Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች‼️
👉 የማያልቅ ጦርነት ውሃ በወንፊት ነው፤ ዝም ብሎ እየተዋጉ መኖር አይቻልም፤
👉 ሰላምና ብልጽግናን ለማስቀጠል ሲባል ጦርነትን ማቆም በእጅጉ ያስፈልጋል፤
👉 የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም፤
👉 ጦርነት እያሸነፍክም ቢሆን መጥፎ ነው፤ ምክንያቱም ሰው ነው የምትገለው፤
👉 የኢትዮጵያን ልዕልና የሚገዳደር ሲፈጠር ያ ነገር በሰላም የማይፈጠርበት ሁኔታ ሲፈጠር መፋለም ግዴታችን ነው፤
👉 ድርድርም ካለ ንግግርም ውይይትም ካለ ለኢትዮጵያ አንደነት ብቻ ነው፤
👉 ለኢትዮጵያ አንደነትና ጥቅም ሲባል መሄድ የማንፈልግባቸው ቦታዎች ጭምር እንሄዳለን፤
👉 ከሰላም የምታተርፈው ኢትዮጵያ ናት፤
👉 ሰላም የሚያስከፋቸው ሃይሎች የጦርነት ነጋዴዎች ናቸው፤
👉 ተነጋግረናል፤ ተስማምተናል፤ ፈርመናል፤ ከዚህ በሁዋላ የገባነውን ቃል በማክበር ሰላሙን ዘላቂ ማድረግ ነው፤
👉 የወልቃይት ህዝብ እንዲገነዘብ የምንፈልገው የሚወራው ሽረባ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት የለበትም፤
👉 ደቡብ አፍሪካ የሄድነው ለወልቃይት ጉዳይ ለመነጋገር አይደለም፤ ቦታውም አይደለም፤
👉 የተስማማነው በኢትዮጵያ ህግና መንግስት ይፈጸም ብለን ነው፤
👉 ወልቃይት በተመለከተ ያ ህዝበ የትም ይሁን የትም እንዲወስን ዴሞክራሲያዊ እድል ከሰጠነው ብቻ ነው ዘላቂ ሰላምና መፍትሄ የሚመጣው፤
👉 ሸኔ እንኳን ለእኛ ለሚልኩት ሰዎችም አስቸጋሪ ሆኗል፤ ምንም የሚጨበጥ አላማም ማዕከልም የሌለው ነው፤
👉 ለኦሮሞ ቆሚያለሁ ይላል ኦሮሞን ይገድላል፤ ያፈናቅላል፤
👉 በሃይል የሚጣ ሰላም የለም፤ እኛ ለሰላምና ለንግግር ሁሌም በራችን ክፍት ነው፤
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች‼️
👉ቀይ መስመር ያልነውን ሌብነት ቀይ ምንጣፍ ያደረጉ ሰዎች እየተፈጠሩ ነው፣
👉 ሳይሰሩ የሚበሉ ሳይሆን የሚሰራውንም ሰው የሚበሉ አሉ፤
👉 ሌባ ቤት ይሰራ ይሆናል እንጂ አገር አይኖረውም፣
👉 በሌብነት ቤት እንጂ አገር አይገነባም፤ አገር አልባ ቤት ደግሞ ዘላቂነት አይኖረውም፤
👉 ሌብነት ባናጠፋ እንኳን አንገቱን እናስደፋለን፤
👉 ብዙ የሚደክሙ ሰዎች ቢኖሩም አሁንም ሌቦች ስላሉ መፈተሽና ማረቅ ያስፈልጋል፤
👉 ሌብነት ብቻ ሳይሆን ስራን የሚገድሉ ሰዎችም አሉ፤
👉 የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መለያ ነጻነት እኩልነት እና ፍትሃዊነት ነው፤
👉 የኢትዮጵያን ሰላም ላገዙ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን፤
👉 ኢትዮጵያዊያን በመላው አለም ባሉበት አገር ሆነው ለአገራቸው ጥቅም ሊሰሩ ይገባል፤ ባሉበት አገር ፖለቲካም እንዲሳተፉ እመክራለሁ፤
ስምምነቱ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የፌዴራል መንግስት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከህወሃት ጋር በደቡብ አፍሪካ የደረሰው ስምምነት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ገለጹ፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሃት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ባደረጉ ኤምባሲዎች ላሉ የወታደራዊ አታሼዎች ስለ ሰላም ስምምነቱ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት የኢትዮጵያን ሰላም ያናጋ፣ የህዝብን በሰላም የመኖር፣ ወጥቶ የመግባትና የመኖር ደህንነትን አደጋ ላይ የጣለ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ስምምነቱ ወሳኝ ምዕራፍ እና አዲስ የተስፋ ምዕራፍን የከፈተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማስከበር፣ የሕዝብን ደህንነት የማስጠበቅ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተቀላጠፈ መንገድ እንዲደርስ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ተናገሩት፡፡
የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተሰራ መሆኑን በመጠቆምም፤ የተደረሰው ስምምነት ተፈጻሚ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባልም ብለዋል፡፡
በዘላለም ግዛው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወልቃይትን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ‼️
የሚናፈሰው ወሬ ላይ የመንግሥት እጅ የለበትም። የፕሪቶሪያው ስምምነት ሰላምን በማምጣት ላይ ያተኮረ ነው እንጂ የሀገራችንን የመሬት ጉዳይ የተመለከተ አይደለም። በሀገራችን ህግ እና ስርዓት መሰረት የሚፈጸም ነው። ከሕገ መንግስቱ በፊት በጉልበት ነው የተወሰደው ላሉት፣ የኔም ፍላጎት ያ እንዳይደገም ነው።
በጉልበት ዛሬም ተመሳሳዩ ተግባር መፈጸም የለበትም። በሕግ እና በስርዓት ቢፈጸም ለወልቃይት ይጠቅማል፣ ለአማራም ለትግራይም ይጠቅማል። ረዘም ላለ ጊዜ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል። ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ንግግር ያስፈልጋል።
የተሰጣቸውን ሥራ በትክክል የማይሰሩ ሰዎች የፌደራል መንግስትን ስም እያነሱ ብዙ ሽረባ እንደሚሰሩ ግልጽ ነው። እኛ ስምምነቱ እንዳይበላሽ ብለን ነው ዝም ያልነው። ሁሉም የተሰጠውን ሥራ መስራት አለበት።
የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው ብለናል፣ ከፍላጉቱና ከእሳቤው ውጪ ችግር ላይ ሲወድቅ እኛ ካላገዝነው ማን ያግዘዋል? መቸገሩ የሚያስታውቅ እኮ ነው። ስናሸነፍ ደግ እና ይቅር ባይ፣ ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል።
የትግራይ ህዝብ ሰላም ፈላጊነቱን አሳይቷል፣ ወታደሩ ተመልሶ ድጋፉን ቀጥሎ ‘ይህንን ሰራዊት ነው ወይ ያጠቃነው?’ የሚሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ውይይቱን ማስቀጠል ያስፈልጋል። የትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላምን፣ ዉሀ፣ መብራት፣ አገልግሎት እንደሚፈልግ፣ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር ምንም ችግር እንደሌለበት አይተናል። ሰላሙ እንዳይበላሽ በታማኝነት ያለውን ሁሉ ለመስራት ዝግጁ ነኝ። እናንተም ይህንኑ እንድትደግፉ ነው የምፈልገው።
ከአማራ በኩል ብዙ ወልቃይቴዎች ተፈናቅለዋል፣ እነርሱ ሳይኖሩ ሕዝበ ውሳኔ ቢባል እንጎዳለን ተብሏል። በትግራይ በኩል አሁን ባለው ግጭት ተፈናቅለናል ስለዚህ ሕዝበ ውሳኔ ቢፈጸም እንጎዳለን ብለዋል። ነገር ግን፣ ወልቃይቴ የትም ቢሄድ ይታወቃል።
የ25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርአት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ላይ ባደረጉን ንግግር፤ 25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለእድለኞች የወጡ ሲሆን፤146ሺ 892 ቆጣቢዎች እጣ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በ20/80 18ሺ 930 ቤቶች፤ በ40/60 6ሺ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 791 ቤቶች እጣ ወጥተዋል፡፡

2014 ዓ.ም. የ20/80 14ኛ ዙርና የ40/60 3ኛ ዙር የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በይፋ የተካሄደ ቢሆንም በወንጀል ጥቆማ መሰረት በተደረገ ኦዲት እጣው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጎ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላትም በህግ አግባብ እንዲጠየቁ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

መስል ችግር እንዳይፈጠር አዲስ የበለጸገ የእጣ አወጣጥ ስነስርአት አምስት አባላት ያሉት ቴክኒካል ኮሚቴ ተዋቅሮ የበለጸገውን ቴክኖሎጂ አረጋግጠዋል ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
1.3 MB
እንኳን ደስ አላችሁ‼️
የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤት ዕድለኞችን ስም ዝርዝር