Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በናይሮቢ የሰላም ስምምነቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርግ የነበረው የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

በመንግሥትና ህወሓት መካከል የተፈረመውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ በናይሮቢ የሰላም ስምምነቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርግ የነበረው የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተደረገውን ውይይት አጠናቀውና ተፈራርመው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሠዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትና ባለወታደራዊ ማዕረጎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በውብሸት ሰንደቁ
"በናይሮቢ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አተገባበር ለመፈፀም በሙሉ ልብ ዝግጁ ነን"
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በደቡብ አፍሪካ በመንግሥትና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርግ የነበረው ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ተደርጎለታል።

ከአቀባበሉ በኋላ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ፤ "በናይሮቢ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አተገባበር ለመፈፀም በሙሉ ልብ ዝግጁ ነን" ብለዋል።

ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በናይሮቢ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው በተደረገው ውይይት መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በተደረገው ውይይትና በተደረሰው መግባባት መሰረትም በናይሮቢ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አተገባበር ለመፈፀም በሙሉ ልብ ዝግጁ ነን ብለዋል።

በውብሸት ሰንደቁ
የሲዳማ የሽምግልና ሥርዓት ሕዝቡ በመተማመን እንዲኖር ማስቻሉን የአገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
****
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል አቦ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ብይን ከመስጠት ባለፈ የእርቅ ሥርዓት የሚከናወንበት ማኅበረሰቡ በይቅርታና በመተማመን አብሮ እንዲኖር በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የአካባቢው ሽማግሌዎች ተናገሩ። ሥርዓቱ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ከመደበኛው ፍርድ ቤት ጎን ለጎን አገልግሎት እንደሚሰጥም ተመልክቷል።

በወንሾ ወረዳ አካባቢ ሽማግሌ አቶ አለሙ ዮኔ፤ ከትውልድ ትውልድ በመሸጋገር እየተከናወነ የሚገኘው አቦ ወንሾ ባህላዊ ዳኝነት ለሲዳሞዎች ትልቅ እሴት እንደሆነ ነው የገለጹት።

ሥርዓቱ ለአገር የሚጠቅም፣ ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት እንደሚያስችል በመጠቆምም፤ ሲዳሞዎች በባህላቸው አስከሬን አስቀምጠው ይቅር የሚባባሉበት ‹‹አፍን›› ሥርዓት መረጋጋትን በመፍጠር፣ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ጉዳዮች እንዲረግቡ ጉልህ ሚና እንደነበረው አመልክተዋል።

አፍን ቂም በቀልን በመተው እርቅ የሚፈጸምበት ሥርዓት እንደሆነ የጠቆሙት የአገር ሽማግሌው፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ቢስፋፋ ኖሮ እርስ በእርስ ግጭት አይኖርም፣ ጦርነት ውስጥም አይገባም፣ የታለፈው አይነት ችግርም አይደርስም ነበር ብለዋል።

አሁን አሁን የሕይወትና የንብረት ውድመት የተባባሰው የእርቅ ሥርዓት ባለመስፋፋቱ ነው። እሴቱን መጠበቅም ማስፋፋትም ይገባል ብለዋል። በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሥርዓቱን..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85736
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio