FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል የቧንቧ ውሃ አስገንብቶ አስረከበ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ በላይ ህሩይ የአካባቢው ማህበረሰብ ከማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና መልካም ዝምድና ያለው መሆኑን ጠቁመው ሰራዊታችን ከህዝብ አብራክ የተገኝ በመሆኑ ድጋፉን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ህዝዊነቱን እያረጋገጠ የመጣና ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት ሻለቃ በላይ ህሩይ ወደፊትም  የአካባቢውን ማህበረሰብ  ችግርን የመቅረፍ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰርካማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኑርዲን አብዱራህማን የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የመከላከያ ሰራዊታችንን ህዝባዊ ባህሪ የሚያረጋግጥ ተግባር ማከናወኑን ጠቁመው ድጋፉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ትልቅ ችግር መቅረፉን ተናግረዋል፡፡

አቶ ኑርዲን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የአካባቢው ማህበረሰብ የዘመናት ችግር ሆኖ የዘለቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወሳ የሚኖር ትልቅ ታሪክ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙት የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ማዲ ሼህ አብዱላሂና ወይዘሮ ሸምሲ ኢብሮ በሰጡት አስተያየት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለበርካታ አመታት ሲደግፋቸውና ህዝባዊነቱን ሲያስመሰክር የመጣ መሆኑን አውስተው የተደረገላቸው ድጋፍም የረጅም ጊዜ ህልማቸውን ያሳካ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡  

ዘጋቢ አምታታው ከበደ
ፎቶ ግራፍ አማረች አሌና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3825👏6🔥1
የሴክተሩ ሁለንተናዊ ዝግጁነት በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 15 ቀን 2016
ዓ ም

የሴክተር 3 ሁለገብ ሎጀስቲክስ ሃላፊ ኮሎኔል አሠፋ አያሌው ሴክተር 3 የሁለተኛ ዙር ወትሮ ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በሁሉም ሞተራይዝድ ሻለቆች ያካሄደ መሆኑን ገልፀው በሁሉም ሞተራይዝድ ሻለቆችና በሴክተር ስታፍ ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ ሰራዊቱ ከምንጊዜውም በላይ የተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ  ኢንስፔክሽን ቡድኑ አረጋግጧል ብለዋል::

በሴክተር 3 ሰላም አስከባሪ ስር የሚገኘው  የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመሳሪያ፣ በተሽከርካሪ ፣በመኖሪያ ቤት ፣በጀኔሬተርና በመመገቢያ ዙሪያ በተደረጉ አጠቃላይ የወትሮ ዝግጁነት ማረጋገጥ ስራ ላይ እንደወትሮው ሁሉ ሠራዊቱ ዛሬም ዝግጁና የመፈፀም አቅሙን አሰጋግጦ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት ደግሞ የሴክተር 3 ኢንስፔክሽን ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ግርማ ሽብሩ ናቸው::   

የሴክተር 3 ትራንስፖርት ሃላፊ ሻለቃ ደሱ ከፈኔ በበኩላቸው ኢንስፔክሽን ቡድኑ ወትሮ ዝግጁነታችንን ማረጋገጡ ለቀጣይ ግዳጃችን የበለጠ ብቁ እንድንሆንና ጠናክረን እንድንሰራ አቅም ሆኖናል ብለዋል::

ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ ከሻለቆች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
22👍14🔥1😁1
በደቡብ ሱዳን ያምቢዩ ከዩናሚስ የመስክ ቢሮ የበላይ ሃላፊ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

በመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከል ሎጅስቲክስ መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ጠቅለው ክብረት ልዑካን ቡድኑ በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያል ስቴት የሚገኘው የኢትዮጵያ 17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ በቀጠናው ከሚገኘው የዩናሚስ የመስክ ቢሮ ጋር በጋራ የሚፈፅማቸውን ተልዕኮዎች ለማሳለጥ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ገልጸዋል።

በውይይቱም ሞተራይዝድ ሻለቃው ከዩናሚስ የመስክ ቢሮው ለተልዕኮው መሳካት አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎች እንዲያገኝ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱንም ነው ብርጋዲየር ጀኔራል ጠቅለው ክብረት የተናገሩት።

