FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር  ሀይልን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ ም

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል   ቡልቲ ታደሰን ጨምሮ የኮሌጁ አመራር እና አባላት እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር ሀይል ያደረጉት ጉብኝት ደስታ አንደፈጠረላቸውና ስለተቋሙም በርካታ መረጃ እንዳገኙ ገልፀዋል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተመራቂ የመደበኛ ኮርስ ተማሪዎች በበኩላቸው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ እና  የኢትዮጵያ አየር ሀይል የአፍሪካ ኩራት መሆናቸውን ጠቅሰው አፍሪካውያን ያለንን ፀጋ በጋራ ከተጠቀምን አለም የደረሰበት የአድገት ጎዳና መድረስ አንደምንችል  ማሳያ ነው ብለዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ ስትራቴጂክ ወታደራዊና ሲቪል የፀጥታ አመራሮችን በአጭርና በመደበኛ ኮርስ አስተምሮ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፣፣

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1810🔥2👏2😁2
አንጋፋው ክለብ መቻል "መቻል ለ ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል 80ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓሉን እያከበረ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በ1936 ዓ.ም የተመሠረተው እና ሀገራቸውን ወክለው በተለያዩ የአለም ሀገራት መወዳደር የቻሉ ብርቅዬ ጀግና አትሌቶችን እግር ኳስ ተጫዎቾችን እና ሌሎች ስፖርተኞችን ማፍራት የቻለ የማይረሳ ታሪክ ያለው አንጋፋ ክለብ ነው መቻል።

ለሠማንያ ዓመታት አንጋፋንቱን አሥጠብቆ የዘለቀ በየጊዜው ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ሠሪዎችን በታሪክ ማህደር አሥፍሮ ዛሬም በሀገራችን የስፖርት ዘርፍ የበኩሉን አሻራ እያሳረፈ ነው።

አትሌት አበበ ቢቂላ ፣ማሞ ወልዴ ፣ምሩፅ ይፍጠር ፣ሌሊሳ ፈይሳ ፣ ፣አልማዝ አያና፣ ደረሠ መኮነን፣ ሙክታር እንድሪስ፣ ኢብራሂም ጀይላን፣ ቲኪ ገላና፣ፀጋዬ ከበደ፣ ድሪባ መርጊያ፣ አሊ አብዱሽ ፣ወርቅውሃ ጌታቸው ፣ጌታነህ ሞላ እና ሌሎችንም አትሌቶችን ያፈራ ክለብ ነው መቻል።

በሁሉም የስፖርት ዘርፍ ለሀገራችን አሻራቸውን አሣርፈው ያለፉ ስፖርተኞችን ያፈራው መቻል አሁን ላይም ሥፖርተኞችን በማሠልጠን የክለቡን ታሪክ የሚያገዝፉ  የሀገራቸውን የሥፖርት ዕድገት የሚያሥቀጥሉ በአለም አደባባይ ሠንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ብርቅዬዎችን ይዞ ቀጥሏል።

ይህ አንጋፋና የሀገር ባለውለታ የሆነው ክለብ 80ኛ አመቱን የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል ታዲያ መቻል ማለት ሀገር ነውና እርስዎም የበኩልዎን ድጋፍ እያደረጉ ማሊያ ኮፊያ ሌሎችንም የተዘጋጁ ለሽያጭ የቀረቡ ቁሶችን በመግዛት ሀገርዎን ይደግፉ መቻል ማለት ሀገር ነው።

በውብሸት ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍159🏆3👎2🔥2🤮1
የፅንፈኛውን ቡድን ዕኩይ ሴራ በማጋለጥ ህግ የማስከበሩ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
 
በአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት አስተባባሪና በምዕራብ ዕዝ የአንድ ኮር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዘዘው መኮንን በዞኑ ውስጥ ሠላምና ፀጥታን በማስፈን የአከባቢውን ደህንነት ከማረጋገጥ አንፃር ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።

ሠራዊቱ ከተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች በሸበል ፣በቦቅላ፣ በአነደድና በባሶሊበን ወረዳዎች ስር ባሉ አስር ቀበሌዎች በጥፋት ተግባር ሲንቀሳቀስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን ፈልጎ ለመደምሰስ በወሰደው እርምጃ 65 የጠላትን ሃይል በመደምሰስና 74 የሚሆኑትን ቁስለኛ በማድረግ ከ15 በላይ የአውቶማቲክና የኋላ ቀር መሳሪያዎችን ከተለያዩ አይነት ተተኳሾች ጋር መማረኩን ገልፀዋል።

የፀረ-ሰላም ሃይሉ ከህብረተሰቡና ከመንግስት ተቋማት ዘርፎ ለረጅም ጊዜ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ከአስራ ዘጠኝ በላይ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ፣ስምንት መኪኖች ፣ስድስት ሞተር ሳይክልና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከእህል ምርት ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ጠቅሰዋል።

በተያያዘ በብቸና ከተማ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በሁለት ማተሚያ ቤቶች ውስጥ ፅንፈኛው ሊጠቀምባቸው የተዘጋጁ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ደረሰኝና የተለያዩ የቀበሌ እና የሌሎች መስሪያ ቤቶች ማህተሞችና አልባሳት መያዛቸውን ተናግረዋል።

በጥቂት የጥፋት ሃይሎች የሀገርና የህዝብ ሠላም ሊናጋ አይገባም ያሉት ኮሎኔል አይቸው ግለጠውና ኮሎኔል ሸዋነህ ገበየው ህግን በመጣስ ለጥፋት ተግባር በተሰማራው ሃይል ላይ እየተወሰደ ባለው ተከታታይ እርምጃ በዞኑ አንፃራዊ ሰላምን መፈጠሩን ገልፀዋል።

ዘጋቢ አብዲ ሁሴን
ፎቶግራፍ አብዲ ሁሴን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍335👏5😁2🏆2🔥1
የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የተቋሙን የ10 ዓመት የዲጂታል ለውጥ እውን ማድረግ የሚያስችል ወር ሾፕ አካሄደ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በወርክሾፑ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስኪያጅ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስተር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ጀነራል መኮንኖችና ባለድርሻ አካላትና መምሪያ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የዕዝና የክፍል አመራሮችም በቪዲዮ ኮንፈረንስ በቀጥታ ተሳትፈዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ መከላከያ ተቋም በሀገር የሚመሰል በመሆኑ  የዲጂታል ለውጡን ተቀብለን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ማዕከሉን መደገፍና ሚስጥራዊነቱንም ማረጋገጥ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው የመከላከያ ተቋም ዲጂታል ለውጥን እንዲላበስና የራሱ የግል ኔትወርክ ኖሮት ደኅንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥና የስራ ቅልጥፍና እንዲኖር ለማድረግ የዳሰሳ ጥናት ተደርጎ ወደስራ መገባቱን ገልፀዋል። በቀጣይም ከመከላከያ  ጋር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ፣ የመረጃና የግንኙነት ሥርዓቱን በማዘመን የተያዘውን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ለማሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተጀመረው ሥራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በወርክ ሾፑ የተሳተፍ አመራርና አባላትም ዲጂታል ለውጡን ለማሳካት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ሜሮን ጌታነህ
ፎቶግራፍ ምስጋናው ከበደ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍234👏3🔥1