Ashara Media - አሻራ ሚዲያ – Telegram
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
79.3K subscribers
24.7K photos
1.17K videos
24 files
9.65K links
ስልክ፥ +251984000629 / +251993111700
Download Telegram
💚💛 ከአማራ ፍኖ በጎጃም ከደጋ ዳሞት ብርጌድ የተላለፈ ጥብቅ ትዕዛዝ ‼️

1ኛ. ከ 10/09/2016 ዓ.ም ጀምሮ በህዝብ ተነሳሽነት የተዘጉ ማንኛውም የንግድ ተቋማት  ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ።

2ኛ. ከህዝብ ትግል እና ጥቅም በተፃራሪ ፅንፍ  በመቆም በራሱ ተነሳሽነት ግብር የከፈለ ማነኛውም ግለሰብ ወይም የድርጅት ባለቤት ለስርዓቱ የከፈለውን በብዙ እጥፋ ለድርጅታችን የሚከፍልና እንደ አስፈላጊየቱ ተመጣጣኝ እርምጃ የሚወሰድበት ይሆናል።

በመጨረሻም ጀግናው የደጋ ዳሞት ህዝብ እያደረገው ያለውን ሁለንተናዊ ትግል እያደነቅን ድርጅታችን የሚያስተላልፈውን ውሳኔ የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን ።
👍697🥰3🔥2
ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ አገዛዙ ኃይሎች የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ።

የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ራያ ቆቦ ከተማ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በወታደራዊ ፖትሮል መኪና ሲንቀሳቀስ የነበረ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ የደፈጣ እርምጃ ወስዷል፤ በተወሰደውም እርምጃም የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዥ ከእነ አጃቢዎች መደምሰሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ኦፕሬሽን የፈፀሙት የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ አሳምነው ጽጌ ክፍለጦርና ዞብል አምባ ክፍለጦር መሆናቸውን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።

በዚህ ቀጠና እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ክፍለጦሮች የተጠኑ እና ልዩ ኦፕሬሽኖችን በአገዛዙ ኃይሎች እየሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
251
👍619
👍65🥰7
በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሰማርተው ከነበሩ የአድማ ብተና አባላት መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የሚሆኑት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ!

በራያ የአማራ ክልል መዋቅር እንዲፈርስ ከተደረገ ወዲህ ከአሃዳቸው እየከዱ ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነው የተመላከተው።

ያለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ ወሎ ዞን በሐይቅ፣ በቢስቲማ፣ በወረባቦ፣ በውጫሌ ዙሪያና በአምባሰል እንዲሁም በሰሜን ወሎ ደግሞ በመርሳ፣ በውርጌሳ፣ በወልድያ ዙሪያ፣ በቆቦ፣ በላስታ እና በሙጃ ዙሪያ በቁጥር ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ነው ለማረጋገጥ የቻሉት።

የአማራ እርስት በሆኑት ግራ ካሱን ጨምሮ በሌሎች የራያ አከባቢዎች የተከሰከሰው የጓዶቻችን አፅም ሳይነሳ የሞቱለት አላማ ከግብ ሳይደርስ በመቅረቱ፡ በገዢው ስርዓት ላይ ያለን እምነት አብቅቷል፣ አማራጫችን አፈሙዝ ማዞር ብቻ ነው ሲሉ የአድማ ብተና አባላቱ የገለፁት።

ግምቦት 09/2016 ዓ/ም እና ግምቦት 10 እንዲሁም በትናንትናው ዕለት ብቻ በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ 24 የአድማ ብተና አባላት፣በወልድያ ዙሪያ 13፣ በመርሣ 12፣ በኒኒ በር 5፣ የአድማ ብተና አባላት እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ በሐይቅ 17፣ በቦቀቅሳ 22፣ በውጫሌ 9፣ በወረባቦ 5(አንድ መቶ አለቃ ከነ አጃቢዎቹ) በአምባሰል 22፣ በፀሀይ መውጫ 4፣ በወግዲና በሌሎች ምዕራብ ወረዳዎች በቁጥር 19 የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአቅራቢያቸው የሚገኙ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ክፍለጦሮችን መቀላቀላቸውን ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።

በተመሣሣይ በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ባሉ አከባቢዎች ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የአድማ ብተና እንዲሁም የሚሊሻና የፖሊስ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት ከ970 በላይ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአሁኑ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አንድ አካል የሆነውን የቀድሞው የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ዕዙ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም።

በሁለቱ ዞኖች ያለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በክልሉ ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መፈጠሩም ተሰምቷል።

ተሰማርተው ከነበሩበት የሐይቅ ከተማ አከባቢ ከድተው ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት በቁጥር 17ቱ የአድማ ብተና አባላት፡ "እስከ ዛሬ ይሰጣችኋል ተብሎ ቃል የተገባልንን የቤት መስሪያ ቦታ ከዛሬ ነገ ይሰጠናል ብለን ብንጠብቅም ነገር ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። በዚህ መኃል በርካታ ጓዶቻችን ተሰውተውብናል" ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም "በርካታ ጓዶቻችንን ገብረን፣ ስጋና አጥንታችን ከስክሰን ያስመለስነውን የራያና የወልቃይት እርስታችን በድጋሚ ተመልሶ ለሕወሓት ተሰቶብናል፣ ለምን ብለው የጠየቁ አባሎቻችንም ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን አናውቅም። በዛላይ ከወንድሞቻችን ጋር እንድንገዳደል ተገደናል። በዚህ ሁኔታ ይሄንን የአገዛዝ ስርዓት እንዴት ልናገለግል እንችላለን?" ሲሉ ጥያቄም አንስተዋል።

የቤት መስሪያ ቦታ ስንጠብቅ በምትኩ እየተሰጠን ያለው የቀብር ጉድጓድ ነው ያሉት የአድማ ብተና አባላቱ፡ ከማለቃችን በፊት እስከ ዛሬ ክህደት የፈፀምንባቸውን ፋኖ ወንድሞቻችን ይቅርታ ጠይቀን ያሳዘነውን ህዝባችንን ልንክስ በአዴንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ክድተን ወጥተናል ብለዋል።

ያለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱ ዞኖች ፋኖን ከተቀላቀሉት ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት መካከል አብዛኻኞቹ ልዩ ኃይሉ ሳይፈርስ በፊት 2ኛና 3ኛ ዙር ሰልጥነው የመክት ብርጌድ፣ የጣና፣ የበላይ እና የመቅደላ ብርጌድ አባላት እንደነበሩ ለማረጋገጥ ችለዋል።

የአማራ ድምፅ
👍9413🥰1
በአማራ ፋኖ በጎንደር ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር።
👍23227🥰17🔥15
ኤርፖርቱ በፋኖ እጅ ገብቷል!

በላሊበላ ከተማ እና በላሊበላ አየር ማረፊያ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው!

በላሊበላ ኤርፖርትና በከተማዋ ዙሪያ ዛሬ ግንቦት 13/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በገዢው ቡድን ወታደሮች እና በላስታ ፋኖዎች መካከል በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዛሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ኤርፖርትና ላሊበላ ከተማን ጨምሮ በላስታ ወረዳ ስር ባሉ በአሸተን፣በቀጭን አበባ ፣ በቤተ አምበሳ ፣ በጣርስታ፣በሽምብርማና በሲመኖ አከባቢዎች ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ የአሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ታዘበው ሻምበል ገልጿል።

ከንጋት ጀምሮ እስካሁን እየተደረገ ባለው ውጊያ የብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ከባድ ኪሳራን ያስተናገዱ ሲሆን፡ ሙትና ቁስለኛ ወታደሮቹን በሁለትና ሦስት አምቡላንሶች እያነሳ ወደ ላሊበላ ከተማ እያጋዘ መሆኑንም ፋኖ ታዘበው ጨምሮ ገልጿል።

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያልቻለው የገዢው ቡድን ወታደር፡ ታሪካዊ ቅርሶች ባሉበት አከባቢ ከባባድ መሣሪያዎችን እየወረወረ መሆኑንም የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ከንጋት ጀምሮ ውጊያ ባልተካሄደባቸው የብልባላ እና የአይና ቡግና አከባቢዎች በመድፍ እየተደበደቡ ሲሆን በዚህም ብልባላ ጊዎርጊስን ጨምሮ ሌሎች ታሪካዊ ቅርሶች አደጋ ላይ መውደቃቸውን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች ጨምረው የገለፁት።

በላሊበላ ከተማ መካልት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የተጠመደው መድፍ የአይናቡግና እና የብልባላ አከባቢዎችን እየደበደበ ሲሆን በዚህም የመድፉ ቅምቡላ በታሪካዊው ብልባላ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቅርብ ርቀት እያረፈ ነው ተብሏል።

በተመሣሣይ በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የተጠመደው ከባድ መሣሪያ ደግሞ በአሸተን ማርያም፣ በቀንቀኒት ሚካኤል እና በቤተአምበሳ ማርያም ዙሪያ ያሉ አከባቢዎችን እየደበደበ ሲሆን በዚህም ቅርሶቹ ላይ ከባድ አደጋ መደቀኑም ተነግሯል።

ከአዲስ አበባና ሌሎች አከባቢዎች ወደ ላሊበላ የሚደረገው መደበኛ የአየር በረራ የተቋረጠ ሲሆን ኤርፖርቱ በፋኖ እጅ መግባቱንም የክ/ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ገልጿል።

በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የላስታ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ፋኖ ከሁለት ቀናት በፊት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጋዝጊብላ ወረዳ ከአስ ከተማ በቅርብ ርቀት የምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጄነራል አበባው ታደሰና የጄነራል ዘውዱ በላይ ትውልድ ቀየ በሆነችው አዲ በር ተብላ በምትጠራው አከባቢ ላይ ባደረገው ውጊያ በርካታ የገዢው ቡድን ወታደሮችን ሲገደል ከ70 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ማቁሰሉን ውጊያውን የመሩ የፋኖ አዛዦችን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን አይዘነጋም።የአማራ ድምፅ
👍1208🤯3👏2😢2
ጃዊ ዙሪያ ዛሬም ውጊያው እንደቀጠለ ነው!
👍60
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰራዊቱ እራስን የማዳን ሩጫ!..‼️‼️

ለግለሰቦች ስልጣን አይተኬ ህይወቴን አልገብርም በማለት የሰራዊቱ አባላት እጅ እየሰጡም እየተማረኩም ይገኛል። ለቤተሰቦቻችሁ መትረፍ በእራሱ ትልቅ እድለኝነትም ብልህነትም ነው።

አዎ ለበሰበሱ ባለስልጣናትና ለፈረሰ ስርዓት ውድ ህይወትክን አትገብር፤ በሰላም እጅ ስጡ፤ ህይወታችሁን አድኑ።
👍10017🥰7😱2
👍375🥰1
የአዲስ አበባው ኦፕሬሽንና የጎንደሩ ተጋድሎ
ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ያለው የጎንደር ፋኖ ዋና ዋና የጎንደር ከተሞችን በቅርብ ቀን ውስጥ ሊቆጣጠር እንደሚችል ጠቆመ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊና የፓርኮች አስተዳደር ሃላፊ ዶ/ር ታምራት ሃይሌ ከአካል ጥበቃና ሹፌሩ ገብረ እግዛቤር ጋር በነበረበት ወቅት ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡
በፋኖ ተፈጽሟል በተባለው  በዚህ ጥቃት የዶ/ር ታምራት ሃይሌ ጥበቃና ሹፌር የተገደለ ሲሆን ዶ/ር ታምራት ሃይሌ ግን ከጥቃቱ ለጥቂት መትረፉን ነው ጊዮን ሚዲያ የዘገበው፡፡
ዶ/ር ታምራት ሃይሌ የአብይ አስተዳደር ዋነኛ ቀኝ እጅ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ፣ ይህ ዜና ሲሰማ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ክፉኛ መረበሹና መደናገጡ ነው የተዘገበው፡፡
በመሆኑም ይህ ጉዳይ እንዳይወጣ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖ ኦፕሬሽንና ውጊያ በአማራ ክልልም የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለይም በሰሜናው ፣ ማዕከላዊና ደቡባዊ ጎንደር አካባቢ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተካሄደ ነው፡፡
ብልጽግና ለአንድ ወር የሚቆይ ኦፕሬሽን በፋኖ ላይ አደርጋለሁ በሚል በጀመረው ውጊያ ፋኖ ኦፕሬሽኑን ቀልብሶ የራሱን ጀብዱ እየፈጸመ ነው፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ እያሱ አባተ በበርካታ አካባቢዎች የብልጽግና ጦር ከበባ ውስጥ ገብቷል ብሏል፡፡
ከብልጽግና ጋር የተሰለፈው አድማ ብተና እና ሚሊሻም የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ እየገባ ነው ሲል ገልጿል፡፡
እያንዳንዱ የአማራ ፋኖ በጎንደር ክፍለጦር እየተናበበ ነው ውጊያውን እያደረገ ያለው የሚለው ቃል አቀባዩ በዚህም ታላቅ ድል እያገኘን ነው ብሏል፡፡
ፋኖ እያሱ አክሎም አገዛዙ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ጎንደርን ፣ ደብረታቦርን እና ዳባትን የሚያጣበት እድሉ ሰፊ ነው ያለ ሲሆን ሰሞነኛው ድልም የእነ ናሁሰናይ ፣ የእነ ውባንተን መስዋዕትነት የጠገነ ነው ሲል አስረድቷል፡፡
roha
👍1559😭4🤯1🤬1
ሰበር የድል ዜና :-
የአማራ ፋኖ በጎጃም የአንደኛ ክፍለጦር በሜጫ ወረዳ በሦሥት ቦታዎች የገባውን ጠላት አይቀጡ ቅጣት ቀጣው።
1. ወደ ደቡብ ሜጫ ወረዳ ገርጨጭ ለመውረር ተግተልትሎ የገባው የዘራፊው አብይ አህመድ ሰራዊት በነበልባሎች አለማየሁ ከቤ ሻለቃ መሪው በአስር አለቃ ዘውዱ እና ዘመቻ መሪው ኮማንዶ አስር አለቃ ሲሰራው ሹመት በመመራት ተግተልትሎ የገባውን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደመጣበት መልሰውታል።
2 . በሌላ አቅጣጫ ዳጊ ከተማን ለመውረር አሰፍስፎ የገባው የበርሀኑ ጁላ ጨፍጫፊ ሀይል በጀግኖቹ ጊወን ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ባለበት ቁሟል።

3. በሌላ አቅጣጫ ከአዴት ተነስቶ ብራቃት ከተማን ለማውደም የገባው የብርሀኑ ጁላ ዘር አጥፊ ሀይል በአይበገሬዎቹ አበራ ሙጨ ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ይገኛል። ሙሉሰው የኔአባት የአንደኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት።ስርዝር መረጃውን ከደቂቃወች በሗላ ይዘን እንመለሳለን
13/09/2016
👍535😢2
#ሰበር_የድል_ዜና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ ..‼️‼️

ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካምፖችን መደምሰስ መቻሉን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ገልጿል።

አሶል አካባቢ የሚገኘ የሚሊሻና የፀረ ሽምቅ ካምፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካመሰፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ኃይል ካምፕ ሙሉ በሙሉ የተመታ ሲሆን አድማ ብተና፣ ፀረሽምቅና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተደምስሷል ያለው ደግሞ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ሸጋ ጌታቸው ነው። የክፍለጦሩ አዛዥ ጨምሮ እንደገለጸውም ራሱን የመከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው ገዳይ ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካምፑን ጥሎ በመፈርጠጥ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን አቅጣጫ ፈርጥጧል ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባትና ወደ ጎረቤት ሱዳን ሀገር ከመሰደድ የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። የነብስ አውጭኙን በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ተናግሯል።

በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይጋኛል ሲል ሻለቃው ተናግሯል።
@የኢትዮ 251
👍8211👏4😢2
የከሸፈው የፋሽስታዊው አገዛዝ ዓላማ!

ጨቅላው አብይ አህመድ ጦሩን በጠቅላላ በአማራ ህዝብ ላይ ሲያዘምት፣ ዓላማው "የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ፣ ፋኖንም አጠፋለሁ" የሚል ነበር።

ይህንን ህልም ለማሳካት ጨቅላው አንድ ዓመት ኳትኗል። በዚህ ሂደት አገዛዙ ያለመውን አሳካ ወይ ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር ምላሽ "እንዲያውም ትልቅ ኪሳራን ተከናንቧል" የሚል ይሆናል።

︎"ትጥቅ አስፈታለሁ" አለ - ይልቁንም ፋኖ በእጅጉ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ታጠቀ፤

︎"ፋኖን እበትናለሁ" አለ - ይልቁንም ፋኖ እራሱን ከሻምበል፣ ሻለቃ፣ ብርጌድና ክፍለጦሮች አልፎም በእዝ ደረጃ አደራጅቶ ሃገራዊ የወታደራዊ ተቋም አቋም መያዝ ችሏል።

︎በአንጻሩ ደግሞ ትጥቅ ማዝፈታት ያሰበው የአብይ አህመድ ሰራዊት በርካታ ወታደራዊ ኃይሉን ገብሮ፣ በመፈረካከስ ላይ ይገኛል።

ይህ እንዳለ ሆኖ "ፋኖስ ግቡን እያሳካ ነው ወይ?" የሚለው ሌላኛው ጥያቄ ይሆናል። መልሱ አዎ ነው! ፋኖ ጥቂት ጀምሮ፣ በጥቂቱ ታጥቆ አሁን ግን ደርጅቶና ተደራጅቶ… ይህንን ፋሽስታዊ ስርዓት ለመገርሰስ ወደፊት ያለው ጉዞው ቀጥሏል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍6913🙏4😢2
የአማራ ክልሉ ተጋድሎ

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብልጽግና ሃይል በተደመሰሰባት የላሊበላ ከተማ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩ ተገለጸ
በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ላሊበላ ከተማ በትናንትናው እለት ፋኖ ወደ ከተማዋ በመዝለቅ አውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን በመያዝ በአገዛዙ ጦር ላይ ኦፕሬሽን መስራቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በዛሬው ማለዳ ሁሉም በየቤቱ ሆኖ ሁኔታውን እየተከታተለ ሲሆን ትላንት በነበረው ውጊያ ከተፋላሚ ኃይሎች ባሻገር መከላከያ በከባድ መሣሪያ ስድስት ንፁሐንን ገድሏል። 
ትላንት ከቀኑ 11:30 ገደማ የፋኖ ኃይሎች የቅዱስ ላሊበላ አየር ማረፊያን ከስድስት ሰዓታት ቁጥጥር በኋላ ለቀው ወጥተዋል።
በዚህም ከ87 በላይ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን የወሰዱ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ወደ ቅዲስ ላሊበላ የአየር በረራ አለመኖሩም ተመላክቷል፡፡
በትላንትናው ውጊያ እስከ 70 የሚደርሱ የመንግሥት ኃይሎች ሙት ሲሆኑ በውል ቁጥራቸው ያልታወቀ ቁስለኛ ሆነዋል።
በሌላ በኩል በጉና በጌምድር ትላንት እኩለ ቀን ላይ እንደገና የተቀሰቀሰው ከባድ ውጊያ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ቀጥሎ አድሯል። 
በዚህ ከባድ ውጊያ የደረሰውን ዝርዝር ጉዳት ማወቅ አልተቻለም።
በምግብ ቤት ይመገቡ የነበሩ አራት ንፁሃን በአድማ ብተና የተገደሉ ሲሆን ፣ ከሁለት ቀናት በፊት በነበረው ውጊያ ከ45 በላይ የመንግስት ኃይሎች ላይ ጉዳት  መድረሱ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። 
ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካምፖችን መደምሰስ መቻሉን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።
አሶል አካባቢ የሚገኝ የሚሊሻና የፀረ ሽምቅ ካምፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካምፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ኃይል ካምፕ ሙሉ በሙሉ የተመታ ሲሆን አድማ ብተና፣ ፀረሽምቅና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተደምስሷል ያለው ደግሞ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ሸጋ ጌታቸው ነው። 
የክፍለጦሩ አዛዥ እንደገለጸውም ራሱን የመከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው  ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካምፑን ጥሎ ወደ ሱዳን ገብቷል ብሏል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባትና ወደ ጎረቤት ሱዳን ሀገር ከመሰደድ የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። 
በነብስ አውጭኝ ሽሽት በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ተናግሯል፡፡
በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይገኛል ሲልም ገልጿል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍3822🥰2
በትናንቱ የላሊበላ ውጊያ ፋኖዎች ምን አይነት ድል ቀናቸው?

ትናንት ግምቦት 13/2016 ዓ/ም ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ላሊበላ ከተማ ዙሪያ እና በላሊበላ አየር ማረፊያ ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ በኤርፖርቱ የነበረ የጥይት ዲፖ ተሰብሮ በቁጥር ከ70 በላይ የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ በፋኖ እጅ መግባቱን በወሎ ዕዝ የላስታ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው ገልጿል።

በተጨማሪም በቁጥር ከ10 ሺ በላይ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ተተኳሽ ጥይት በፋኖ እጅ የገባ ሲሆን አስቃጥላና ሌሎች ወታደራዊ ስንቆችንም ማርከናል ሲል ቃል አቀባዩ ጨምሮ ገልጿል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 61ኛ፣65ኛና 12ኛ ክፍለ ጦሮች በውጊያው የተሳተፉ ቢሆንም ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው የሦስቱም ክ/ጦር ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነው የተረፉት ወደ ኋላ ማፈግፈጋቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

በፋኖ በኩል በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ስር የሚገኙ ማዕረጉ ተማረ፣ ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ ሻለቃ ውባንተ አባተ የተባሉ ሦስት ብርጌዶች የተሳተፉ ሲሆን በጣት የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከመቁሰላቸው ውጭ ጉዳት እንዳልደረሰ ነው ፋኖ ሞገስ አባራው የገለፀው።

በውጊያው ከሦስት በላይ አላማዎችን አሳክተንበታል ያለው የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ፡ የመጀመሪያው አላማችን የጠላትን ኃይል ማመናመንና ስነልቦናውን መስበር፣ ሁለተኛ አላማችን የወረዳው አመራሮች ፋኖ ፈርሷል፣ ምንም አይነት ውጊያ ማድረግ አይችልም በሚል ከሰሞኑ በላሊበላ ከተማ የበተኑት ሀሰተኛ በራሪ ወርቀትን በሚመለከት እውነታውን ለህዝባችን ማሳየት፣ ሦስተኛው አላማችን ትጥቅና ስንቅ ማገኘት ነበር እሱም ከበቂ በላይ በእጃችን ገብቷል ብሏል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍586
ገዢው ቡድን ሐይማኖታዊ ክብረ በዓላትን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመባቸዉ ነዉ ተባለ!

በአቡነ ሃራ ገዳም ይህን መሰል ድርጊቱን ተጠቅሞ ምዕመናን ላይ ግፍ መፈፀሙን ለማረጋገጥ ችለዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ የሚገኘዉ የአቡነ ሃራ አንድነት ገዳም ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉን ተከትሎ መንግስት ሀይማኖታዊ ክበረ በዓላትን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም በማዋሉ ምዕመናኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሷል ሲል ገዳሙ አስታውቋል።

በየዓመቱ ግንቦት 11የሚከበረዉ የአቡነ ሃራ አንድነት ገዳም በአሉ ከዚህ በፊት ሲከበር ያለምን የፀጥታ ችግር ሲሆን ነገር ግን በዚህ ዓመት ገዳሙ በዓሉን ያሳለፈዉ በአስቸጋሪ ሁኔታ እንደሆነ የገዳሙ አባቶች ገልፀዋል።

የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ጥሪ ሳናደርግላቸዉ ወደ ገዳሙ ከመጡ በኋላ ችግር ፈጥረውብናል፣ ምዕመኖቻችንላይም ግድያ ፈፅመዋል፣ መንግስት እንደዚህ አይነቱን ድርጊት ሲፈፅም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አለመሆኑን የገዳሙ አባቶች ተናግረዋል።

በአሉን ለማክበር ወደ ገዳሙ የሄዱት ምዕመናን በበኩላቸዉ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በሀይማኖት ጣልቃ እየገቡ ምዕመናኑን ግፍ እየፈፀሙበት ነዉ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ህዝቡን ከፋኖ ሀይሎች ለመነጠል በሚል የቂል ፕለቲካ በማራመዳቸዉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍411
#ሰበር_ወለጋ

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ከቱሉገና ከተማ ወጣ ብሎ ጫንጫ ተብሎ የሚጣራው አካባቢ የአገዛዙ ሊኮፍተር ዝቅ ብላ አሰሳ እያደረገች ባለችበት ስዓት ምን አደጋ እንደደረሰባት ለግዜው ባይታዎቅም ከአፈር ተቀላቅላለች ሲሉ የካባቢው ኗሪዎች ገልጸዋል።

በኢራን ላይ የደረሰው የሂልኮቭተር መከስከስ
በረከቱ በብልፅግናም እንደሚደርስ ጠቋሚ ነው።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍6612🔥8
በአገዛዙ ውድቀት የተራበው ከተሜውና የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ብቻ አይደለም።

የአገዛዙ ጦር  ርሃብ ላይ ነው። አንድ ከፍተኛ ማዕረግ ያለው ወታደራዊ መኮንን በመኮንኖች ስልጠና ላይ ቢገኝም ወላጅ ቤተሰቦቹን ገንዘብ ላኩልኝ እያለ ሲላክ አውቃለሁ። በቅርብ ሰሞን የሆነ ነው። ጦሩ እየተራበ ነው። ሻለቆችና ኮለኔሎችን ጨምሮ!!
ተራው ወታደር ዘርፈህ ብላ ተብሏል። The largest elite army ግን በዚያው ደጋ ዳሞት ጠፍታ ቀረች አይደል።

-
በኦሮሚያ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሐረርጌ በግድ እየተጫነ ወደማሰልጠኛ የሚገባው ወጣት በርካታ ነው።
አፈሳው በሁለት መልኩ እየተፈፀመ ነው።
አንዱ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ የሚገባ አፈሳ ሲሆን ሁለተኛው የግዳጅ ዘመቻ እየተሠራ ያለው አዲስአበባ ዙሪያ ነው።
<< የሥርዓቱ ዘብ >> በሚል ልክ እንደሁቱ ሚሊሻ እየሠለጠነ ያለው ሕዝብ ከፍተኛ ነው።
አላማው አዲስአበባ የሚመጣን ታጋይ መመከት ነው ቢባልም ሕዝብን ከሕዝብ የማጨፋጨፍ አላማ የያዘ እንጂ ወታደራዊ ትርጉም ያለው አይደለም።

--
የአገዛዙ ሠራዊት አንድ ከፍተኛ ትኩረት የተሠጠው የሥራ ክፍል አደራጅቷል። የሚከዱና የሚኮበልሉ ወታደሮች ጥበቃና ክትትል ክፍል ነው።
እግዚኦ ነው መቼስ!!
የወታደራዊ መረጃ መምሪያ አንዱ ሥራ ሠራዊቱ ውስጥ ሊከዳ የሚፈልግ፣ የሚሞክር ወዘተ መከታተልና በዚህ ተጠርጥረው በመላ አገሪቱ የታሠሩ ወታደሮችን ፍርድ ማስፈፀም ነው።

ብርሃኑ ጁላ በእምነት ሳይሆን በክትትልና ጥበቃ የሚሰነብት ወታደር ፈጥሮልን አረፈው !!


ድል ለሕዝባዊው የአማራ ትግል
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍41