TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
911 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
ለሴት ተማሪዎች የትምህርት ውጤታማነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ገለፁ።

---------------------------------------

(ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም) የጳጉሜን 2 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ለዳግማዊ ሚኒሊክ እና ለቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የተደረገው ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ውጤታማነት የላቀ ትርጉም ያለው መሆኑን ተናግረው መሠል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል

አክለውም በቅርቡ የጸደቀው የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ሴት ተማሪዎችን በትምህርት ውጤታማ የማድረግ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ትምህርት ቤቶች ሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያሰፈልጓቸው ነገሮች አንዱ የሆነውን የንጽህና መጠበቂያ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አዋጁ በቅርቡ የጸደቀ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለአዋጁ መተግበር በትምህርት ዙሪያ የሚሰሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር፣ በመተጋገዝና በመደጋገፍ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በበኩላቸው አገር የሚገነባው በእያንዳንዱ ዜጋ አስተዋጽኦ በመሆኑ በህብር በመቆም በአንድነት በመሆን ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግና የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶቻችንን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/19NojjS3hB/
1
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ራሱን በራሱ ማብረር የሚችል የአየር ላይ ኤሌክትሪክ ታክሲ አስተዋወቀች።

ሩዋንዳ self-flying ወይም ራሳቸውን በራሳቸው የሚያበሩ የአየር ላይ ታክሲ በመጀመር ከአፍሪካ ፈር ቀዳጇ ሀገር መሆን ችላለች።

ከChina Road and Bridge Corporation እና EHang Holdings Limited ጋር በመተባበር እንደተሰራች የተገለፀችው ይህቺ የአየር ላይ ታክሲ ኪጋሊ ላይ በተዘጋጀው የAviation Africa 2025 ፕሮግራም ላይ ለእይታ ቀርባለች።

EH216-S የሚል ስያሜ ሲሰጣት ከፍተኛ ፍጥነቷ 130 ኪሎ ሜትር በሰአት እንዲሁም ለ35 ኪሎ ሜትር ወይም ለ21 ደቂቃ መብረር ትችላለች ተብሏል።

ሹፌር አልባ የሆነችውና ከelectrically vertical takeoff and landing (eVTOL) የኤርክራፍት ቤተሰብ የምትመደብ ሲሆን ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና የአቪዬሽን ባለሙያዎች በተገኙበት በኪጋሊ ሰማይ ላይ መብረር ችላለች። #BST
@TEMARI_Net1
🔥2
#ቀይ_ጨረቃ የሙሉ ጨረቃ ግርዶች በኢትዮጵያ ሰማይ እየታየ ነው።

ጨረቃ በመሬት ሙሉ ጥላ ውስጥ ስታልፍ ደማቅ ቀይ ቀለም ስለምትይዝ " ቀይ ጨረቃ " (Blood Moon) በመባል ይታወቃል።

@TEMARI_Net1
💔1
ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

ለፈተና የተመረጣችሁ ስም ዝርዝራችሁን በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ከዛሬ ጀምሮ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባችሁ በኦላይን ቅሬታችሁን እስከ አርብ መስከረም 02/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ፦ ለፈተና ያለፋችሁ ተማሪዎች በየክልላችሁ/ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኩል ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለፅን በቀጣይ በኦላይን ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

@TEMARI_Net1
1
ኢንተርኔት በነፃ‼️
የታላቁ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ነገ የምረቃ ስነስርዓቱን በቀጥታ ስርጭት በነፃ ይከታተሉ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ብስራት አሰምቷል።
የዓመታት ሕልማችን በይፋ ዕውን የሚሆንበት ታላቅ ታሪካዊ የድል ብስራት ነገ ዻጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢንተርኔት ክፍያ ነፃ መከታተል ይችላሉ።
#አዩዘሀበሻ

@TEMARI_Net1
👍2
#GERD💪

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምን አሉ ?

" ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ በዓል አደረሳችሁ! 

የዚህ አስደናቂ ክስተት አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።  የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፕሮጀክቱን ለመጀመር ባሳዩት ራዕይ እና ድፍረት እናስታውሳቸዋለን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ፕሮጀክቱን ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@TEMARI_Net1
🔥41
Forwarded from AAU MEREJA
🌿 Happy Ethiopian New Year (Enkutatash)! 🎉🇪🇹
We Ethiopians are unique, unlike the rest of the world that follows the Gregorian calendar, we celebrate our own. May this new year bring peace, unity, prosperity, and endless blessings to all Ethiopians at home and abroad. 🌞💐

🌸 እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! 🎊🇪🇹
መልካም አዲስ አመት! 🌿🌞

@AAUMEREJA
🔥41
Larry Ellison የአለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብት መሆን ቻለ።

Larry Ellison elon muskን በመብለጥ የአለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብት መሆን ችሏል።

የ81 አመቱ Larry Ellison oracle የተሰኘው በSoftware፣ databaseና cloud computing ላይ ትኩረቱን ያደረገ የTechnology ድርጅት መስራች ሲሆን ይህም ድርጅት ሰሞናዊ የስቶክ ማርኬት ዋጋው በ40% ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የEllison ሀብት በአንድ ቀን ብቻ በ101 ቢሊዮን ዶላር ጨምሮ አጠቃላይ ሀብቱ ከ393 ቢልዮን ዶላር በላይ መሆን ችሏል።

Oracleን በ19777 ከBob Miner እና Ed Oates በጋራ የመሰረተው Ellison እስካሁን ድረስ የድርጅቱ ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር እና ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ያገለግላል።

Elon musk በ2021 የAmazonኑን Jeff Bezosን በመብለጥ የአለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም መሆን መቻሉ አይዘነጋም።

በነገራችን ላይ በአሁኑ ሰአት አለማችን ላይ ካሉ Top 10 ባለፀጋዎች መካከል 8ቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ እንደሆኑ ታውቃላችሁ?

ምንጭ፡ #Fortune, #Bloomberg

©bighabesha_softwares

@TEMARI_Net1
2👏1
#ጥቆማ
#EthiopianAviationUniversity

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከስር በተገለፁ አራት የመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ፕሮግራሞች ትምህርት መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

Aeronautical Engineering
Aviation Management
Aircraft Maintenance
Tourism

የምዝገባ ጊዜው ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት መቅረቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ይመዝገቡ!

ለማመልከት 👉 https://eau.edu.et

ለተጨማሪ መረጃ 👇

Email:
etauinfo@ethiopianairlines.com, eaainfo@ethiopianairlines.com
Phone: +251-115174600 / 8598

@TEMARI_Net1
1
#Grade12Result

" ሲያልቅልን ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ትክክለኛ ቀን እናሳውቃችኋለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት


በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች " የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ነው ይፋ የሚደረገው ? ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጳጉሜን 4/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋል ብለው ነበር ሳይደረግ አለፈ ውጤት ይፋ የሚደረገው መቼ ነው ? " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች እና ወላጆችን ጥያቄ ይዞ አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን አነጋግሯል።

እኚህ አመራር " ውጤት ሲያልቅ እንገልፃለን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ይለቀቃል፤ ትክክለኛው ቀን ሲወሰንም በይፋ ሚዲያ ጠርተን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ተማሪዎችን እያወናበዱ ነው " ያሉት አመራሩ ተማሪዎች ውጤቱ ይፋ የሚደረግበትን ቀን ከተቋሙ እስኪሰሙ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ገፆች (በፌስቡክ ፣ ቴሌግራም) " ስለ ውጤት መረጃ አገኘን በዚህ ቀን ይወጣል " እያሉ የሚያሰራጩት መረጃም ሀሰተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል።

" እኛ በሚያልቅ ጊዜ እናንተን ጨምሮ ሚድያዎችን ጠርተን እናሳውቃለን " ያሉም ሲሆን " ' በዚህ ቀን ይወጣል ተብሎ ነበር ' የሚለው ሳይሆን ጥርት ብሎ ሲያልቅልን በፍጥነት እናሳውቃለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ580 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@TEMARI_Net1
በአዲስ አበባ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የስድስት ወር እና የአመት ከሰባት ወር ህጻናትን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ራዕይ ጤና ጣቢያ አካባቢ በትላንትናው ዕለት በግምቱ 9:45 አካባቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

አደጋው የደረሰው በሙያዋ ነርስ የሆነች እናት በስድስት ወር እና በአመት ከሰባት ወር ልጆቿ ፣ በሰራተኛዋ እንዲሁም ቡና ለመጠጣት ህጻን ወንድ ልጇን ይዛ በመጣች ጎረቤቷ ላይ ነው።

የአምስቱ አስክሬን ትላንት ምሽት የተገኘ ሲሆን የሰራተኛዋ አስክሬን አለመገኘቱን እና በፍለጋ ላይ መሆኑን በእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኮማንደር ልኡል ሃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኮማንደር ልኡል ሃይሉ አደጋው ጠባብ በሆነ እና የተደፈነ ድልድይን አልፎ በወጣ ደራሽ ጎርፍ ውሃ ምክንያት የደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮማንደር ልኡል ሃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ዝርዝር ቃል ምን አሉ ?

" አደጋው የተከሰተው ከላይ አካባቢ በመጣ ደራሽ ውሃ እንጂ በአካባቢው በዘነበ ዝናብ አይደለም።

ቀጠና 3  ፖሊ መምህራን ኮሌጅ አጠገብ የሚገኝ ድልድይ አለ ድልድዩ በግንድ እና በተለያዩ እንጨቶች ተጋድሞ ቆሻሻ የደፈነው በመሆኑ መንደሩን ሊጥለቀለቅ ችሏል።

መምህራን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አጥሩ ስር የሚገኘው ድልድይ በቆሻሻ እና ግንድ ሲዘጋ የመጣው ጎርፍ ኦፈር ፍሎው ሲያደርግ ቀጥታ ወደ መንደሮች ገባ ወደ መንደሮች ሲገባ በቀጥታ ያገኘው ቤት አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ቤት ሆነ።

ከድልድዩ የወጣው ውሃ ቁልቁለት ላይ በመንደርደር 200 ሜትር አካባቢ ከሄድ በኋላ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ስድስት ሰዎችን ውስዷል።

ቤቱ ወንዝ ዳር የሚገኝ በመሆኑ የመጣው ጎርፍ የቤቱን ግድግዳ ጣሪያ ድረስ ከሞላ በኋላ ግድግዳውን በማፍረስ ይዟቸው ሄዷል።

ነርስ የሆነች እናት ሁለት ልጆቿን ይዛ ቁጭ ብላ ነበር ከሰራተኛዋ ጋር ቡና እየጠጡ ነበር ከጎረቤት ልጇን ይዛ የመጣች ሴትም ከእነ ልጇ በጎርፉ ተወስደዋል።

የስድስት ወር እና የአመት ከሰባት ወር ህጻናትን ጨምሮ ሁለት ወንድ እና አራት ሴቶችን በአጠቃላይ ስድስት ሰዎች በአደጋው ህይወታቸው አልፏል።

አደጋው በደረሰ ሰአት በሙያው ዶክተር የሆነው ባለቤቷ በስራ ላይ ነበር።

የአምስቱ ሰዎች አስክሬናቸው ከጥቁር አባይ እስከ ጎሮ ባለው አካባቢ ትላንት ምሽት ተገኝቷል የሰራተኛዋ አስክሬን እስካሁን አልተገኘም።

አስክሬኖቹ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወስደዋል የመለየት ስራ ተሰርቷል ስርአተ ቀብራቸው ገና አልተፈጸመም።

ሎሎች ቤቶች ላይ ውሃ ገብቶ ነበር ነገር ግን የተገነቡበት ግንባታ አስተማማኝ ስለነበር ምንም አልሆኑም።

አደጋው ሊደርስ የቻለበት ምክንያት ሰዎቹ ከወንዙ አካባቢ ያላቸው አሰፋፈር ትክክል ስላልሆነ እና የአደጋ ስጋት ስለመኖሩ በተደጋጋሚ ሲነገር ችላ በመባሉ ነው።

የጠበበው ድልድይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ይታወቅ ነበር በአካባቢው የሚገኙ ማህበረሰቦች ሊሰሩትም ገንዘብ አዋጥተው ነበር ነገር ግን ገንዘቡ ስላልሞላ እስካሁን ሳይሰራ ቆይቷል።

ምልከታ አድርገናል የወደቀውን ቤት ለማንሳትም ማሽን ይዘው እየመጡ ነው ውሃ የወጣበት ድልድይም ማንሆሉ ጠባብ ስለሆነ መሻሻል አለበት ማንሆሉ ክፍት ሆኖ ቦዩን ተከትሎ እንዲፈስ እና ወደ መንደሩ የሚመጣው ውሃ መከላከያ ግንብ ተሰርቶለት ምላሽ መሰጠት አለበት።

ስጋት እስከ ታች መንደሮች ድረስ አለ ስጋት የኖረበት ምክንያት ወንዙን ተከትለው እስከ ታች ቤት ሰርተውበታል ቤቶቹም ቢሆኑ እንዲህ አይነት ደራሽ ውሃ ሲመጣ መቋቋም የሚችሉ አይደሉም።

እነዚህን ስጋቶች ለመከላከል እየተሰራ ነው አሁን አደጋ የተከሰተበት ቦታ ላይ ማሽኖችን አስገብቶ የማጽዳት ስራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
💔122
Forwarded from AAU MEREJA
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።

የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ ነ ከ10 ሰዓት ጀምሮ መግለጫ ይሰጣል።

#MoE

@AAUMEREJA
🌟

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የሚሰጠውን መግለጫ ቀጥታ በ t.me/TikvahethMagazine ላይ በቀጥታ መከታተል ይችላሉ።

#TikvahEthiopia

@TEMARI_Net1
1