የመስክ ቢሮው የበላይ ሃላፊዋ ወይዘሮ ኮን ጄኒን በበኩላቸው ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃው በምዕራብ ኢኳቶሪያል ስቴት አስቸጋሪና ውስብስብ በሆነ መልክዓ-ምድር እና አየር ፀባይ እንዲሁም ሰፊ የግዳጅ ቀጠናን በመሸፈን የተሠጠውን ተልዕኮ በአስተማማኝ መልኩ እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሞተራይዝድ ሻለቃው የሚፈፅማቸውን ማንኛውንም ግዳጆች የተሳካ እንዲሆኑ የመስክ ቢሮው እገዛ እንደማይለየው ሃላፊዋ አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ብርጋዲየር ጀኔራል ጠቅለው ክብረት ለመስክ ቢሮው የበላይ ሃላፊ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁ ሥጦታዎችን አበርክተውላቸዋል።

ዘጋቢ አዲሱ ሙጨ
ፎቶግራፍ እፀገነት ዴቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1411👏1
ለማሰልጠኛው ማዕከል ስኬት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረትና ተነሳሽነት የማይተካ ሚና እንደነበረው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ የአመራሩ ፣ የስታፍ አባላቱና የአሰልጣኞች ተናብቦ መስራት ለላቀ ውጤት እንዳበቃቸው ገልፀዋል። 

ለተቋሙ ራዕይ መሳካት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት አዛዡ፣ በቀጣይም ሁለንተናዊ አቅማቸው የጎለበቱ የኮማንዶ አመራርና አባላትን ከማፍራት በተጨማሪ የትምህርት ቤቱን መሰረተ ልማቶችና የግብርና እንቅስቃሴውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

የማሠልጠኛ ማዕከሉ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል አለማየሁ ጨዋቃና ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ቴዎድሮስ ሀዲሽ በሰጡት አስተያየት የኮማንዶ ስልጠና ለመውሰድ መስፈርቱን ያሟሉና ፍላጎቱ ያላቸውን ወታደሮች ከመሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛዎችና ከሰራዊቱ ክፍሎች መልምለው በማስገባትና በቆይታቸውም ሙሉ አካላዊና አዕምሯአዊ ጥንካሬ ይዘው እንዲወጡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሀገራዊና አካባቢያዊ ግንዛቤያቸው የጨመረ ፣ የወታደራዊ ሳይንስ አቅማቸው የላቀ የኮማንዶ ሀይሎችን እያፈሩ እንደሚገኙም አመራሮቹ  ገልፀዋል።

የማሰልጠኛው ማህበረሰብ ያለው ቅንጅታዊ አሰራርና ተነሳሽነት ለውጤት እንዳበቃቸው የገለፁት አዛዦቹ ፤ አንጋፋው የብላቴ የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከሉ የጀግኖች ማፍሪያነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል የተጀመሩትን ሰፋፊ ስራዎች አጠናክረው ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

የማሠልጠኛ ማዕከሉ የስነልቦና ግንባታ ሀላፊ ሻለቃ ኤልያስ ቢያድግልኝ በበኩላቸው ፣ በትምህርት ቤቱ ገብተው የሚሰለጥኑ ኮማንዶዎች ሀገራዊ ፍቅርና ህብረታቸው እንዲጨምርና አካባቢያዊና አለም አቀፋዊ ዕውቀታቸው በመጨመርና የጠላትን የስነልቦና ውጊያ አስቀድመው የተረዱ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከጠንካራ የአካል ብቃት እና ወታደራዊ ቴክኒኮች የላቁ ኮማንዶዎችን ከማፍራት በተጨማሪ ጠንካራ ስነልቦናዊና አቅም እንዲኖራቸው የተለያዩ የግንባታ ማቴሪያሎችን በመጠቀም ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩም እንደሚገኙ የስነልቦና ግንባታ ሀላፊው ጠቁመዋል።

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በቅርቡ 42ኛ ዙር የኮማንዶ አባላትን ያስመረቀ ሲሆን የአመራር ትምህርት ቤቱ እያሰለጠናቸው የሚገኙ ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞችን በቅርቡ ያስመርቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍14👏3🔥1