የተጀመሩትን በመጨረስና አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን፦
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት ከመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡ ቀደም ሲል የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር አብረሃም በላይ ከዚህ በፊት ሲመሩት የቆዩት ተቋም የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስል እንደነበር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ተቋሙን በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ የተጠሪ ክፍል የስራ ሃላፊዎች ብዙ ነገር ለመቀየር እና ተቋሙን በለውጥ ጎዳና ለማራመድ የሚተጉ አመራሮች መሆናቸውን ገልፀው ቀጣይ የተጀመሩትን ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ስራዎችን ከኢንጂነር አይሻ ጋር ሆነው እንደሚሠሩ እምነታቸውን ገልፀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከጥቅምት 2011 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ተቋሙን በሀላፊነት የመሩ ሲሆን በቆይታቸው መከላከያ የሰላም ዘብ፤ የሃገር ዋልታ እና ማገር በመሆኑ ይህንን ተቋም በሀላፊነት ለመምራት እድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ በፊት በተቋሙ የነበራቸው ቆይታ አጭር መሆኑን አሁን ላይ በርካታ ለውጦች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጂነር አይሻ የተጀመሩትን በመጨረስ አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር ለውጡን በጋራ እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም እስካሁን መከላከያን በሚኒስትርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር አብረሃም በላይ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የስራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ኢንጂነር አይሻ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶ ግራፍ ድምሩ ህሩይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
👍28❤17
የማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የማዕከላዊ ዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በአሁኑ ሰዓት ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራባቸው ዞኖች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን ታጣቂዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመደምሰስ ለህዝቦች ሰላም እና ልማት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ የማድረስ ስራ በሰፊዉ እየተሰራ መሆኑን ገለፀዋል።
ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት አገራችን በአሁኑ ወቅት የተያዙ የልማት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ የፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ሃይሎችን እኩይ ሴራ በማምከን ሰራዊቱ የተሠጠውን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ባለፉት ጊዜያት ወጤት ማምጣቱን ተናግረዋል።
የዕዙ ሠራዊት በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ በርካታ ድሎች አግኝቷል ፤በርካታ የሸኔ ታጣቂዎችንም ደምስሷል ጠላት ላይ ከፍተኛ ሞራላዊና ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሷልም ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ከፍተኛ አመራሮችም ሠራዊቱ በቁርጠኝነትና በጀግንነት ተልዕኮን የመወጣት ብቃቱን ወደ ላቀ ደረጃ አድርሷል ብለዋል።
ዘጋቢ ገዛኸኝ ፀጋዬ
ፎቶ ግራፍ ወርቁ አሰፋ

❤20👍9👏1
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል የቧንቧ ውሃ አስገንብቶ አስረከበ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ በላይ ህሩይ የአካባቢው ማህበረሰብ ከማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና መልካም ዝምድና ያለው መሆኑን ጠቁመው ሰራዊታችን ከህዝብ አብራክ የተገኝ በመሆኑ ድጋፉን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ህዝዊነቱን እያረጋገጠ የመጣና ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት ሻለቃ በላይ ህሩይ ወደፊትም የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግርን የመቅረፍ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሰርካማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኑርዲን አብዱራህማን የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የመከላከያ ሰራዊታችንን ህዝባዊ ባህሪ የሚያረጋግጥ ተግባር ማከናወኑን ጠቁመው ድጋፉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ትልቅ ችግር መቅረፉን ተናግረዋል፡፡
አቶ ኑርዲን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የአካባቢው ማህበረሰብ የዘመናት ችግር ሆኖ የዘለቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወሳ የሚኖር ትልቅ ታሪክ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙት የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ማዲ ሼህ አብዱላሂና ወይዘሮ ሸምሲ ኢብሮ በሰጡት አስተያየት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለበርካታ አመታት ሲደግፋቸውና ህዝባዊነቱን ሲያስመሰክር የመጣ መሆኑን አውስተው የተደረገላቸው ድጋፍም የረጅም ጊዜ ህልማቸውን ያሳካ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ አምታታው ከበደ
ፎቶ ግራፍ አማረች አሌና

👍38❤25👏6🔥1
የሴክተሩ ሁለንተናዊ ዝግጁነት በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 15 ቀን 2016
ዓ ም
የሴክተር 3 ሁለገብ ሎጀስቲክስ ሃላፊ ኮሎኔል አሠፋ አያሌው ሴክተር 3 የሁለተኛ ዙር ወትሮ ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በሁሉም ሞተራይዝድ ሻለቆች ያካሄደ መሆኑን ገልፀው በሁሉም ሞተራይዝድ ሻለቆችና በሴክተር ስታፍ ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ ሰራዊቱ ከምንጊዜውም በላይ የተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ኢንስፔክሽን ቡድኑ አረጋግጧል ብለዋል::
በሴክተር 3 ሰላም አስከባሪ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመሳሪያ፣ በተሽከርካሪ ፣በመኖሪያ ቤት ፣በጀኔሬተርና በመመገቢያ ዙሪያ በተደረጉ አጠቃላይ የወትሮ ዝግጁነት ማረጋገጥ ስራ ላይ እንደወትሮው ሁሉ ሠራዊቱ ዛሬም ዝግጁና የመፈፀም አቅሙን አሰጋግጦ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት ደግሞ የሴክተር 3 ኢንስፔክሽን ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ግርማ ሽብሩ ናቸው::
የሴክተር 3 ትራንስፖርት ሃላፊ ሻለቃ ደሱ ከፈኔ በበኩላቸው ኢንስፔክሽን ቡድኑ ወትሮ ዝግጁነታችንን ማረጋገጡ ለቀጣይ ግዳጃችን የበለጠ ብቁ እንድንሆንና ጠናክረን እንድንሰራ አቅም ሆኖናል ብለዋል::
ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ ከሻለቆች

❤22👍14🔥1😁1