አራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የህግ ጥናትና ማውጣት ስርጭት ቡድን – Telegram
አራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የህግ ጥናትና ማውጣት ስርጭት ቡድን
869 subscribers
98 photos
1 file
Download Telegram
ሴት የምክር ቤት አባላት የምክር ቤቱን ህግና ደንብ በተገቢው መንገድ በመረዳት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

አራዳ ታህሳስ 8/2015

አራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በምክር ቤት ህግና ደንብ ላይ ለሴት የምክር ቤት አባላት ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ የምክር ቤቱን አሰራር፣ ህግና ደንብ በመገንዘብ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የተጠቃሚነት ጥያቄዎችን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ እንደሚገባ ለሴት የምክር ቤቱ አባላት የማስታወስና ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

በተያያዘም ሴት የምክር ቤት አባላት የምክር ቤቱን ህግና ደንብ በተገቢው መንገድ በመረዳት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አስፈጻሚው አካል የመቆጣጠር፣ የመከታተል ድጋፍ የማድረግ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡

የምክር ቤት አባላት በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የታወቁ ህግና ደንቦችን ከስራቸው ጋር አጣጥመው መስራት አለባቸው ያሉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ምከር ቤት ጽ/ቤት የህግ ጥናት ማውጣትና ስርጭት ቡድን መሪ አቶ ኤርሚያስ ተስፋዬ በህግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባሩን የህዝብና የዜጎችን ጥቅም ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከማስከበር ውጭ ለግል ጥቅምና አድሎአዊ ተግባራትን ለመፈፀም መጠቀም እንደሌለባቸው ገልፀዋል፡፡

ሴት የምክር ቤት ተሳታፊዎችም በህግ የተሰጣቸውን ሰልጣንና ተግባር በአግባቡ በመጠቀም የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
😁21
የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የህግ ጥናት ማውጣትና ስርጭት ቡድን የክፍለ ከተማና የወረዳ ህጻናት ፖርላማ አባላት በህጻናት ፖርላማ ምርጫ ዙርያ በቀን 15/04/2015 ዓ.ም የህግ ጥናት ማውጣትና ስርጭት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ኤርሚያስ ተስፋዬ አማካኝነት ስልጠና ተሰጠ።
1
የህፃናት ፓርላማ ሁለተኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

አራዳ ታህሳስ 22/2015 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የህፃናት ፓርላማ ሁለተኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው ያሉት አራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ንግስቲ ጫላ ህፃናት በትምህርት ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ ዘርፍ ታንፀው እንዲያድጉና የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን በኃላፊነት ስሜት እንዲያድጉ አስተምሮቱ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በጉባኤውም የ2015 በጅት ዓመት የ6ወር ሪፖርትና የ8ቱም ወረዳ ክትትልና ደረጋፍ ግብረ ምልስ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም የህፃናት ፖርላማ እንደ አዲስ አፈ -ጉባኤ፣ ምክት አፈ -ጉባኤና ፀኃፊ ተመርጦ ፀድቋል፡፡
👍51