FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

"የተዋጊ ኃይላችን የውጊያ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ በማድረግ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ መሀንዲስ ተልዕኮውን በሚገባ ተወጥቷል።"  የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ብ/ጀኔራል ደረጄ መገርሳ

የምዕራብ ዕዝ መሀንዲስ መምሪያ በስሩ የሚገኙ የተዋጊ መሃንዲስ አባላትን ለሁለት ወር አሰልጥኖ አስመርቋል።

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ ንግግር የደረጉት የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ብ/ጀኔራል ደረጄ መገርሳ እንደተናገሩት በህልውና ዘመቻ ወቅት አሸባሪው የህውሃት ቡድን ፈንጂዎችን በማጥመድ የወገን እንቅስቃሴን ለመገደብ ጥረት ቢያደርግም የዕዙ ተዋጊ መሃንዲሶች ወጥመዱን በማክሸፍ ሠራዊቱ ወደ ፊት እንዲገሰግስ እና ግዳጁን በድል እንዲወጣ ከፍተኛ አስተዋፆ ነበራቸው።

የምዕራብ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ ያሉትን አቅሞች በመጠቀም የተዋጊ ኃይላችን የውጊያ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ የመሃንዲስ ተግባራትን አከናውኗል ያሉት ጀነራል መኮንኑ የውሃ አቅርቦት እና የዳቦ ማሽን የጀኔሬተር ተከላ ስራን  በመስራት የሠራዊቱ ማህበራዊ ኑሮ የተሟላ እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ ስራ ሠርቷል ብለዋል።

ጀነራል መኮንኑ አክለውም የተዋጊ መሃንዲስ አባላት በተደረጉ ዘመቻዎች ሁሉ ያሳያችሁትን ጥንካሬ ከወሰዳችሁት ስልጠና ጋር በማዛመድ  ለበለጠ ተልዕኮ መዘጋጀት ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የስልጠናው አስተባባሪ  ሻ/ል አበበ የሺጥላ በበኩላቸው ህግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የተዋጊ መሃንዲስ ሙያተኞችን በተከታታይ አሰልጥነው ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ተመራቂ  ሙያተኞች ተገቢውን የተዋጊ መሃንዲስ እውቀት በንድፈ ሀሳብና በተግባር የጨበጡ መሆናቸውንም ገልፀው በስልጠና ቆይታቸው በሰባት ወታደራዊ የትምህርት አይነቶች ሰልጥነው መመረቃቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ አባላት መካከል ሃምሳ አለቃ ዳንኤል ምህረቱ እና መሰረታዊ ወታደር ሶፊያ ሀሰን በሰጡት ተመሳሳይ አስተያዬት ስልጠናው ተጨማሪ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀው ለሚሰጠን ማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ ነን ብለዋል።

ፍፁም ከተማ
ፎቶግራፍ ፍፁም ከተማ

ለተጨማሪ መረጃዎች  ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

               ቴሌግራም  👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

                   ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍185👏1
ሚያዚያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አቅመ-ደካሞችን፣ ተፈናቃዮችን የሚደግፍ እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ያለው መሆኑን የሶማልያ ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ገለፁ።

በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) ግዳጅ ተቀብሎ ቡርድቦና አካባቢው የሰላም ማስከበር ተልኮውን እየፈፀመ የሚገኘው የኢትዮጵያ 33ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለሶማልያ ብሄራዊ ጦር (SNA) ለምግብ ፍጆታ የሚውል ድጋፍ አድርጓል።

የ33ው ሞተራይዝድ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሻለቃ ገረመው ሙሉነህ እንደተናገሩት በድጋፉ የተበረከተው 33 ካርቶን ጁስ እና 3 ካርቶን ቴምር ሲሆን የድጋፋም አላማ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ግዳጅ ለሚያግዙን የሶማልያ ብሄራዊ ጦር የረመዳን ፆምን እንዲያፈጥሩ እና ያለንን ክብር ለመግለፅ ነው።

ከፍተኛ መኮንኑ አክለውም የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ግዳጅ በምንፈፅምበት እና የፀጥታ ስራዎችን በምናከናውንበት ወቅት መረጃ በመስጠትና አብረው በመስራት ያሳዩት ታማኝነትና ቅንነት የሚያስመሠግን በመሆኑ እኛም ካለን ላይ በማካፋል ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

የቡርድቦ ወረዳ ምክትል አስተዳደር አቶ ሽንብሮ ሁሴን እና በአካባቢው የሚገኘው የሶማልያ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ሻምበል አብዱራህማን አሊ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ወገንተኝነት ያለው፣ አቅመ-ደካሞች እና ተፈናቃዮችን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰራዊት ነው።

ኃላፊዎቹ በአካባቢው ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረጉ የህግ ማስከበር ተግባሮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁ ሲሆን ለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

ዳምጤ ማናዬ
ፍቶግራፍ ከግዳጅ ቀጠናው

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍121
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያ የሚገኘው የ15ኛ ሞተራዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ የሌቭል አንድ ሆስፒታል በሽታን ለመከላከል ባከናወናቸው ስራዎች ስኬት ማስመዝገቡ ተገለፀ።

ሠራዊቱ ጤንነቱ የተጠበቀና አካላዊ ብቃቱ የተረጋገጠ እንዲሆን ከዩናሚስስ የሚሰጡትን ማናቸውንም ግዳጆች በጀግንነትና በብቃት እንዲፈፅም ለማስቻል ተከታታይነት ያለው የበሽታ መከላከል ስራ መሠራቱን እና የጤና ትምህርቶች መሠጠታቸውን የሌቭል አንድ ሆስፒታል ሜዲካል ኦፊሰር ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር ገልፀዋል።

ሠራዊቱ የተለያዩ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ወታደራዊ ታዛቢዎችን አጅቦ ረጅም ርቀት በሚጓዝበት ወቅትም የህክምና ባለሙያዋች አብረው ተንቀሳቅሰው ሙያዊ አገልግሎት እንደሚሰጡ ሜዲካል ኦፊሰሩ ተናግረዋል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙትን የህብረተሠብ ክፍሎች ለኮቪድ-19 በሽታ እንዳይጋለጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችና በሽታውን ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር በጁባ የስደተኞች መጠለያ እና ያምቢዮ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር የፅዳት ዘመቻ ስራዎች በጋራ ተሰርቷል ብለዋል።

በሆስፒታሉ የሚገኙ የህክምና መስጫ መገልገያ ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች በአግባቡ በመያዛቸው በዩናሚስስ ኢንስፔክሽን ቡድን በተደረገው የወትሮ ዝግጅነት ፍተሻ ጥሩ ውጤት መገኘቱንም ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ ባልደረባ ሻምበል ዶክተር አይናለም በላይ እና መቶ አለቃ ነርስ ፈዬ ቢቂላ በበኩላቸው ሠራዊቱ  የሚሠጠውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ የህክምና አባላቱ ሙያዊ ግዴታቸውን በቁርጠኝነት እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ በመድኃኒት ቤት፣ በላብራቶሪ እንዲሁም በቀላል ቀዶ ጥገና የተደራጀ ሲሆን ለተመላላሽ እና ተኝተው ለሚታከሙ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መሆኑም ተገልጿል።

ታደሠ ታምራት
ፍቶግራፍ ሠለሞን ጌታቸው

ለተጨማሪ መረጃዎች  ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

               ቴሌግራም  👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

                   ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

"በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ በመረጃ ኮሌጅ የሚማሩ እጩ መኮንኖች የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ተልዕኳቸውን በቁርጠኝነት ሊወጡ ይገባል።" ሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ

በሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ የተመራው ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች በመከላከያ ስልጠና ዋና መምሪያ የሚገኘውን የመረጃ ትምህርት ኮሌጅ ጎብኝተዋል።

የመረጃ ኮሌጁ እጩ መኮንኖችን በማስተማር የሀገርንና የተቋሙን ደህንነት የሚጠብቁ የመረጃ ሙያተኞችን እያፈራ የሚገኝ ሲሆን ኮሌጁ በማስተማር የደረሰበት ደረጃ ለጎብኚዎች ገለፃ ተደርጓል።

በጉብኝቱ ወቅት ሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ የመረጃ ኮሌጁን ለማጠናከር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ወደፊትም የመማር ማስተማር አቅሙን የበለጠ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል።

ጀኔራል መኮንኑ በመረጃ ኮሌጅ በመሠልጠን ላይ ላሉ እጩ መኮንኖች እንደተናገሩት የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ የሚማሩትን ወታደራዊ ስልጠና በቁርጠኝነት ሊወጡ ይገባል። የሚሰጣችሁን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁ መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡

ብ/ጀኔራል ደርቤ መኩሪያ በበኩላቸው የኮሌጁን አደረጃጀት እና ካሪኩለም ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር ለማዛመድ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ያሉ ሲሆን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችም ብቃት እና ዲስፒሊን ያለው ሙያተኛ መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡

የመረጃ ኮሌጁ አዛዥ ኮ/ል አባቡ ተሾመ ለጉብኝት ተሳታፊዎቹ እንደገለፁት በትምህርት ቤቱ ያሉ የመረጃ ተማሪዎች ለሚሰጣቸው ማንኛውም ግዳጅ ራሳቸውን በሙያው እያበቁ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ለኮሌጁ መሟላት ስለሚገባችው ነገሮችም አብራርተዋል፡፡

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የቴክኖሎጂ መረጃ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም ሀገር እና ተቋሙን ከማንኛውም አደጋ የመከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

ትግስት ምትኩ
ፎቶግራፍ ትግስት ምትኩ

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍4