FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሜንቴናንስ መምሪያ የተሸከርካሪ መካኒኮችን አሰልጥኖ አስመረቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሜንቴናንስ መምሪያ በአውቶ መካኒክ፤በአውቶ ኤሌክትሪሻን፤ በፓምፕና ጄነሬተር ጥገና እንዲሁም በብየዳ ሙያ ያሠለጠናቸውን አባላት ፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሃላፊ ኮሎኔል ሙሉጌታ ንጉሴ የሜንቴናንስ መምሪያ ሰራዊቱ ባለበት ጫፍ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ የመፈፀም ብቃቱ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

መምሪያው ከስራ ውጭ የሆኑ ተሸከርካሪ እና ማሽነሪዎችን በፍጥነት ጠግኖ ወደ አገልግሎት እየመለሰ ያለው ተግባር የሚበረታታ እንደሆነ የጠቆሙት ሃላፊው ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ሙያተኞችን በራስ አቅም አሰልጥኖ ማብቃቱ ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት በሜንቴናንስ መምሪያ የተሸከሪካሪ ቡድን መሪ የሆኑት ሻለቃ መሀመድ ሲራጅ ስልጠናው በተመደበው ፕሮግራም መሰረት በቴዮሪ እና በተግባር ልምድ ባላቸው ሙያተኞች ለአራት ወራት እንደተሰጠ ገልፀዋል፡፡ 

ዘጋቢ ጌታሠው ጌትነት
ፎቶግራፍ ታሪኳ ብርሃኑ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
14👍9👏3🔥1
የአየር ኃይል ሴት የሠራዊት አባላት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጡ ሰልጣኝ ሴት የአቭዬሽን ሙያተኞች ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

የአየር ኃይል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮሎኔል ሀገሬ ዘመነ በተሞክሮ ልውውጥ መድረኩ ላይ ሴቶች በውትድርናው መስክ ሀገራቸውን ለማገልገል ቆርጠው የተነሱ መሆናቸውን ገልፀው የኃላፊነት ክብደቱ ይበልጥ እንደሚጎላ ጠቁመዋል።

የአዲሱ ትውልድ ሴት የሰራዊት አባላት እንዲሁም የአየር መንገድ ሴት የአቭዬሽን ሙያተኞች  የቀደምት ሴት ጀግኖችን አርማ በማንገብ ተልዕኳቸውን ፍፁም በሆነ ሀገራዊ ፍቅርና ታማኝነት ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በአየር ኃይል ጤና መምሪያ የሎጅስቲክስ ኃላፊ ኮሎኔል ቸኮለች ወንዳቸው ከ33 ዓመት በላይ በዘለቀ የውትድርና ህይወታቸው በርካታ መሰናክሎችን እንዳለፉና በአላማ ቁርጠኝነት ለዛሬው አመራር ደረጃ እንደበቁ አውሰተው አሁን በየተቋማቱ ሀገር ለማገልገል የመጣችሁ ወጣት ሴቶችም ለሚገጥሟችሁ ፈተና እጅ ሳትሰጡ ነገን በማሰብ በየተሰማራችሁበት ብቁ ሆናችሁ ሃላፊነታችሁን መውጣት አለባችሁ ብለዋል ።

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ቆይታቸው ውትድርና ስለሀገር ሲባል መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ክቡር ሙያ መሆኑን መገንዘባቸውንና በተለይም ከራስ ይልቅ ለሀገር ቅድሚያ ስለመስጠት በሁሉም የሰራዊት አባላት ዘንድ እንደመርህ  መያዙ ለአነሱም ትልቅ የስነ ልቦና መነቃቃት አንደሆነ የገለፁት ሰልጣኝ የአየር መንገድ አባላት ወጣት አፀደ ገነነ ናቸው።

በዕለቱ የሁለተኛ ዓመት ትምህርታቸውን በከፍተኛ ውጤት ላጠናቀቁ የአየር ኃይል አካዳሚ ሴት ተማሪዎች እና በስልጠና ወቅት ጠንካራ ለሆኑ የአየር መንገድ ሰልጣኝ ሴት የአቭዬሽን ሙያተኞች በአየር ኃይል ሴቶች ጉዳይ የተዘጋጀውን የማበረታቻ ምስክር ወረቀት የአየር ኃይል ስነ ልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ተሾመ በዳዳ አበርክተዋል።

ዘጋቢ ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ ገነት ካሳዬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
12👍6🔥3👏1
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር  ሀይልን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ ም

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል   ቡልቲ ታደሰን ጨምሮ የኮሌጁ አመራር እና አባላት እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር ሀይል ያደረጉት ጉብኝት ደስታ አንደፈጠረላቸውና ስለተቋሙም በርካታ መረጃ እንዳገኙ ገልፀዋል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተመራቂ የመደበኛ ኮርስ ተማሪዎች በበኩላቸው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ እና  የኢትዮጵያ አየር ሀይል የአፍሪካ ኩራት መሆናቸውን ጠቅሰው አፍሪካውያን ያለንን ፀጋ በጋራ ከተጠቀምን አለም የደረሰበት የአድገት ጎዳና መድረስ አንደምንችል  ማሳያ ነው ብለዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ ስትራቴጂክ ወታደራዊና ሲቪል የፀጥታ አመራሮችን በአጭርና በመደበኛ ኮርስ አስተምሮ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፣፣

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1810🔥2👏2😁2
አንጋፋው ክለብ መቻል "መቻል ለ ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል 80ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓሉን እያከበረ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በ1936 ዓ.ም የተመሠረተው እና ሀገራቸውን ወክለው በተለያዩ የአለም ሀገራት መወዳደር የቻሉ ብርቅዬ ጀግና አትሌቶችን እግር ኳስ ተጫዎቾችን እና ሌሎች ስፖርተኞችን ማፍራት የቻለ የማይረሳ ታሪክ ያለው አንጋፋ ክለብ ነው መቻል።

ለሠማንያ ዓመታት አንጋፋንቱን አሥጠብቆ የዘለቀ በየጊዜው ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ሠሪዎችን በታሪክ ማህደር አሥፍሮ ዛሬም በሀገራችን የስፖርት ዘርፍ የበኩሉን አሻራ እያሳረፈ ነው።

አትሌት አበበ ቢቂላ ፣ማሞ ወልዴ ፣ምሩፅ ይፍጠር ፣ሌሊሳ ፈይሳ ፣ ፣አልማዝ አያና፣ ደረሠ መኮነን፣ ሙክታር እንድሪስ፣ ኢብራሂም ጀይላን፣ ቲኪ ገላና፣ፀጋዬ ከበደ፣ ድሪባ መርጊያ፣ አሊ አብዱሽ ፣ወርቅውሃ ጌታቸው ፣ጌታነህ ሞላ እና ሌሎችንም አትሌቶችን ያፈራ ክለብ ነው መቻል።

በሁሉም የስፖርት ዘርፍ ለሀገራችን አሻራቸውን አሣርፈው ያለፉ ስፖርተኞችን ያፈራው መቻል አሁን ላይም ሥፖርተኞችን በማሠልጠን የክለቡን ታሪክ የሚያገዝፉ  የሀገራቸውን የሥፖርት ዕድገት የሚያሥቀጥሉ በአለም አደባባይ ሠንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ብርቅዬዎችን ይዞ ቀጥሏል።

ይህ አንጋፋና የሀገር ባለውለታ የሆነው ክለብ 80ኛ አመቱን የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል ታዲያ መቻል ማለት ሀገር ነውና እርስዎም የበኩልዎን ድጋፍ እያደረጉ ማሊያ ኮፊያ ሌሎችንም የተዘጋጁ ለሽያጭ የቀረቡ ቁሶችን በመግዛት ሀገርዎን ይደግፉ መቻል ማለት ሀገር ነው።

በውብሸት ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍159🏆3👎2🔥2🤮1