FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሚያዚያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አቅመ-ደካሞችን፣ ተፈናቃዮችን የሚደግፍ እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ያለው መሆኑን የሶማልያ ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ገለፁ።

በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) ግዳጅ ተቀብሎ ቡርድቦና አካባቢው የሰላም ማስከበር ተልኮውን እየፈፀመ የሚገኘው የኢትዮጵያ 33ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለሶማልያ ብሄራዊ ጦር (SNA) ለምግብ ፍጆታ የሚውል ድጋፍ አድርጓል።

የ33ው ሞተራይዝድ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሻለቃ ገረመው ሙሉነህ እንደተናገሩት በድጋፉ የተበረከተው 33 ካርቶን ጁስ እና 3 ካርቶን ቴምር ሲሆን የድጋፋም አላማ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ግዳጅ ለሚያግዙን የሶማልያ ብሄራዊ ጦር የረመዳን ፆምን እንዲያፈጥሩ እና ያለንን ክብር ለመግለፅ ነው።

ከፍተኛ መኮንኑ አክለውም የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ግዳጅ በምንፈፅምበት እና የፀጥታ ስራዎችን በምናከናውንበት ወቅት መረጃ በመስጠትና አብረው በመስራት ያሳዩት ታማኝነትና ቅንነት የሚያስመሠግን በመሆኑ እኛም ካለን ላይ በማካፋል ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

የቡርድቦ ወረዳ ምክትል አስተዳደር አቶ ሽንብሮ ሁሴን እና በአካባቢው የሚገኘው የሶማልያ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ሻምበል አብዱራህማን አሊ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ወገንተኝነት ያለው፣ አቅመ-ደካሞች እና ተፈናቃዮችን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰራዊት ነው።

ኃላፊዎቹ በአካባቢው ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረጉ የህግ ማስከበር ተግባሮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁ ሲሆን ለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

ዳምጤ ማናዬ
ፍቶግራፍ ከግዳጅ ቀጠናው

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍121
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያ የሚገኘው የ15ኛ ሞተራዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ የሌቭል አንድ ሆስፒታል በሽታን ለመከላከል ባከናወናቸው ስራዎች ስኬት ማስመዝገቡ ተገለፀ።

ሠራዊቱ ጤንነቱ የተጠበቀና አካላዊ ብቃቱ የተረጋገጠ እንዲሆን ከዩናሚስስ የሚሰጡትን ማናቸውንም ግዳጆች በጀግንነትና በብቃት እንዲፈፅም ለማስቻል ተከታታይነት ያለው የበሽታ መከላከል ስራ መሠራቱን እና የጤና ትምህርቶች መሠጠታቸውን የሌቭል አንድ ሆስፒታል ሜዲካል ኦፊሰር ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር ገልፀዋል።

ሠራዊቱ የተለያዩ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ወታደራዊ ታዛቢዎችን አጅቦ ረጅም ርቀት በሚጓዝበት ወቅትም የህክምና ባለሙያዋች አብረው ተንቀሳቅሰው ሙያዊ አገልግሎት እንደሚሰጡ ሜዲካል ኦፊሰሩ ተናግረዋል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙትን የህብረተሠብ ክፍሎች ለኮቪድ-19 በሽታ እንዳይጋለጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችና በሽታውን ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር በጁባ የስደተኞች መጠለያ እና ያምቢዮ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር የፅዳት ዘመቻ ስራዎች በጋራ ተሰርቷል ብለዋል።

በሆስፒታሉ የሚገኙ የህክምና መስጫ መገልገያ ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች በአግባቡ በመያዛቸው በዩናሚስስ ኢንስፔክሽን ቡድን በተደረገው የወትሮ ዝግጅነት ፍተሻ ጥሩ ውጤት መገኘቱንም ሻለቃ ዶክተር ሃይሉ ቢሰውር ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ ባልደረባ ሻምበል ዶክተር አይናለም በላይ እና መቶ አለቃ ነርስ ፈዬ ቢቂላ በበኩላቸው ሠራዊቱ  የሚሠጠውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ የህክምና አባላቱ ሙያዊ ግዴታቸውን በቁርጠኝነት እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ በመድኃኒት ቤት፣ በላብራቶሪ እንዲሁም በቀላል ቀዶ ጥገና የተደራጀ ሲሆን ለተመላላሽ እና ተኝተው ለሚታከሙ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መሆኑም ተገልጿል።

ታደሠ ታምራት
ፍቶግራፍ ሠለሞን ጌታቸው

ለተጨማሪ መረጃዎች  ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

               ቴሌግራም  👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

                   ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

"በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ በመረጃ ኮሌጅ የሚማሩ እጩ መኮንኖች የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ተልዕኳቸውን በቁርጠኝነት ሊወጡ ይገባል።" ሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ

በሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ የተመራው ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች በመከላከያ ስልጠና ዋና መምሪያ የሚገኘውን የመረጃ ትምህርት ኮሌጅ ጎብኝተዋል።

የመረጃ ኮሌጁ እጩ መኮንኖችን በማስተማር የሀገርንና የተቋሙን ደህንነት የሚጠብቁ የመረጃ ሙያተኞችን እያፈራ የሚገኝ ሲሆን ኮሌጁ በማስተማር የደረሰበት ደረጃ ለጎብኚዎች ገለፃ ተደርጓል።

በጉብኝቱ ወቅት ሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ የመረጃ ኮሌጁን ለማጠናከር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ወደፊትም የመማር ማስተማር አቅሙን የበለጠ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል።

ጀኔራል መኮንኑ በመረጃ ኮሌጅ በመሠልጠን ላይ ላሉ እጩ መኮንኖች እንደተናገሩት የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ የሚማሩትን ወታደራዊ ስልጠና በቁርጠኝነት ሊወጡ ይገባል። የሚሰጣችሁን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁ መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡

ብ/ጀኔራል ደርቤ መኩሪያ በበኩላቸው የኮሌጁን አደረጃጀት እና ካሪኩለም ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር ለማዛመድ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ያሉ ሲሆን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችም ብቃት እና ዲስፒሊን ያለው ሙያተኛ መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡

የመረጃ ኮሌጁ አዛዥ ኮ/ል አባቡ ተሾመ ለጉብኝት ተሳታፊዎቹ እንደገለፁት በትምህርት ቤቱ ያሉ የመረጃ ተማሪዎች ለሚሰጣቸው ማንኛውም ግዳጅ ራሳቸውን በሙያው እያበቁ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ለኮሌጁ መሟላት ስለሚገባችው ነገሮችም አብራርተዋል፡፡

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የቴክኖሎጂ መረጃ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም ሀገር እና ተቋሙን ከማንኛውም አደጋ የመከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

ትግስት ምትኩ
ፎቶግራፍ ትግስት ምትኩ

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍4
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የደረሰችው በየዘመናቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በድል እየተሻገረች ነው። እንድትጠፋ የሚፈልጉ ኃይሎች ሊያጠፏት ሲነሡ ምንጊዜም ሦስት ኃይሎችን እንደሚጠቀሙ እሙን ነው።

የመጀመሪያዎቹ ምንጊዜም የማይተኙት ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው። እነዚህ ጠላቶቻችን ጠላትነታቸውን የሚያቆሙት ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር ከምድር ገጽ ስትጠፋ ብቻ ነው። ይኼ ምኞታቸው እንዲሳካ ብቻቸውን አይሠሩም። ተላላኪ አላቸው። እነዚህም ሁለተኛዎቹ ናቸው። ለገንዘብና ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ወገናቸውን እንደ ይሁዳ የሚሸጡ፣ ሀገር የጣለባቸውን እምነት በሽርፍራፊ ሳንቲም የሚለውጡ ሀገር አልባ ባይተዋሮች ሞልተዋል። የተናገሩትን ሆነው የማይገኙ፣ ቀን ቀን በአደባባይ ስለ ሕዝብ ፍቅር እና ስለ ሀገር አንድነት የሚደሰኩሩ፤ ማታ ማታ ከጠላት ጋር እያሴሩ ወገንን የሚክዱና ሀገር ለማፍረስ ጉድጓድ የሚቆፍሩ ናቸው።

ሦስተኛዎቹ የኢትዮጰያ ጠላቶች ደግሞ ባለማወቅ የእነዚህ የሁለቱ አካላት ተባባሪ የሚሆኑት ናቸው። ግዴለሽ ስለሆኑ፣ የሚያደርጉት ነገር የሚያስከትለውን ውጤት ሳይገምቱ እንዲሁ በነሲብ የጠላትን ተልዕኮ የሚፈጽሙ ውል አልባ ኢትዮጵያውያን ናቸው። እነዚህ ኢትዮጵያውያን አንድን ነገር ተቀብለው ማውራታቸውን፤ ወይም አድርጉ የተባሉትን ነገር ማድረጋቸውን፤ ወይም ሳይመረምሩ የሰጧቸውን መረጃ ሁሉ ማስተላለፋቸውን እንጂ በሀገራቸውና በሕዝባቸው ላይ የሚያስከትለውን ጣጣ አይመረምሩትም። ከመረመሩም ጉዳቱ ከደረሰ በኋላ ብቻ የሚፀፀቱ ናቸው።

ኢትዮጵያ ይበልጥ እየተፈተነች ያለችው በእነዚህ በሁለቱ ነው። ታሪካዊ ጠላቶቻችን በአንድ ስሙ ቁርጣቸው የታወቀ ጠላቶቻችን ናቸው።

ባይተዋሮችና ውል አልባ ኢትዮጵያውያን ግን በወቅቱ ልብ ሳንላቸው ደጋግመው ዋጋ ያስከፍሉናል። በዚህ መልኩ እስከመቼ? ለዚህ ጥያቄ ሁላችንም ቆም ብለን ምላሽ ልንሰጥ ይገባል።

ለውጡ ከመጣ ጀምሮ እንኳን እንደ ሀገር በብዙ ተፈትነናል፤ የሰነቅነውን ተስፋ እንዳናይ የሚከልሉ ስንት ጋሬጣዎች ገጠሙን? ስንቱን ተሻገርን? በስንቱ ወደቅን? አንድ በአንድ ብንዘረዝረው ቁጥሩ ቀላል አይደለም። እነዚህ ፈተናዎች የመጡት ከላይ ከተጠቀሱት የኢትዮጵያ ጠላቶች ነው።

ለውጡ እንዳይሳካና ኢትዮጵያ ጠንካራ የአፍሪካ ኃይል ሆና እንዳትወጣ ለማድረግ ዐቅማቸው የፈቀደውን አድርገዋል። ኢትዮጵያውያን በዘር ተከፋፍለው እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ሀገር በኢኮኖሚ እንድትዳከም፣ ሀገር ተሸክመው የኖሩ ተቋሞቻችን እንዲፈራርሱ በብርቱ ሲሠሩ ነበር።

ሚዲያና የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሰዎችን በመጠቀም ማህበራዊ እሴቶቻችንን ለመበጣጠስ፣ የእምነትና ማኅበራዊ ተቋማትን ለማቃጠል፣ በሕዝብ መካከል ሽብር ለመንዛትና ዜጎቻችንን ዕረፍት ለመንሣት ክፋት የተባሉትን ተግባራት ሁሉ ፈጽመዋል። የፈጸሙት እኩይ ሥራ እጅግ አሰቃቂና ዜጎቻችንን የጎዳ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ለሀገራቸው ባላቸው የጸና ፍቅር ምክንያት ጠላቶቻችን የሚፈልጉትን ግብ ሊያሳኩ አልቻሉም።

ውድ ኢትዮጵያውያን፣

ከለውጡ በፊት ተቋማዊ ስብራት ከገጠማቸው መካከል የሕግና ጸጥታ ተቋማት ይገኙበታል። እነዚህ ተቋማት እንዲሰበሩ የተደረጉት ሆን ተብሎ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ዓላማ ለማሳካት አንዲቻል ነው። በሀገር ውስጥ ሥልጣንና ሀብት ይዘው የነበሩት የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪዎች፣ የሕግና የጸጥታ ተቋማትን በሞትና በሕይወት መካከል እንዲኖሩ አድርገዋቸው ነበር። ከለውጡ በኋላ በእነዚህ ተቋማት ላይ በተሠራው ሥራ የኢትዮጵያን ህልውና ለመታደግ ወደሚችሉበት ደረጃ ለማድረስ ተችሏል። እስከዛሬ ድረስ እነዚህን ተቋማት ለማጠናከርና ለዛሬ ችግሮች ምላሽ፣ ለነገ ፈተናዎች ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ሲባል፣ እያመመንም ቢሆን አያሌ ችግሮችን ተሸክመን ለማለፍ ተገደናል።

ዳሩ ግን ትዕግሥትም ልክና መጠን አለው። አሁን የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት በተሻለ ቁመና ላይ ስለሚገኙ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ ተመጣጣኝ ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ አንልም። ከደህንነትና ከጸጥታ ጋር የተያያዙ ችግሮቻችን በዘላቂነት እንዲቀረፉ የብዙ አካላት ርብርብና ተናብቦ መሥራትን እንደሚጠይቅ ምንም ጥርጥር የለውም። እኛኑ ለሚያሸብሩና እኛኑ ለሚያሰቃዩ ጠላቶች ሕዝብ ምሽግ ከሆነ የጸጥታ አካላት ጥረት ብቻውን መፍትሔ አያመጣም። ስለዚህ እያንዳንዱ ዜጋ፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሚዲያና ሌሎች የሕዝብ ዐይን፣ ጆሮና ክንድ ሆናችሁ የምትሰሩ አካላት ከጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በመግባባት ለመሥራት በሙሉ ልብ ቁርጠኞች መሆን አለባችሁ።

በለውጥ ጎዳና ላይ በመጓዝ ዴሞክራሲን የሚገነቡ ሀገራት በሁለት ጫፍ መካከል የሚቆም ፈተና ይገጥማቸዋል። በአንድ በኩል ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሀገርንና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በጥብቅ ርምጃዎች ማስከበር ነው። ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ስንነሣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ ጥብቅ ርምጃዎችቻን በነጻነትና መብት ስም እንዳይላሉ፤ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የምንወስዳቸው ጥብቅ ርምጃዎችም ዴሞክራሲያዊ ባህልን እንዳያቀጭጩ በሚዛን መንቀሳቀስ ይገባናል። ሁለቱን በሚዛን ለማከናወን ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ ፓርቲ፣ ቡድን፣ ወገን፣ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። የሕግና የጸጥታ ተቋማትም ሕገ መንግሥታዊና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው።

በመሆኑም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን፣ በመሬት ወረራና በተለያዩ የሥርቆትና የማታለል ተግባራት የተሠማሩትን፣ የትራንስፖርትና ሕዝብ እንቅስቃሴዎችን የሚያውኩትን፣ የልማትና የኢንቨስትመንት ተግባራትን የሚያደናቅፉትን፣ በጥናትና በመረጃ በመለየት አስፈላጊው ሁሉ ሕግ የማስከበር ርምጃ እንዲወሰድ የደኅንነት ምክር ቤቱ ወስኗል። በተመሳሳይ የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥ መንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል።

ወላጆች ልጆቻችሁን፣ ሽማግሌዎች ወጣቶቻችሁን፣ የሃይማኖት አባቶች ምእመኖቻችሁን፣ የፓርቲ መሪዎች አባሎቻችሁን፣ የጎሳ መሪዎች ወገኖቻችሁን፣ በመምከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እንድታደርጉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እያቀረብን፣ ከዚህ በተቃራኒው ተሰልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ አካልና ቡድን ላይ ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢውን ሕግና ጸጥታ የማስከበር ሥራ የምንሠራ መሆኑን እናሳውቃለን።

መጭው ቀናት ለሕዝበ ክርስቲያኑም ሆነ ለሕዝበ ሙስሊሙ የበዓላት ሰሞን እንደመሆኑ መጠን አማኞች በትብብርና በመግባባት የጠላቶቻችንን ፍላጎት በማክሸፍና የጋራ ደህንነታችንን በማረጋገጥ እንደ ሀገር የተሳካ ጊዜያት እድንናሳልፍ የደህንነት ምክር ቤቱ አበክሮ ይጠይቃል።

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት
ሚያዚያ 14፣ 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
👍10👏1
ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

በማዕከላዊ ዕዝ በአንድ ኮር ስር ለሚገኙ የከባድ መሳሪያ ምድብተኞቸ ለተከታታይ ወራት ሲሠጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል እያዩ መጠነ እንደገለፁት ከዘሙኑ ጋር የሚዘምን ፕሮፌሽናል ሰራዊት ለመገንባት ስልጠና ወሳኝ በመሆኑ በኮሩ ለሚገኙ ከባድ መሣሪያ ምድብተኞች የተሠጠው ስልጠና የዚሁ አካል ነው።

የከባድ መሣሪያ ምድብተኞች በሙያቸው ተጣጣፊ በመሆን ሁኔታዎችን በመረዳት እና የበላይ አካልን ፍላጎት ቀድሞ በመረዳት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በቁርጠኝነት መወጣት ይገባችኃልም ብለዋል።

ምክትል አዛዡ አክለውም በስልጠናው ያገኛችሁትን እውቀት በመጠቀም ለተፈላጊው ግዳጅ ምንግዜም ራሳችሁን ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሩ መድፈኛ አዛዥ ኮሎኔል አስጨናቂ ፅጌ በበኩካቸው ላለፉት ተከታታይ ወራት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ምድብተኛው በቀጣይ ለሚሰጠው ግዳጅ ዝግጁ የሚያደርገው ነው።

ከሰልጣኞች መካከል ፶/አ መንግስቱ ለገሰ በሠጠው አስተያየት ባለፉት ወራት በተሰጠው ስልጠና ተጨማሪ እና ለቀጣይ ሊያሰራ የሚችል ሙያዊ አቅም ፈጥሬአለሁ ብሏል።

አንዋር ሁሴን
ፎቶግራፍ እንግዳው ታደሰ

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍6