድረስ ስራ በሰፊዉ እየተሰራ መሆኑን ገለፀዋል። 

ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር  ባደረጉት ውይይት አገራችን በአሁኑ ወቅት የተያዙ የልማት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ የፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ሃይሎችን እኩይ ሴራ በማምከን ሰራዊቱ የተሠጠውን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ባለፉት ጊዜያት ወጤት ማምጣቱን ተናግረዋል።

የዕዙ ሠራዊት በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ በርካታ ድሎች አግኝቷል ፤በርካታ የሸኔ ታጣቂዎችንም ደምስሷል ጠላት ላይ ከፍተኛ ሞራላዊና ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሷልም ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ከፍተኛ አመራሮችም ሠራዊቱ በቁርጠኝነትና በጀግንነት ተልዕኮን የመወጣት ብቃቱን ወደ ላቀ ደረጃ አድርሷል ብለዋል።

ዘጋቢ ገዛኸኝ ፀጋዬ
ፎቶ ግራፍ ወርቁ አሰፋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
20👍9👏1
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል የቧንቧ ውሃ አስገንብቶ አስረከበ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ በላይ ህሩይ የአካባቢው ማህበረሰብ ከማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና መልካም ዝምድና ያለው መሆኑን ጠቁመው ሰራዊታችን ከህዝብ አብራክ የተገኝ በመሆኑ ድጋፉን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ህዝዊነቱን እያረጋገጠ የመጣና ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት ሻለቃ በላይ ህሩይ ወደፊትም  የአካባቢውን ማህበረሰብ  ችግርን የመቅረፍ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰርካማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኑርዲን አብዱራህማን የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የመከላከያ ሰራዊታችንን ህዝባዊ ባህሪ የሚያረጋግጥ ተግባር ማከናወኑን ጠቁመው ድጋፉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ትልቅ ችግር መቅረፉን ተናግረዋል፡፡

አቶ ኑርዲን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የአካባቢው ማህበረሰብ የዘመናት ችግር ሆኖ የዘለቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወሳ የሚኖር ትልቅ ታሪክ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙት የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ማዲ ሼህ አብዱላሂና ወይዘሮ ሸምሲ ኢብሮ በሰጡት አስተያየት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለበርካታ አመታት ሲደግፋቸውና ህዝባዊነቱን ሲያስመሰክር የመጣ መሆኑን አውስተው የተደረገላቸው ድጋፍም የረጅም ጊዜ ህልማቸውን ያሳካ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡  

ዘጋቢ አምታታው ከበደ
ፎቶ ግራፍ አማረች አሌና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3825👏6🔥1