TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
911 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት ስለጠና የምዘና ውጤት በቀጣይ ቀናት በበይነ መረብ ይለቀቃል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ላለፉት 25 ቀናት ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

መምህራኑ በሚያስተምሩበት የትምህርት ዓይነት ይዘት፣ በቴክኖሎጂ እና በማስተማር ዘዴ (ፔዳጎጂ) አቅም የገነቡበት እንደነበር በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም በሦስት ተከፍሎ በተሰጠው ስልጠና፤ 64,900 መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ከ60 እስከ 120 ሰዓት የቆየ ስልጠና መውሰዳቸውን በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ አሰገደች መሬሳ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ከ2,400 በላይ አሰልጣኖች መሳተፋቸውንና 184 ሺህ የስልጠና ሞጁሎች ተዘጋጅተው መሰራጨታቸውን ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

ሰልጣኞቹ የድህረ ስልጠና ምዘና ፈተና በበይነ መረብ የወሰዱ ሲሆን፤ በቀጣይ ቀናት የይለፍ ቃል (Password) እና የመጠቀሚያ ስማቸውን (User Name) በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ብለዋል፡፡

70 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀታቸውን አውርደው መውሰድ እንደሚችሉ ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

@TEMARI_NET1
🔥1
#ጥቆማ

ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ደረጃ ባቋቋማቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

እነዚህን ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚመሩ #ዳይሬክተሮችን ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉና በልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዳይሬክተር መሆን የምትፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ይመዝገቡ 👇
http://sbs.moe.gov.et/directors/apply

የቅጥር ሁኔታ 👉 በቋሚነት

ደመወዝ 👉 የልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለማስተዳደር በሚወሰነው የደመወዝ ስኬል መሰረት

መስፈርቶች፦

አካዳሚያዊ ብቃት / የትምህርት ዝግጅት
➫ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራርነት 10 ዓመትና በላይ ልምድ ያላው/ያላት፣
➫ በት/ት ቤት አመራርነት ሙያ 2ኛ ዲግሪ እና በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላው/ያላት፣
➫ በት/ት ቤት አመራርነነት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ሰርትፍኬት ያለው/ያላት፣
➫ በክረምት ልዩ የመምህራን እና ት/ት ቤት አመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና ሰርትፍኬት ያለው/ያላት፣
➫ የአንድ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት አመራሮች የስራ ላይ ስልጠና የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
➫ መሰረታዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕውቀትና ክህሎት ያለው/ያላት።

የምዝገባ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ ቀናት


(ሙሉ የተቋሙ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@TEMARI_Net1
1🔥1🙏1
Forwarded from Alpha Market
📢 We’re Buying!

If you have a phone or PC for sale, please DM us at @ordernow21.
🥰1
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ተለቋል

በ16 የጤና ሙያ መስኮች ተመርቃችሁ በነሐሴ 2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115186275 / 0115186276 በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በማሳወቅ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@TEMARI_Net1
1
Call for training at AAU,School of Commerce

@TEMARI_Net1
🔥1💯1
ECONOMICS GRADUATE PROGRAMS ENTRANCE EXAM GUIDELINE 2025.pdf
6.9 MB
Dear Economics Postgraduate Program Applicants:
The department has prepared a detailed guideline outlining the specific procedures we will pursue to enroll students to MSc in Economics and PhD in Economics programs. It provides all important information regarding entry requirements, entrance exam coverage, and enrollment procedures.
Please follow the guideline for your entrance exam preparation (attached here!).
Best of luck
The Department

Department of Economics,

@TEMARI_Net1
1
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአራት የአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና አጊኝቷል።

ዩኒቨርሲቲው በባዮ-ቴክኖሎጂ፣ በምግብ ሳይንስና አመጋግብ ስርዓት፣ በኬሚካል ኢንዱስትሪ እንዲሁም በጅኦሎጂ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጃ እንግዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ዕውቅናው (Accreditation) በትምህርት መስኮቹ የተመረቁ ተማሪዎች 'ያለምንም' መመዘኛ በውጭ ሀገራት ሥራ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተገኘባቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ለውጭ ሀገራት ተማሪዎች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ ዕውቅናው እ.አ.አ ከ2023 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁትን እንደሚያጠቃልል አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው Accreditation Board of Engineering and Technology (ABET) ተቋም ነው ዕውቅናውን ያገኘው፡፡

@TEMARI_Net1
🔥71
Heinken Ethiopia hiring sales Analyst in Addis Ababa
https://www.linkedin.com/jobs/view/4295023339
1
ለሴት ተማሪዎች የትምህርት ውጤታማነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ገለፁ።

---------------------------------------

(ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም) የጳጉሜን 2 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ለዳግማዊ ሚኒሊክ እና ለቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የተደረገው ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ውጤታማነት የላቀ ትርጉም ያለው መሆኑን ተናግረው መሠል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል

አክለውም በቅርቡ የጸደቀው የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ሴት ተማሪዎችን በትምህርት ውጤታማ የማድረግ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ትምህርት ቤቶች ሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያሰፈልጓቸው ነገሮች አንዱ የሆነውን የንጽህና መጠበቂያ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አዋጁ በቅርቡ የጸደቀ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለአዋጁ መተግበር በትምህርት ዙሪያ የሚሰሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር፣ በመተጋገዝና በመደጋገፍ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በበኩላቸው አገር የሚገነባው በእያንዳንዱ ዜጋ አስተዋጽኦ በመሆኑ በህብር በመቆም በአንድነት በመሆን ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግና የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶቻችንን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/19NojjS3hB/
1
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ራሱን በራሱ ማብረር የሚችል የአየር ላይ ኤሌክትሪክ ታክሲ አስተዋወቀች።

ሩዋንዳ self-flying ወይም ራሳቸውን በራሳቸው የሚያበሩ የአየር ላይ ታክሲ በመጀመር ከአፍሪካ ፈር ቀዳጇ ሀገር መሆን ችላለች።

ከChina Road and Bridge Corporation እና EHang Holdings Limited ጋር በመተባበር እንደተሰራች የተገለፀችው ይህቺ የአየር ላይ ታክሲ ኪጋሊ ላይ በተዘጋጀው የAviation Africa 2025 ፕሮግራም ላይ ለእይታ ቀርባለች።

EH216-S የሚል ስያሜ ሲሰጣት ከፍተኛ ፍጥነቷ 130 ኪሎ ሜትር በሰአት እንዲሁም ለ35 ኪሎ ሜትር ወይም ለ21 ደቂቃ መብረር ትችላለች ተብሏል።

ሹፌር አልባ የሆነችውና ከelectrically vertical takeoff and landing (eVTOL) የኤርክራፍት ቤተሰብ የምትመደብ ሲሆን ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና የአቪዬሽን ባለሙያዎች በተገኙበት በኪጋሊ ሰማይ ላይ መብረር ችላለች። #BST
@TEMARI_Net1
🔥2
#ቀይ_ጨረቃ የሙሉ ጨረቃ ግርዶች በኢትዮጵያ ሰማይ እየታየ ነው።

ጨረቃ በመሬት ሙሉ ጥላ ውስጥ ስታልፍ ደማቅ ቀይ ቀለም ስለምትይዝ " ቀይ ጨረቃ " (Blood Moon) በመባል ይታወቃል።

@TEMARI_Net1
💔1
ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

ለፈተና የተመረጣችሁ ስም ዝርዝራችሁን በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ከዛሬ ጀምሮ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባችሁ በኦላይን ቅሬታችሁን እስከ አርብ መስከረም 02/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ፦ ለፈተና ያለፋችሁ ተማሪዎች በየክልላችሁ/ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኩል ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለፅን በቀጣይ በኦላይን ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

@TEMARI_Net1
1
ኢንተርኔት በነፃ‼️
የታላቁ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ነገ የምረቃ ስነስርዓቱን በቀጥታ ስርጭት በነፃ ይከታተሉ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ብስራት አሰምቷል።
የዓመታት ሕልማችን በይፋ ዕውን የሚሆንበት ታላቅ ታሪካዊ የድል ብስራት ነገ ዻጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢንተርኔት ክፍያ ነፃ መከታተል ይችላሉ።
#አዩዘሀበሻ

@TEMARI_Net1
👍2
#GERD💪

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምን አሉ ?

" ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ በዓል አደረሳችሁ! 

የዚህ አስደናቂ ክስተት አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።  የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፕሮጀክቱን ለመጀመር ባሳዩት ራዕይ እና ድፍረት እናስታውሳቸዋለን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ፕሮጀክቱን ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@TEMARI_Net1
🔥41