Ashara Media - አሻራ ሚዲያ – Telegram
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
79.3K subscribers
24.7K photos
1.17K videos
24 files
9.65K links
ስልክ፥ +251984000629 / +251993111700
Download Telegram
👍375🥰1
የአዲስ አበባው ኦፕሬሽንና የጎንደሩ ተጋድሎ
ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ያለው የጎንደር ፋኖ ዋና ዋና የጎንደር ከተሞችን በቅርብ ቀን ውስጥ ሊቆጣጠር እንደሚችል ጠቆመ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊና የፓርኮች አስተዳደር ሃላፊ ዶ/ር ታምራት ሃይሌ ከአካል ጥበቃና ሹፌሩ ገብረ እግዛቤር ጋር በነበረበት ወቅት ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡
በፋኖ ተፈጽሟል በተባለው  በዚህ ጥቃት የዶ/ር ታምራት ሃይሌ ጥበቃና ሹፌር የተገደለ ሲሆን ዶ/ር ታምራት ሃይሌ ግን ከጥቃቱ ለጥቂት መትረፉን ነው ጊዮን ሚዲያ የዘገበው፡፡
ዶ/ር ታምራት ሃይሌ የአብይ አስተዳደር ዋነኛ ቀኝ እጅ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ፣ ይህ ዜና ሲሰማ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ክፉኛ መረበሹና መደናገጡ ነው የተዘገበው፡፡
በመሆኑም ይህ ጉዳይ እንዳይወጣ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖ ኦፕሬሽንና ውጊያ በአማራ ክልልም የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለይም በሰሜናው ፣ ማዕከላዊና ደቡባዊ ጎንደር አካባቢ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተካሄደ ነው፡፡
ብልጽግና ለአንድ ወር የሚቆይ ኦፕሬሽን በፋኖ ላይ አደርጋለሁ በሚል በጀመረው ውጊያ ፋኖ ኦፕሬሽኑን ቀልብሶ የራሱን ጀብዱ እየፈጸመ ነው፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ እያሱ አባተ በበርካታ አካባቢዎች የብልጽግና ጦር ከበባ ውስጥ ገብቷል ብሏል፡፡
ከብልጽግና ጋር የተሰለፈው አድማ ብተና እና ሚሊሻም የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ እየገባ ነው ሲል ገልጿል፡፡
እያንዳንዱ የአማራ ፋኖ በጎንደር ክፍለጦር እየተናበበ ነው ውጊያውን እያደረገ ያለው የሚለው ቃል አቀባዩ በዚህም ታላቅ ድል እያገኘን ነው ብሏል፡፡
ፋኖ እያሱ አክሎም አገዛዙ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ጎንደርን ፣ ደብረታቦርን እና ዳባትን የሚያጣበት እድሉ ሰፊ ነው ያለ ሲሆን ሰሞነኛው ድልም የእነ ናሁሰናይ ፣ የእነ ውባንተን መስዋዕትነት የጠገነ ነው ሲል አስረድቷል፡፡
roha
👍1559😭4🤯1🤬1
ሰበር የድል ዜና :-
የአማራ ፋኖ በጎጃም የአንደኛ ክፍለጦር በሜጫ ወረዳ በሦሥት ቦታዎች የገባውን ጠላት አይቀጡ ቅጣት ቀጣው።
1. ወደ ደቡብ ሜጫ ወረዳ ገርጨጭ ለመውረር ተግተልትሎ የገባው የዘራፊው አብይ አህመድ ሰራዊት በነበልባሎች አለማየሁ ከቤ ሻለቃ መሪው በአስር አለቃ ዘውዱ እና ዘመቻ መሪው ኮማንዶ አስር አለቃ ሲሰራው ሹመት በመመራት ተግተልትሎ የገባውን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደመጣበት መልሰውታል።
2 . በሌላ አቅጣጫ ዳጊ ከተማን ለመውረር አሰፍስፎ የገባው የበርሀኑ ጁላ ጨፍጫፊ ሀይል በጀግኖቹ ጊወን ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ባለበት ቁሟል።

3. በሌላ አቅጣጫ ከአዴት ተነስቶ ብራቃት ከተማን ለማውደም የገባው የብርሀኑ ጁላ ዘር አጥፊ ሀይል በአይበገሬዎቹ አበራ ሙጨ ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ይገኛል። ሙሉሰው የኔአባት የአንደኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት።ስርዝር መረጃውን ከደቂቃወች በሗላ ይዘን እንመለሳለን
13/09/2016
👍535😢2
#ሰበር_የድል_ዜና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ ..‼️‼️

ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካምፖችን መደምሰስ መቻሉን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ገልጿል።

አሶል አካባቢ የሚገኘ የሚሊሻና የፀረ ሽምቅ ካምፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካመሰፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ኃይል ካምፕ ሙሉ በሙሉ የተመታ ሲሆን አድማ ብተና፣ ፀረሽምቅና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተደምስሷል ያለው ደግሞ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ሸጋ ጌታቸው ነው። የክፍለጦሩ አዛዥ ጨምሮ እንደገለጸውም ራሱን የመከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው ገዳይ ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካምፑን ጥሎ በመፈርጠጥ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን አቅጣጫ ፈርጥጧል ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባትና ወደ ጎረቤት ሱዳን ሀገር ከመሰደድ የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። የነብስ አውጭኙን በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ተናግሯል።

በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይጋኛል ሲል ሻለቃው ተናግሯል።
@የኢትዮ 251
👍8211👏4😢2
የከሸፈው የፋሽስታዊው አገዛዝ ዓላማ!

ጨቅላው አብይ አህመድ ጦሩን በጠቅላላ በአማራ ህዝብ ላይ ሲያዘምት፣ ዓላማው "የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ፣ ፋኖንም አጠፋለሁ" የሚል ነበር።

ይህንን ህልም ለማሳካት ጨቅላው አንድ ዓመት ኳትኗል። በዚህ ሂደት አገዛዙ ያለመውን አሳካ ወይ ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር ምላሽ "እንዲያውም ትልቅ ኪሳራን ተከናንቧል" የሚል ይሆናል።

︎"ትጥቅ አስፈታለሁ" አለ - ይልቁንም ፋኖ በእጅጉ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ታጠቀ፤

︎"ፋኖን እበትናለሁ" አለ - ይልቁንም ፋኖ እራሱን ከሻምበል፣ ሻለቃ፣ ብርጌድና ክፍለጦሮች አልፎም በእዝ ደረጃ አደራጅቶ ሃገራዊ የወታደራዊ ተቋም አቋም መያዝ ችሏል።

︎በአንጻሩ ደግሞ ትጥቅ ማዝፈታት ያሰበው የአብይ አህመድ ሰራዊት በርካታ ወታደራዊ ኃይሉን ገብሮ፣ በመፈረካከስ ላይ ይገኛል።

ይህ እንዳለ ሆኖ "ፋኖስ ግቡን እያሳካ ነው ወይ?" የሚለው ሌላኛው ጥያቄ ይሆናል። መልሱ አዎ ነው! ፋኖ ጥቂት ጀምሮ፣ በጥቂቱ ታጥቆ አሁን ግን ደርጅቶና ተደራጅቶ… ይህንን ፋሽስታዊ ስርዓት ለመገርሰስ ወደፊት ያለው ጉዞው ቀጥሏል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍6913🙏4😢2
የአማራ ክልሉ ተጋድሎ

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብልጽግና ሃይል በተደመሰሰባት የላሊበላ ከተማ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩ ተገለጸ
በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ላሊበላ ከተማ በትናንትናው እለት ፋኖ ወደ ከተማዋ በመዝለቅ አውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን በመያዝ በአገዛዙ ጦር ላይ ኦፕሬሽን መስራቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በዛሬው ማለዳ ሁሉም በየቤቱ ሆኖ ሁኔታውን እየተከታተለ ሲሆን ትላንት በነበረው ውጊያ ከተፋላሚ ኃይሎች ባሻገር መከላከያ በከባድ መሣሪያ ስድስት ንፁሐንን ገድሏል። 
ትላንት ከቀኑ 11:30 ገደማ የፋኖ ኃይሎች የቅዱስ ላሊበላ አየር ማረፊያን ከስድስት ሰዓታት ቁጥጥር በኋላ ለቀው ወጥተዋል።
በዚህም ከ87 በላይ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን የወሰዱ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ወደ ቅዲስ ላሊበላ የአየር በረራ አለመኖሩም ተመላክቷል፡፡
በትላንትናው ውጊያ እስከ 70 የሚደርሱ የመንግሥት ኃይሎች ሙት ሲሆኑ በውል ቁጥራቸው ያልታወቀ ቁስለኛ ሆነዋል።
በሌላ በኩል በጉና በጌምድር ትላንት እኩለ ቀን ላይ እንደገና የተቀሰቀሰው ከባድ ውጊያ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ቀጥሎ አድሯል። 
በዚህ ከባድ ውጊያ የደረሰውን ዝርዝር ጉዳት ማወቅ አልተቻለም።
በምግብ ቤት ይመገቡ የነበሩ አራት ንፁሃን በአድማ ብተና የተገደሉ ሲሆን ፣ ከሁለት ቀናት በፊት በነበረው ውጊያ ከ45 በላይ የመንግስት ኃይሎች ላይ ጉዳት  መድረሱ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። 
ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካምፖችን መደምሰስ መቻሉን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።
አሶል አካባቢ የሚገኝ የሚሊሻና የፀረ ሽምቅ ካምፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካምፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ኃይል ካምፕ ሙሉ በሙሉ የተመታ ሲሆን አድማ ብተና፣ ፀረሽምቅና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተደምስሷል ያለው ደግሞ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ሸጋ ጌታቸው ነው። 
የክፍለጦሩ አዛዥ እንደገለጸውም ራሱን የመከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው  ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካምፑን ጥሎ ወደ ሱዳን ገብቷል ብሏል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባትና ወደ ጎረቤት ሱዳን ሀገር ከመሰደድ የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። 
በነብስ አውጭኝ ሽሽት በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ተናግሯል፡፡
በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይገኛል ሲልም ገልጿል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍3822🥰2
በትናንቱ የላሊበላ ውጊያ ፋኖዎች ምን አይነት ድል ቀናቸው?

ትናንት ግምቦት 13/2016 ዓ/ም ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ላሊበላ ከተማ ዙሪያ እና በላሊበላ አየር ማረፊያ ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ በኤርፖርቱ የነበረ የጥይት ዲፖ ተሰብሮ በቁጥር ከ70 በላይ የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ በፋኖ እጅ መግባቱን በወሎ ዕዝ የላስታ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው ገልጿል።

በተጨማሪም በቁጥር ከ10 ሺ በላይ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ተተኳሽ ጥይት በፋኖ እጅ የገባ ሲሆን አስቃጥላና ሌሎች ወታደራዊ ስንቆችንም ማርከናል ሲል ቃል አቀባዩ ጨምሮ ገልጿል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 61ኛ፣65ኛና 12ኛ ክፍለ ጦሮች በውጊያው የተሳተፉ ቢሆንም ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው የሦስቱም ክ/ጦር ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነው የተረፉት ወደ ኋላ ማፈግፈጋቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።

በፋኖ በኩል በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ስር የሚገኙ ማዕረጉ ተማረ፣ ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ ሻለቃ ውባንተ አባተ የተባሉ ሦስት ብርጌዶች የተሳተፉ ሲሆን በጣት የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከመቁሰላቸው ውጭ ጉዳት እንዳልደረሰ ነው ፋኖ ሞገስ አባራው የገለፀው።

በውጊያው ከሦስት በላይ አላማዎችን አሳክተንበታል ያለው የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ፡ የመጀመሪያው አላማችን የጠላትን ኃይል ማመናመንና ስነልቦናውን መስበር፣ ሁለተኛ አላማችን የወረዳው አመራሮች ፋኖ ፈርሷል፣ ምንም አይነት ውጊያ ማድረግ አይችልም በሚል ከሰሞኑ በላሊበላ ከተማ የበተኑት ሀሰተኛ በራሪ ወርቀትን በሚመለከት እውነታውን ለህዝባችን ማሳየት፣ ሦስተኛው አላማችን ትጥቅና ስንቅ ማገኘት ነበር እሱም ከበቂ በላይ በእጃችን ገብቷል ብሏል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍586
ገዢው ቡድን ሐይማኖታዊ ክብረ በዓላትን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመባቸዉ ነዉ ተባለ!

በአቡነ ሃራ ገዳም ይህን መሰል ድርጊቱን ተጠቅሞ ምዕመናን ላይ ግፍ መፈፀሙን ለማረጋገጥ ችለዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ የሚገኘዉ የአቡነ ሃራ አንድነት ገዳም ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉን ተከትሎ መንግስት ሀይማኖታዊ ክበረ በዓላትን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም በማዋሉ ምዕመናኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሷል ሲል ገዳሙ አስታውቋል።

በየዓመቱ ግንቦት 11የሚከበረዉ የአቡነ ሃራ አንድነት ገዳም በአሉ ከዚህ በፊት ሲከበር ያለምን የፀጥታ ችግር ሲሆን ነገር ግን በዚህ ዓመት ገዳሙ በዓሉን ያሳለፈዉ በአስቸጋሪ ሁኔታ እንደሆነ የገዳሙ አባቶች ገልፀዋል።

የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ጥሪ ሳናደርግላቸዉ ወደ ገዳሙ ከመጡ በኋላ ችግር ፈጥረውብናል፣ ምዕመኖቻችንላይም ግድያ ፈፅመዋል፣ መንግስት እንደዚህ አይነቱን ድርጊት ሲፈፅም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አለመሆኑን የገዳሙ አባቶች ተናግረዋል።

በአሉን ለማክበር ወደ ገዳሙ የሄዱት ምዕመናን በበኩላቸዉ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በሀይማኖት ጣልቃ እየገቡ ምዕመናኑን ግፍ እየፈፀሙበት ነዉ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ህዝቡን ከፋኖ ሀይሎች ለመነጠል በሚል የቂል ፕለቲካ በማራመዳቸዉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍411
#ሰበር_ወለጋ

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ከቱሉገና ከተማ ወጣ ብሎ ጫንጫ ተብሎ የሚጣራው አካባቢ የአገዛዙ ሊኮፍተር ዝቅ ብላ አሰሳ እያደረገች ባለችበት ስዓት ምን አደጋ እንደደረሰባት ለግዜው ባይታዎቅም ከአፈር ተቀላቅላለች ሲሉ የካባቢው ኗሪዎች ገልጸዋል።

በኢራን ላይ የደረሰው የሂልኮቭተር መከስከስ
በረከቱ በብልፅግናም እንደሚደርስ ጠቋሚ ነው።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍6612🔥8
በአገዛዙ ውድቀት የተራበው ከተሜውና የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ብቻ አይደለም።

የአገዛዙ ጦር  ርሃብ ላይ ነው። አንድ ከፍተኛ ማዕረግ ያለው ወታደራዊ መኮንን በመኮንኖች ስልጠና ላይ ቢገኝም ወላጅ ቤተሰቦቹን ገንዘብ ላኩልኝ እያለ ሲላክ አውቃለሁ። በቅርብ ሰሞን የሆነ ነው። ጦሩ እየተራበ ነው። ሻለቆችና ኮለኔሎችን ጨምሮ!!
ተራው ወታደር ዘርፈህ ብላ ተብሏል። The largest elite army ግን በዚያው ደጋ ዳሞት ጠፍታ ቀረች አይደል።

-
በኦሮሚያ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሐረርጌ በግድ እየተጫነ ወደማሰልጠኛ የሚገባው ወጣት በርካታ ነው።
አፈሳው በሁለት መልኩ እየተፈፀመ ነው።
አንዱ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ የሚገባ አፈሳ ሲሆን ሁለተኛው የግዳጅ ዘመቻ እየተሠራ ያለው አዲስአበባ ዙሪያ ነው።
<< የሥርዓቱ ዘብ >> በሚል ልክ እንደሁቱ ሚሊሻ እየሠለጠነ ያለው ሕዝብ ከፍተኛ ነው።
አላማው አዲስአበባ የሚመጣን ታጋይ መመከት ነው ቢባልም ሕዝብን ከሕዝብ የማጨፋጨፍ አላማ የያዘ እንጂ ወታደራዊ ትርጉም ያለው አይደለም።

--
የአገዛዙ ሠራዊት አንድ ከፍተኛ ትኩረት የተሠጠው የሥራ ክፍል አደራጅቷል። የሚከዱና የሚኮበልሉ ወታደሮች ጥበቃና ክትትል ክፍል ነው።
እግዚኦ ነው መቼስ!!
የወታደራዊ መረጃ መምሪያ አንዱ ሥራ ሠራዊቱ ውስጥ ሊከዳ የሚፈልግ፣ የሚሞክር ወዘተ መከታተልና በዚህ ተጠርጥረው በመላ አገሪቱ የታሠሩ ወታደሮችን ፍርድ ማስፈፀም ነው።

ብርሃኑ ጁላ በእምነት ሳይሆን በክትትልና ጥበቃ የሚሰነብት ወታደር ፈጥሮልን አረፈው !!


ድል ለሕዝባዊው የአማራ ትግል
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍41
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ዛሬ ያወጣው መግለጫ  ከላይ ተያይዟል።
ኮሚቴው
<<የወሰንና ማንነት ጥያቄችንን በዚህ መሰል ሁኔታዎች ማዳፈን እንደማይቻል የመጣንበነት የትግል መንገድ ምስክር ነው፡፡

ሕዝባችን በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን እንኳ ለነጻነትና ለክበሩ ይፋለማል፡፡

በባህላቻን እጅ መንሳት እንጂ፤ እጅ መስጠት አናውቅም!! ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት፤ ዳግም የሚወረር መሬት የለም!!የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ።ማይጠምሪ-ጎንደር ።
ግንቦት 13/2016
👍5211🤯1🤬1
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Photo
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ኮሚቴው

"ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት፤ ዳግም የሚወረር መሬት የለም!!"

በሚል ርዕስ ነው መግለጫውን ያወጣው።

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

➡️ የምስራቅ ጠለምት ሦስት ቀበሌዎች እና ግማሽ የአንድ ቀበሌ ቦታ ማለትም፡- ‹ደገብራይ›፣ ‹ሜዳ›፣ ‹ሀምሾምድር› እና ‹ጥርሰጌ› የተባሉት ቀበሌዎች እስካሁን ነጻ እንዳልወጡ፤

በእነዚህ አካባቢዎች ወያኔ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሆነ፤

ወያኔ ከሕግ አግባብ ውጭ ሲንቀሳቀስ የፌዴራል መንግሥቱ ይህ ነው የሚባል እርምት እርምጃም ሆነ ማስተባበያ ሲሰጥ አለመታዩ፡፡

በዚህም ይህ ሁኔታ በወያኔ በኩል እያደገ ሂዶ ራያን በኃይል በመውረር የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ ጥሶታል፡፡ 

ወያኔ ይህን ያደረገው ችግሮችን በሰላም ከመፍታት ይልቅ በጉልበት የመፍታት ፍላጎት ስላለው እንደሆነ፤

በዚህ ድርጊቱ ይህ ነው የሚባል ተቃውሞም ሆነ አጸፋዊ ምላሽ ያልተሰጠው በመሆኑ ተመሳሳይ ወረራ በጠለምት እና በወልቃይት-ጠገዴ አካባቢው እያሰበ እንደሚገኝ፤

ስለሆነም፦

እኛ የጠለምት አማራዎች ይህንን ሁኔታ በማየት ሕዝባችን ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲጠቀም ጥሪ ለማቅረብ እንገደዳለን፡፡  በማለት ጥሪ አቅርቧል።

መግለጫው በተጨማሪ

በተጨባጭ እንደሚታየው በወያኔ በኩል አሁንም ጠባጫሪነቱ አለመገደቡን፣ በዚህም ኮሚቴው ወያኔ በምስራቅ ጠለምት በኩል የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን በልዩ ትኩረት ለማየት እንደሚገደድ፤

በመሆኑም፡-

  ➡️ የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ  ያቀረበው የማንነት ጥያቄ በዘለቄታው የማይመለስለት ከሆነ ሕዝቡ ራሱን ለዳግም ባርነት አሳልፎ እንደማይሰጥ፤


➡️ ትሕነግ አሁንም በራያ ያካሄደውን የጦር ወረራ በጠለምት፣ እንዲሁም በወልቃይት-ጠገዴ ለመድገም የቀየሰው ስልት፡- ከፊት ተፈናቃይ የሚለው  አካል በማስቀደም በግራና በቀኝ የራሱ “የትግራይ ፀጥታ ኃይል" ብሎ እያሰለጠነና እያደራጀ፤ የተደራጁ ኃይሎቹን  ለማስገባት  ሙሉ ዝግጅት ላይ ነው።

የፌዴራል መንግሥትም በዚህ ላይ የተለሳለሰ አቋም እያሳየ በመሆኑ ህዝብ እያስቆጣ ይገኛል። ሕዝባችንም የራሱን ተፈጥሯዊ የመከላከል መብቱን ለመጠቀም የሚገደድ በመሆኑ ራሱን ለሁንተናዊ ትግል እንዲያዘጋጅ እናደርጋለን!! 

➡️ የጠለምት፣ ራያና ወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን በዘላቂነት እንዲጸና ስትታገል የቆየህው መላው የአማራ ሕዝብና ዲያስፖራ ወገናችን በሙሉ፡- ወራሪውና ዘራፊው የትሕነግ ቡድን የሚያደርገውን የትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን በመገንዘብ ይህን የጥፋት ዓላማውን ለማምከን በሚደረገው ትግል ተሳትፏችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ታሪካዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 

➡️ የአማራ ሕዝብ ለዘመናት ሲታገልላቸው የኖሩ ሦስቱም የአማራ ታሪካዊ ርስቶች ማለትም ጠለምት፣ ራያ እና ወልቃይት-ጠገዴ ከማንነትና ከርስት ባሻገር ቁልፍ አገራዊ የህልውና ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች በትሕነግ እጅ ዳግም ከወደቁ ድርጅቱ ለረዥም ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን የመገንጠል አጀንዳውን እውን እንደሚያደርገው ታውቆ እነዚህ ግዛቶች የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ህልውና ቁልፍ ጉዳዩች ሆነው መታየት እንዳለባቸው፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚወዱ ወገኖች ሁሉ የትግላችን አጋር እንዲሆኑ ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 

➡️ ባለፉት ሦስት ዓመታት የካፒታልና የመደበኛ በጀት ክልከላ ተደርጎብን፤ በበጀት ክልከላ የሚጣል ማንነት እንደሌለን በጽናት ቆመን አሳይተናል፡፡ ለአማራ ማንነታችን ከዚህ በላይም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡ 

በመርህ ደረጃ የሕዝቡ የመልማት ጥያቄና ፍትሃዊ  ተገቢነት ያለው የሪሶርስ አጠቃቀም ጊዜ የማይሰጠውና በፖለቲካ አስተዳደር ምክንያት የማይገደብ በመሆኑ የበጀትና የመሰረታዊ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ መጠየቃችንን አናቆምም፡፡ 

የወሰንና ማንነት ጥያቄችንን በዚህ መሰል ሁኔታዎች ማዳፈን እንደማይቻል የመጣንበነት የትግል መንገድ ምስክር ነው፡፡

➡️ ሕዝባችን በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን እንኳ ለነጻነትና ለክበሩ ይፋለማል፡፡ በባህላቻን እጅ መንሳት እንጂ፤ እጅ መስጠት አናውቅም!! ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት፤ ዳግም የሚወረር መሬት የለም!!

በማለት የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ጠንካራ መግለጫውን ከማይጠምሪ-ጎንደር አውጥቷል።

ግንቦት 15/2016
👍475🤯2
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ትላንት ሚያዚያ 12/09/2016ዓ.ም አመሻሸ 11:30 ገደማ ጀምሮ እስከ ምሽት12:30 ድረስ በተለምዶ ኬላ ወይም ጊወርጊስ መገንጠያ አከባቢ እና በ04 ቀበሌ  ልዩ ሃይል ከምፕ አከባቢ ከባድ የተኩስ ድምፅ እንደነበር እና በዚህ ተኩስ 8የሚጠጉ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
በተለይ 04 ቀበሌው ጋር አምስት ሰዎች አስኬረናቸው አስፓልት ላይ ተጥሎ ተመልክተናል ብለዋል።
እንዲሁም ጊወርጊስ መገንጠያ እና ፍርፍርም በሚባል ቦታ በተባራሪ ጥይት  የሞቱ አሉ ብለዋል። ተኩሱ የተከፈተው ሰው የዕለት ከዕለት ተግባሩን ከውኖ በሚገባበት ሰዓት በመሆኑ ለጉዳቱ መባባስ እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰዋል። በከተማዋ መደበኛ የባጃጅ እና የሰዉ እንቅስቃሴ ግን እንደቀጠለ ነው ብለዋል።
👍19😱2
ጥብቅ መልዕክት ከአማራ ፋኖ በጎጃም‼️
በመላው አማራ ክልል የምትገኙ ማንኛውም የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች በሙሉ !
ከነገ ማለትም ከግንቦት15/2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል "የአማራ ፋኖ በጎጃም" ጥብቅ ትዕዛዝ አውርዷል።
ከዛሬ በፊት ለስምሪት የወጣ ተሽከርካሪ ካለም በአለበት አካባቢ እንዲቆም እያሳሰብን ይህንን ትእዛዝ ወይም መልዕክት ጥሶ የተገኘ"በቀጠናው የሚገኝ ፋኖ ለሚወስደው እርምጃ ሀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናሳስባለን!
የአማራ ፋኖ በጎጃም ‼️
👍1157🥰2
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ

ትናንት በደቡባዊ ጎንደር በነበረው አውደ ውጊያ በሻለቃ ፀዳሉ ደሴ የሚመራዉ  ጀነራል ተገኝ ክፍለ ጦር ጉና በየጌምድር ግንባር ከፈተኛ ድል አሰመዝግቧል።
ሌኛዉ የሻለቃ ተሾመ የሚመራዉ ጣይቱ ከፍለ ጦር በእሰቴ ግንባር  በ3 ቦታ ከጠላት ጋር ሲፋለም ዉሏል  ።
👍8411👏8🥰7🔥1