TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
910 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
በጎ ፈቃደኛ ይሁኑ!

የኢ.ስ.ሳ.ሶ በሚያዘጋጀው የክረምት የሕዋ ሥልጠና ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለመሳተፍ ዕድሉን ያግኙ!

ለማመልከት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ!


https://forms.gle/BdtH8ReHf3RSZp5u7

የማመልከቻ ቀነ ገደብ፦ ሐምሌ 11 ፤ 2017 ዓ.ም

#ESSS #Volunteer #SST

@TEMARI_Net1
#Opportunity

🚀 Join the Free Cisco Networking Academy Summer Camp 2025🚀

Are you ready to level up your tech skills this summer? Whether you joined us last year or are new to the journey, this is your chance to unlock your digital future with world-class training from Cisco experts.

Why You Should Join:
Explore Python, AI, HTML, Cybersecurity, Ethical Hacking, and Networking
Flexible, Self-Paced Learning
Real-World Practice
Earn Recognized Certifications
No Fees, No Barriers
Choose What Fits You Best
🔹 Track 1: Programming, AI & Digital Innovation
🔹 Track 2: Cybersecurity & Networking Fundamentals

Program Info:
🗓 Duration: August 1 – September 30, 2025
🧠 Format: Online | Self-Paced + Live Webinars
💰 Cost: Absolutely FREE
📜 Certification: Yes! From Cisco NetAcad
📌 Spots are limited – first come, first served!

🔗 Apply: https://forms.gle/K4crPZwYuzZop4YM9

@TEMARI_Net1
1
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉት ለ2018 ትምህርት ዘመን የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በእቴጌ መነን የሴት እና በገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል።

በትምህርት ቤቶቹ ለመማር ፍላጎት ያላችሁና በ2017 የትምህርት ዘመን በ6ኛ እና 8ኛ ከፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች አማካኝ (Average) 80 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ከሐምሌ 14-18/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ በኦንላይን http://bs.ministry.et ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የመግቢያ ፈተና ለ9ኛ ክፍል አመልካቾች ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም እና ለ7ኛ ክፍል አመልካቾች ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተና የሚሰጥበትን ቦታ በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

#tikvahuniversity

@TEMARI_Net1
👍2
2018 F.Y Call for Community Engagement Proposals.pdf
16.2 MB
We are pleased to announce the opening of the 2025/2026 call for applications for evidence-based community engagement initiatives. A total of 24 proposals will be selected, each receiving an award of 100,000 Birr.
Priority will be given to collaborative engagements that draw upon research findings to address community needs.
The deadline for submission is August 10, 2025.
Please find attached further details regarding the application process. For any inquiries, kindly contact us at community.services@aau.edu.et.

@TEMARI_Net1
2
የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከባለፉት ሶስት አመታት በተሻለ መልኩ በሠላም እና በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ።
----------------------------------------------
(ሐምሌ 9/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የታለመለትን ግብ በመምታት በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ሚንስትሩ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት ሶስት አመታት በተወሰነ መልኩ ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች፣ የፈተና ስርቆት ሙከራዎች፣ የፈተና ስርዓትና አስተዳደር የዲሲፒሊን ግድፈቶች በዘንድሮው አመት ቀንሰው መገኘታቸውን አብራርተዋል።

ለዚህም የበይነ መረብ የፈተና ሽፋን በአንድ አመት ውስጥ በአራት እጥፍ ማደጉ፤የፈተና ግብረ ሀይሉ ያልተቆጠበ ጥረት፤ እንዲሁም ተማሪዎች ሰርቶ ውጤት ማምጣት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን መገንዘባቸውና መሰል ለውጦች ችግሮች ጎልተው እንዳይስተዋሉ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ap4FMbaWM/
#MOE

@TEMARI_Net1
1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መቼ ይገለጻል?

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በጳጉሜን ወር 2017 ዓ.ም እንደሚገለፅ ተናግረዋል፡፡

"በማረሚያ ቤት ያሉ የሕግ ታራሚዎች፣ በአማራ ክልል ፈተናውን መውስድ ያልቻሉ ተማሪዎች እንዲሁም ዘግይተው ትምህርት ለጀመሩ ተፈታኝ ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተናውን በነሐሴ ወር ከሰጠን በኋላ ጳጉሜን ላይ ውጤት እናሳውቃለን" ብለዋል፡፡

ሁሉም ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች መስከረም 08/2018 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከመስከረም እስከ ሰኔ የሚለው የትምህርት ካላንደር በ2018 ትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረው 5.4% የተሻለ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች እነደሚያልፉ ተስፋ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

@TEMARI_Net1
በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ያዘጋጅ የነበረን ርዕሰ መምህር ከግብረአበሩ ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሰላም ቀበሌ ልዩ ስሙ ሳይለንት የእንግዳ ማረፊያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰሩና የሚያሰራጩ መምህራን መኖራቸውን ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ሁለት መምህራን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልፆል፡፡

ተጠርጣሪዋቹ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል የቻሉት አንዲት ግለሰብ የትምህርት ማስረጃ ከ10ኛ ክፍል ወደ 11 ክፍል እንደተዛወረች በማስመሰል ሀሰተኛ ማስረጃ በመስጠታቸውና ወደ አንድ መንግስታዊ ተቋም ለመቀጠር ስትሄድ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባታቸው ለፖሊስ መረጃውን ያሳወቃሉ፡፡

ግለሰቧ ከተቋሙ የልደት ሰርተፊኬት እንድታመጣ ስትጠየቅ ሁለቱ ግለሰቦች ጋር በመሄድ ሀሰተኛ የልደት ሰረተፊኬት በማምጣት አንደኛው ርዕሰ መምህር ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና ሁለተኛው መምህር በአገናኝነት ከግለሰቧ 1ሺህብር ተቀብሎ ለርዕሰ መምህሩ 600 ብር ለራሱ 400 ብር የተከፋፈሉ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባደረገው  ብርበራ 5 ክብ ማተሞች ፣ 5 የራስጌ ማህተሞች ፣የተለያዩ ኃላፊዎች የስምና የስራ ኃላፊነት ቲተሮች ፣ የ1ኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማህተሞች ፣ የነርሲግ፣ የአካውንቲን የዲፕሎማ የትምህርት ማስረጃዎች እና የልደት ሰርተፊኬቶች ከመኖሪያ ቤቱ ሊገኝ  መቻሉ ተገልፆል፡፡

የሁለቱ ግለሰቦች ድርጊት ሌሉች ሙያቸውን አክብረዉ የሚሰሩ መምህራንን እንደማይወክል ተገልጿል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል
@TEMARI_Net1
#TAX
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ!

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወዛጋቢውን የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ በይፋ አጽድቋል። ይህ ውሳኔ ከሠራተኛ ማኅበራት ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም፣ የሀገሪቱን የደመወዝ ታክስ አወቃቀር እንደሚቀይር ይጠበቃል።

ማሻሻያው ምን ይዟል?

አዲሱ አዋጅ ከዚህ ቀደም ከ600 ብር በታች የነበረውን ከቀረጥ ነፃ ገደብ ወደ 2,000 ብር ከፍ አድርጓል። መንግሥት ይህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የግብር ጫና ለመቀነስ እና የግብር መሠረቱን በማስፋት የሀገር ገቢን ለመጨመር እንደሚያስችል ገልጿል።

ሆኖም ተቺዎች፣ ይህ ጭማሪ የኢትዮጵያን የኑሮ ውድነት ያላገናዘበ ነው ይላሉ። አዲሱ የግብር ተመን 15% ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረው 10% የመግቢያ ተመን ተነስቷል። ከፍተኛው የ35% ግብር ደግሞ ወርሃዊ ገቢያቸው ከ14,100 ብር በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይሠራል።

@TEMARI_Net1
1
Forwarded from AAU MEREJA
Call_for_applications_for_admission_to_graduate_programs_PADM.pdf
879.9 KB
Call for Application!
🎓 Graduate Program Opportunities at Addis Ababa University
Department of Public Administration and Development Management (PADM)

📚 Now accepting applications for the 2025/26 academic year:

MA in Public Policy & Development Management(Regular & Extension Programs)
PhD in Public Management & Policy(Regular Program)

🗓 Important Dates:

GAT Registration:July 7 – August 17, 2025
GAT Examination Period: August 18 – 25, 2025

🌐 Apply Now:[https://portal.aau.edu.et](https://portal.aau.edu.et)

📍 Location:
Eshetu Chole Building, Offices 507 & 407, College of Business and Economics (CoBE), AAU

📞 Contact Us:
Tel: +251 111 229 602 / 0910 081 200


📄 For More Information:Please refer to the official PDF announcement.


The Department

@AAUMEREJA
1
መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት እለት መሆኑ ተነገረ

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ጳጉሜ ላይ ይፋ ይሆናል በማለት እስከዚያም ድረስ የሚቆየው ፈተና ያልወሰዱና በመጪው ነሐሴ ወር ለፈተና የሚቀመጡ ቀሪ ተፈታኝ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ትምህርት የጀመሩ በመኖራቸው ነው ፈተና እኩል ያልወሰዱ ተፈታኞች ያሉት በማለትም በመሆኑም ጳጉሜ ወር ላይ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ከታወቀ በኋላ መስከረም 8 ቀን ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚጀምርበት እለት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ካላንደርን በአግባቡ አክብሮ በመስራት የፈተና ጊዜያትንም ላለመሻማት ይሰራል ሲሉ ያከሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከመስከረም ጀምሮ ጥብቅ አሰራር እንደሚኖር ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እኩል ውጤት ተናግሮ በእኩል ትምህርት ለማስጀመር ሲባል ቀሪ ያልተፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎችን ጠብቆ ማስጨረስ እንደሚገባ የተናገሩት የትምህርት ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድና ምክንያት አስቀድመው ፈተና ላይ ካልተቀመጡት በቀር ሌሎቹ የመመዘኛ መስፈርቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።


@TEMARI_Net1
Forwarded from #Abugida Message Board
🌍 The environment is not someone else’s problem: it’s everyone’s responsibility.
From rising temperatures to shrinking green spaces, the challenges are real and urgent.

🌱 Join the Abugida GRC 2025/26 Team!
We’re calling on passionate individuals ready to take meaningful action for a greener, healthier planet.
Together, let’s protect the only home we share.

2025/26 Theme:
_"From Local Action to Global Impact: Human Beings for Earth"_
(Aligned with SDGs 11, 13, and 17)

📌 Why Join?
*   Take action for the environment
*   Connect with passionate changemakers
*   Build local impact with global reach
*   Grow through leadership and learning

📩 Get Involved Now:
Join our group → t.me/+oCSPS4HZys01ZTQ0
Contact:
@kinde21 | 0921385604
@ananiya_sirak | +251965941486


#GRC #RacAbugida  #Rotaract #Rotary #District9212 #UniteForGood #MakeItHappen

Follow us on 👇

Facebook | Instagram | Telegram | Linkedin | TikTok | WhatsApp | X(Twitter)
1
#TECH
የቀድሞው የTwitter co-founder እና CEO የነበረው Jack Dorsey ያለምንም sim card እና internet network በBluetooth ብቻ text message መላላክ የሚያስችላችሁ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።

⚫️አፕሊኬሽኑ Bitchat ይባላል።
⚫️ከPlaystore ላይ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.hostingduty.bitchat

⚫️አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም አካዉንት መክፈት አይጠይቅም።
⚫️ምንም አይነት Server ስለሌለው end-to-end encrypted ነው። ያ ማለት 3ኛ ወገን የምንፃፃፈውን ሊያይ አይችልም።

Bluetooth በ10 ሜትር ርቀት ስለሚሰራ text መላላክ የምንችለው በ10 ሜትር ርቀት ብቻ ነዉ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።
ነገር ግን ከዛም በላይ መላላክ እንችላለን። ምክንያቱም በአካባቢያችን ብዙ ተጠቃሚዎች ካሉ የሚፈጠሩት ትንንሽ ኔትዎርኮች ሌላ ትልቅ mesh network እየፈጠሩ ሰፊ ክልል እንዲያካልሉ ያስችላሉ።

ይህ ቴክኖሎጂ በጣም ብዙ አይነት ጠቀሜታዎች አሉት።
⚫️የስልክ ኔትዎርክ በሌለባቸውና አደጋ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች communication እንዲኖር ያስችላል።
⚫️Security ለሚያሳስባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ።

©️bighabesha_software

@TEMARI_Net1
👍21
በምድር ላይ እስካሁን ከተገኙት የማርስ ድንጋዮች ትልቁ የሆነው ድንጋይ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ።

NWA 16788 በመባል የሚታወቀው ሜትሮዪት 24.5 ኪሎ ግራም ክብደት እና 38.1 ሴንቲ ሜትር እርዝማኔ አለው ሲባል በ2023 ነበር በኒጀር የተገኘው።

ከሱ ቀጥሎ ካለው የማርስ ክፋይ በ70 በመቶ ትልቅ መሆኑ ሲነገር በምድር ላይ እስካሁን 400 የሚሆኑ የማርስ ድንጋዮች ብቻ መገኘታቸውም ይነገራል።

ድንጋዩ በጨረታ በኒው ዮርክ ሲሸጥ ከታክስ እና ሌሎች ክፍያዎች ጋር ተዳምሮ ዋጋው 5.3 ሚሊየን ዶላር አውጥቷል።

ከሽያጩ በኋላም ጉዳዩ ሚስጥር በመሆኑ የድንጋዩ የመጨረሻ መዳረሻ እና ማን እንደገዛው ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።

የማርስ ድንጋዩ በ2023 የተገኘባት ኒጀር ከሽያጩ የገንዘብ ክፍያ ስለማግኘቷም የተባለ ነገር የለም።

Source: BBC

@TEMARI_Net1
1
#DRC
በዓመት ከ11-13 ሚሊየን ዶላር ለባርሴሎና ስፖርት ክለብ ለመክፈል የተስማማችው አፍሪካዊት ሀገር!

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ሃገሯን ለማስተዋወቅ ከስፔኑ የእግር ኳስ ክለብ ባርሴሎና ጋር የ46 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራርማለች።

በስምምነቱ መሰረትም የማልያ ላይ ስፖንሰር ሲሆን በባርሴሎና የወንዶች እና የሴቶች ቡድን የልምምድ እና የማሟቂያ ማልያ ላይም ኮንጎን ለማስተዋወቅ 'Heart of Africa' የሚል ፅሁፍ ይኖራል ተብሏል።

በተጨማሪ ይህ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ማስታወቂያ በባርሴሎና አመታዊ ሪፖርት እና መፅሔት ላይም ይኖራል ተብሏል።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በየአመቱ ለመጪዎቹ አራት አመታትም ከ11-13 ሚሊየን ዶላር ለባርሴሎና ትከፍላለች።

በተጨማሪ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ጋር አመታዊ የ1.9 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ባለፈው ወር ስትፈራረም  ከጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ጋር መጠኑ ያልተገለፀ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈራርማለች።

ከዚህ በፊት ሩዋንዳ 'visit rwanda' በሚል ከአርሰናል፣ ፒ ኤስ ጂ እና ባየር ሙኒክ ጋር ተመሳሳይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማድረጓ ይታወሳል።

Source: TRT

@TEMARI_Net1
Forwarded from Alpha Market
💠Shop at #AlphaMarket at a discount price

Airpods Pro(USA) white color 1699 birr
Airpods pro (USA) Black color 1799 birr

Calculator (Scientific) : 800 birr
P9 headset 1599 birr
Airpods Pro 5s 1199 birr
Galaxy buds pro(New product) 1900 birr


u can check additional products @alphamarket21

contact us @ordernow21
with free delivery
1