Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወልቃይትን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ‼️
የሚናፈሰው ወሬ ላይ የመንግሥት እጅ የለበትም። የፕሪቶሪያው ስምምነት ሰላምን በማምጣት ላይ ያተኮረ ነው እንጂ የሀገራችንን የመሬት ጉዳይ የተመለከተ አይደለም። በሀገራችን ህግ እና ስርዓት መሰረት የሚፈጸም ነው። ከሕገ መንግስቱ በፊት በጉልበት ነው የተወሰደው ላሉት፣ የኔም ፍላጎት ያ እንዳይደገም ነው።
በጉልበት ዛሬም ተመሳሳዩ ተግባር መፈጸም የለበትም። በሕግ እና በስርዓት ቢፈጸም ለወልቃይት ይጠቅማል፣ ለአማራም ለትግራይም ይጠቅማል። ረዘም ላለ ጊዜ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል። ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ንግግር ያስፈልጋል።
የተሰጣቸውን ሥራ በትክክል የማይሰሩ ሰዎች የፌደራል መንግስትን ስም እያነሱ ብዙ ሽረባ እንደሚሰሩ ግልጽ ነው። እኛ ስምምነቱ እንዳይበላሽ ብለን ነው ዝም ያልነው። ሁሉም የተሰጠውን ሥራ መስራት አለበት።
የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው ብለናል፣ ከፍላጉቱና ከእሳቤው ውጪ ችግር ላይ ሲወድቅ እኛ ካላገዝነው ማን ያግዘዋል? መቸገሩ የሚያስታውቅ እኮ ነው። ስናሸነፍ ደግ እና ይቅር ባይ፣ ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል።
የትግራይ ህዝብ ሰላም ፈላጊነቱን አሳይቷል፣ ወታደሩ ተመልሶ ድጋፉን ቀጥሎ ‘ይህንን ሰራዊት ነው ወይ ያጠቃነው?’ የሚሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ውይይቱን ማስቀጠል ያስፈልጋል። የትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላምን፣ ዉሀ፣ መብራት፣ አገልግሎት እንደሚፈልግ፣ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር ምንም ችግር እንደሌለበት አይተናል። ሰላሙ እንዳይበላሽ በታማኝነት ያለውን ሁሉ ለመስራት ዝግጁ ነኝ። እናንተም ይህንኑ እንድትደግፉ ነው የምፈልገው።
ከአማራ በኩል ብዙ ወልቃይቴዎች ተፈናቅለዋል፣ እነርሱ ሳይኖሩ ሕዝበ ውሳኔ ቢባል እንጎዳለን ተብሏል። በትግራይ በኩል አሁን ባለው ግጭት ተፈናቅለናል ስለዚህ ሕዝበ ውሳኔ ቢፈጸም እንጎዳለን ብለዋል። ነገር ግን፣ ወልቃይቴ የትም ቢሄድ ይታወቃል።
የ25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርአት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ላይ ባደረጉን ንግግር፤ 25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለእድለኞች የወጡ ሲሆን፤146ሺ 892 ቆጣቢዎች እጣ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በ20/80 18ሺ 930 ቤቶች፤ በ40/60 6ሺ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 791 ቤቶች እጣ ወጥተዋል፡፡

2014 ዓ.ም. የ20/80 14ኛ ዙርና የ40/60 3ኛ ዙር የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በይፋ የተካሄደ ቢሆንም በወንጀል ጥቆማ መሰረት በተደረገ ኦዲት እጣው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጎ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላትም በህግ አግባብ እንዲጠየቁ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

መስል ችግር እንዳይፈጠር አዲስ የበለጸገ የእጣ አወጣጥ ስነስርአት አምስት አባላት ያሉት ቴክኒካል ኮሚቴ ተዋቅሮ የበለጸገውን ቴክኖሎጂ አረጋግጠዋል ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
1.3 MB
እንኳን ደስ አላችሁ‼️
የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት ዕድለኞችን ስም ዝርዝር
በአማራ ክልል ሁለት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግንባታ ላይ ናቸው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል ሁለት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግንባታ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ። በክልሉ በርካታ ባለሀብቶች በማዕድን ዘርፍ ላይ ገብተው የምርመራ ፍቃድ በመውሰድ ወደ ማምረት ስራ መግባታቸውም ተገልጿል።
የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይታየው ተስፋሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የምርመራ ፍቃድ ከወሰዱ ሰባት ኩባንያዎች መካከል ሁለቱ ወደ ግንባታ ገብተዋል።
እንደ አቶ ይታየው ገለፃ፤ በክልሉ በሲሚንቶ ዘርፍ ገብተው ለመስራት ፍቃድ ከተሰጣቸው ሰባት ኩባንያዎች መካከል ናሽናል እና በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የግንባታ ስራ ጀምረዋል።
የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ መገንባት እንደ ሀገር የተከሰተውን የሲሚንቶ እጥረት ችግር የመቅረፍ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ነው አቶ ይታየው የገለፁት።
ናሺናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በክልሉ ሰሜን ሸዋ እንሳሮ ወረዳ ለሜ እንዲሁም በረንታ ሲሚንቶ በክልሉ ምስራቅ ጎጃም ዞን በረንታ እንደሚገኙም አቶ ይታየው ተናግረዋል። ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ ስራውን በቀጣይ አንድ አመት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩነ ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85874
ክልሉ 321 ዋሻዎችን ለቱሪዝም አገልግሎት ለማዋል እየሰራ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የቱሪዝም ሀብቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች አገልግሎት በማዋል ከዘርፉ የሚጠበቀውን ገቢ ለማስገኘት 321 ዋሻዎችን ለቱሪዝም አገልግሎት ለማዋል በትኩረት እየሰራበት መሆኑን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ ዋሻዎች ላይ የተደረገ ጥናት ክልሉ የዓለም ቱሪዝም ቀን በሚያከብርበት ቀን ይፋ ተደርጓል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዋሻ ጥናት ባለሙያ ናስር አህመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቢሮው በክልሉ ለቱሪዝም ሀብት የሚውሉ ዋሻዎች ለሚፈለገው አገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ በዋሻ ጥናት አድርጓል፡፡ ከውጪ ሀገራት ባለሙያ ጋር በመሆን በተደረገው ጥናት ለ321 ዋሻዎች አስፈላጊ መረጃ መሰባሰቡንም ገልጸዋል፡፡
ጥናት ከተደረገባቸው ውስጥ ለ200 ዋሻ ካርታና ፕላን የተሰራላቸው ሲሆን አብዛኞቹ በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ሌሎቹ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ መልከ ቁንጡሬ አካባቢ ፣ ሰሜን ሸዋ ፣ ወለጋ ግምቢና ደምቢዶሎ እንደሚገኙ ጥናቱ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በዋሻ ሀብት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት ያሉት አቶ ናስር፤ አሁን ጥናት ከተደረገባቸው አካባቢዎች በምስራቅ ሀረርጌ አንድ ወረዳ ብቻ 55 ዋሻዎች መኖራቸው ክልሉ በዋሻ ሀብት ቀዳሚ መሆኗን ያሳያል....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85862
(ፎቶ የሶፍዑመር ዋሻ ከኢንተርኔት የተገኘ)
በተያዘው ዓመት በማክሮ ኢኮኖሚው ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ እድገት ይጠበቃል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በዘንድሮው ዓመት በማክሮ ኢኮኖሚው ዘርፍ ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ እድገት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከህዝብ እንደራሴዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ዓመታት፣ በተለይም ደግሞ ባለፈው ዓመት ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ፈተናዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ቢያስተናግድም፤ በቀላሉ የማይሰበርና በተያዘው የዕድገት መስመር የሚቀጥል በመሆኑ፤ ጫናን ተቋቁሞ 6 ነጥብ 16 ትሪሊየን ብር (127 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር) ደርሷል፡፡ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሺህ 212 ዶላር ሆኗል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚው አምና ስድስት ነጥብ አራት በመቶ የተመዘገበ ሲሆን፤ በዘንድሮ ዓመት ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ባንክን መረጃ ዋቢ አድርገው እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛው፣ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሃገራት ደግሞ ሶስተኛው ግዙፍ ኢኮኖሚ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚያዊ እ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85846
የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ከዛሬ ጀምሮ ይወጣል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የገንዘብ ሚኒስሩር አቶ አህመድ ሽዴ እና ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ኢትዮቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል በሚዛወርበት (ፕራይቬታይዝ በሚደረግበት) ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።
መንግስት የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ለማዛወር አውጥቶት የነበረው ዓለም አቀፍ ጨረታ በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና በአገር አቀፍ ደረጃም ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ መቋረጡን አስታውሰዋል።
ዓለም አቀፍ ኩባንያን ለማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ጨረታው ለቀጣይ ሶስት ሳምንታት እስከ እአአ ዲሴምበር 19 ቀን 2022 ክፍት ተደርጓል።
አሁን በተፈጠረው ስምምነት መሰረትና አለም አቀፋዊ ሁኔታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ከሳፋሪኮም ቀጥሎ አንድ ተጨማሪ ኩባንያ ለማስገባት ጨረታ ወጥቷል ብለዋል።
በዘላለም ግዛው
ከሁመራ -ወልቃይት እስከ ሽራሮ ያለው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከሁመራ – ወልቃይት እስከ ሽራሮ ያለው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጥገና እንደቀጠለ ነው።
ከሁመራ እስክ ሽራሮ የተዘረጋውን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ላይ በአማካይ በቀን እስከ 200 የሚደርሱ የኢትዮጵያ ኤለኬክትሪክ ኃይል ሰራተኞች እየተሳተፉበት ይገኛሉ ብለዋል። በከፍተኛ የኃይል መስመሩ ላይ የሚገኙ የኤሌክትሪክ መስመሮች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸውና ተበጣጥሰው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሞገስ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎችም መስመሮቹ ዳግም አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከመስመር ጥገናው ባለፈ የወልቃይት አካባቢ የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያው ቀደም ብሎ በነበረው ጦርነት የተነሳ ጉዳት እንደደረሰበት አቶ ሞገስ አስታውሰዋል። የወልቃይት ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የጥገና ስራም እየተከናወነ መሆኑንና ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85884