Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የውሃ አቅርቦት ከአንድ ወር በላይ በመቋረጡ ለችግር መጋለጣቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
👉የችግሩ መንስኤ በውሃ መስመር እና ኃይል አቅርቦት ላይ በተከሰተ ችግር መሆኑም ተጠቁሟል
ከአንድ ወር በላይ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በመቋረጡ ለችግር መጋለጣቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቅሬታቸውን ያቀረቡ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ችግሩ በውሃ መስመር ላይ በተፈፀመ አሻጥርና በተወሰኑ አካባቢዎች ጉድጓዶች ላይ በደረሰ መጠነኛ የቴክኒክ ችግር የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቅሬታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከገለፁት ነዋሪዎች መካከል በወይራ አካባቢ ለምለም በሚባል መንደር የሚገኙ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በአካባቢያቸው ከአንድ ወር በላይ የመጠጥ ውሃ ተቋርጦባቸው ቆይቷል፡፡ ይህም ለከፍተኛ እንግልት እንደዳረጋቸውና ከዚህም በተጨማሪ ለውሃ አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ከሚመለከታቸው አካላት በቅጡ እንዳልተነገራቸው እንዲሁም ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መልዕክት አለመተላለፉን አስገንዝበዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ሃና ማርያም በሚባለው አካባቢ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ መሆኑንና ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፈጣን ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸው እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲፈትሽ ጠይቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85873
የይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ በሊዝ የሚተላለፍ 97 ሄክታር መሬት ዝግጁ አድርጓል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሲዳማ ክልል የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የለማ 97 ሄክታር መሬት ለባለሀብቶች በሊዝ ለማስተላለፍ ዝግጁ ማድረጉን በክልሉ የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ ገለጹ።
በፓርኩ ከገቡ አምራቾች መካከል የግብርና ምርቶችን ከአርሶ አደሩ ተቀብለው በማቀነባበር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ መኖራቸውን ገልጸዋል። የአቮካዶ ምርትን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከጀመሩት የኢትዮጵያና የኔዘርላንድ ኩባንያዎች ባለፉት አራት ዓመታት አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱንም ጠቁመዋል።
እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ 11 ሼዶች ተገንብተው ተከራይተዋል፡፡ በፓርኩ ለማልማት ውል ከፈጸሙ 20 የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አራቱ ምርት ጀምረዋል፣ አንዱ በሙከራ ትግበራ ላይ ነው፤ ስድስቱ ደግሞ ከባንክ ጋር ውል ገብተው በሂደት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85864
ትኩረቱን በአባይ ግድብና በሌሎች ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ያደረገ ውይይት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ትኩረቱን በአባይ ግድብና በሌሎች ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ያደረገ ውይይት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፍ (ዶክተር) በመድረኩ ላይ እነደተናገሩት፤ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ባህሪው ውሃ አመንጭቶ ወደ ታችኛው የተፋሰስ አገራት የሚፈስ ቢሆንም ከዚህ እወነታ በተቃራኒ የሚደረገው ጫናው መሰረት የሌለው ነው።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ አንድ አንደ ምእራባውያን አገራትና ሚዲያዎቻቸው በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና ለማሳደር ጥረዋል፤ ኢትዮጵያ ግን እውንትን ይዛ በመጓዝ የአባይ ግድብን ሶስተኛ ዙር ሙሌት አጠናቃ ሁለት ተርባይኖች ሃይል እያመነጩ ነው።
የዓባይ ግድብ ኢትዮጵያውያን ከተባበርንና አንድ ከሆን ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት እድገት ማስመዝገብ ማሳያ ነው ብለዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ እያደረጉ ያሉት ጥናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ለተከታታይ አመታት በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረስብ ላደረገው ፍትሃዊ ትግል ምስጋና አቅርበዋል።
የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ጥቂት ምእራባውያን አገራትና ግብጽ ጨምሮ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው የአባይ ግድብ ሀሰተኛ መረጃዎችንና ጥናት ላይ ያልተመሰረቱ ሀሰተኛ መረጃዎችን ሚዲያዎቻቸውን ጨምሮ በማሰራጨት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ሲያሳድሩ ቆይተዋል ብለዋል።
ለናይል ወንዝ 86 በመቶ የሚሆነውን ውሃ የምትለቀው ኢትዮጵያ በሚገባው ልክ ሳታለማ ቆይትለች። 65 በመቶ የሚሆነውም ህዝቧ በጨለማ ውስጥ የሚኖር ነው። ስለዚህ የሚገነባው ግድብ በጨለማ ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ ብርሃን እንዲገኝ ለማድረግ ነው ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፍ(ዶክተር)፣ ዶክተር ያቆብ አርሳኖ፣ ኢንጂነር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ በካናዳ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጥምረት ተወካዮችና ሌሎች ምሁራን ተገኝተዋል።
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ውይይት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባላው የአባይ ግድብና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በሚደርስባት ጫና የዳያስፖራው፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና፣ የሃይድሮ ዲፕሎማሲን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው የወጣው መርሃግብር ያሳያል።
ሞገስ ተስፋ( ሆሳዕና)
ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ወደ ሽሬ የመጀመሪያውን በረራ ማድረጉን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ከሁለት ዓመት በኋላ የመጀመሪያው የሆነው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ዛሬ ሽሬ አየር ማረፊያ አርፏል ሲል አስታውቋል።
ወደ ትግራይ የሚደረጉ የአየር በረራዎች እንደገና መጀመራቸው አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታን በፍጥነት ወደ ክልሉ ለማድረስ ያግዛል::
ይህም አፋጣኝ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በርካታ ሰዎች ስቃይ ለመቅረፍ ይረዳል ብሏል፤ ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ::
ብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ የሰብዓዊ ርዳታ አቅርቦትና ተደራሽት ጉዳይ ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫን አስቀመጠ
****
(ኢ.ፕ.ድ)

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራዉ ብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና ተደራሽነት ጉዳይ ላይ በመምክር የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ኮሚቴዉ በአገሪቱ በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ገምግሟል፡፡ በድርቅ፣ በጎርፍ እና በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት የሚፈልግና የሁሉንም ዜጋ ርብርብ እንደሚፈልግ ተጠቁሟል፡፡

በትግራይ፣ አፋር፣ አማራና በሌሎች አካባቢዎች በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች መንግስት አስቾኳይ የሰብአዊ ርዳታ በማድረስ ላይ መሆኑንና ለችግር የተጋለጡ ተረጂዎችን በዘላቂነት ማቋቋም እንደሚያስፈልግ የኮሚቴዉ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል፡፡

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት ለችግር ከተጋለጡት ዜጎች ጎን ለጎን ባለፉት ዓመታት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ተረጂዎችም ትኩረት እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡

በግጭት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸዉ ርቀው የቆዩ ተማሪዎችና በተለያየ ምክንያት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም ከሰብዓዊ ርዳታ በተጨማሪ የስነ-ልቦና ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባም አቶ ደመቀ አሳስበዋል፡፡

የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ በሃገሪቱ ካላት የተረጂዎች ቁጥር አንፃር መንግስት ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ሴክተሮች ሃብት ማሰባሰብና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ለመድረስ መቀናጀት አለባቸው ብለዋል፡፡

የሰብአዊ ርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና የልማት አጋሮችም ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ለማገዝ ባላቸው አቅም ሁሉ መረባረብ እንዳለባቸዉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የግብርናና የከተማ ሴፍትኔት መርሃ ግብሮችም የተረጂዎችን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር በሚያሰችል መልኩ ሊሰራባቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

የሚመለከታቸዉ ሴክተሮች፣ የፌዴራልና የክልሎች የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ተቋማት ልምዳቸዉንና ሃብታቸዉን በማቀናጀት በእለት ተእለት እቅዳቸዉ ዉስጥ በማካተት መረባረብ እንዳለባቸዉና ዜጎች በዘላቂነት ከተረጂነት በሚላቀቁበት መንገድ ላይ አተኩረዉ መስራት እንዳለባቸዉም በአስቸኳይ ስብሰባው አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ብሔራዊ ኮሚቴዉም በየሳምንቱ በመገናኘት የሰብአዊ ርዳታ ፍላጎት፣ አቅርቦትና ተደራሽነት ሁኔታን እየገመገመ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋም

ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡

ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ የንግድ ማጭበርበር ሙስናን ለዓላማቸው ማስፈጸሚያነት ይፈልጉታል፡፡

በዓለማችን የተጀመሩ ጦርነቶች እንዳይጠናቀቁ፤ ግጭቶች እንዳይበርዱ፣ ሕዝቦች እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ ሙሰኞች ከዚህ አይነት ቀውሶች ስለሚያተርፉ ነው፡፡

ሙስና ዛሬ የሀገራችን የደኅንነት ሥጋት ሆኗል፡፡ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ እጅ ተወርች አሥሮ ለመያዝ ከጠላቶቻች እኩል ሙሰኛው እየታገለን ነው፡፡

የተስተካከለ ቢሮክራሲ፣ የተቀናጀ መዋቅርና ዘመናዊ አሠራር ለሙስና ተጋላጭነትን ስለሚቀንሱ፣ እነዚህን ለማጥፋት ወይም ለማሰናከል ሙሰኛው ቀን ከሌት እየሠራ ነው፡፡ሕዝባችን በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመሬት ጋር በተያያዙ አሠራሮች፣ በፋይናንስ ዘርፍ፣ በሽያጭና ግዥ ሂደቶች፣ በፍትሕ አደባባዮች፣ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶች፣ የህዝብ ተቋማት ወዘተ. በሚያጋጥመው ሙስና እየተማረረ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ከሕዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከጸጥታ ሥጋቶች እኩል ሙስና የብልጽግና ጉዟችን ዋናው ዕንቅፋት መሆኑን አንሥቷል፡፡

መንግሥት በየደረጃው የሚገኘውን መዋቅር በመፈተሽ፣ አዳዲስ አሠራሮችን በመዘርጋት፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን እያሳለጠ ሥራዎችን ከእጅ ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ በሙስና ወንጀል የሚሳተፉ አመራሮችንና ሌሎች ተዋንያንን ለሕግ በማቅረብ፣ ሙስና ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠርለት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን ያጋጠማትን ጦርነትና ኮሮናን የመሳሰሉ ወረርሽኞች የመንግሥትን ትኩረት ወስደዋል ብለው ያሰቡ ሙሰኞች፣ በየቦታው ተሠግሥገውና ኔት ወርክ ዘርግተው፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየሠሩ መሆናቸውን በዝርዝር የቀረበው የጥናት ሪፖርት ያሳያል፡፡ መንግሥት በጸጥታው ዘርፍ እንዳደረገው ሁሉ በሙስና ላይ ጠንካራና የማያዳግም ኦፕሬሽን ማድረግ እንዳለበት የጥናቱ ውጤትና የሕዝብ ውይይቱ ግምገማ ያመለክታል፡፡ በአንድ በኩል የመንግሥት ሕጎች፣ደንቦች፣ መመሪያዎችና አሠራሮች ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት የማጥፋት ሥራ ይሠራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሙስና ተዋንያንን የማጋለጥና በሕግ የመጠየቅ ተግባር ይከናወናል፡፡

መንግሥት በጥናት በደረሰባቸው የመንግሥት ሹመኞች፣ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ አቀባባዮችና ጉቦ ሰጪዎች ላይ ምርመራ እያደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ሙስና በባሕርዩ በረቀቀ መንገድ፣ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ አንዳንድ ጊዜም በሕጋዊነት ሽፋን የሚካሄድ በመሆኑ በመንግሥት ጥናት የተደረሰባቸው አካላትን ብቻ ለሕግ በማቅረብ የሚፈታ አይደለም፡፡ ሙስናን ከሥር ከመሠረቱ ለመንቀል እንዲቻል ከሕግና ከአሠራር ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ የሙስና ተዋንያን ሁሉ ሙስናን እርም እንዲሉ የሚያደርግ ርምጃ ያስፈልጋል፡፡መንግሥት በሙስና ላይ የሚያደርገውን ዘመቻ የሚያስተባብር፣ በጥናት ተለይተው ከቀረቡት በተጨማሪ ሌሎችንም ተዋንያን የሚለይና ለሕግ እንዲቀርቡ የሚያደርግ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡

ብሔራዊ ከሚቴው ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡-
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
2. ዶ/ር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ
3. አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ
4. አቶ ሰሎሞን ሶቃ
5. አቶ ደበሌ ቃበታ
6. ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
7. አቶ አብዱሃሚድ መሃመድ ናቸው፡፡

ይህ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት እንዲችል የኅብረተሰቡ ሙሉ ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኅብረተሰቡ በሙስና ላይ በሚደረገው ዘመቻ ሊሳተፍ እንደሚገባ በተለያዩ መድረኮች ሲያነሣ ቆይቷል፡፡ መንግሥትም ይሄንን የሕዝብ ተሳትፎ በእጅጉ ይፈልገዋል፤ ምክንያቱም ሙስና በዋናነት የሚጠፋው ሕዝብ አምርሮ ሲታገለው ነውና፡፡

በመሆኑም ኅብረተሰቡ የሙስና ተዋንያንን በተመለከተ ያለውን መረጃ፣ ከቂምና ከበቀል ነጻ በሆነ መንገድ፣ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች ለብሔራዊ ኮሚቴው በመላክ ሙስናን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የሚቀርቡ ጥቆማዎች የጠቋሚዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እና ሚስጥራዊነት በጠበቀ መንገድ ተይዘው ይመረመራሉ። ብሄራዊ ኮሚቴው የሚወስዳቸው እርምጃዎች እና የእንቅስቃሴው ውጤት በየጊዜው ለህዝብ ይፋ ይደረጋል። የየክልሉ ርእሳነ መስተዳድሮች በየደረጃው የሚሠሩ ክልላዊ ኮሚቴዎችን በቅርቡ እንደሚያቋቁሙ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጣለን።

ስልክ ፡ 9555
አጭር የፅሁፍ መልዕክት : 9555
ድረ ገፅ ፡ http://www.9555pmo.et/
ኢሜይል : http://9555pmo.et/
ቴሌግራም ፡ https://news.1rj.ru/str/PMOfeedback
በመጀመሪያው ሩብ አመቱ 419 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት አስታወቀ
*********************
(ኢ ፕ ድ )
በተያዘው የበጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመቱ 419 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ከክልል ኢንተርፕራይዝ ቢሮዎች ጋር የሩብ አመቱን አፈጻጸም በአዳማ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኢንተርፔራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የሩብ አመቱን የእቅድ አፈጻጸምን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት
በበጀት አመቱ አራት ሽህ 62 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ለማቋቋም እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።
እንደ አቶ አብዱልፈታ ገለጻ፤ በሩብ አመቱ 551 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ለማቋቋም ታልሞ 419 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ማቋቋም ተችሏል።
በሩብ አመቱ 258 ሚሊዮን ብር የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ለአምራች ኢንተርፕራይዞች መሰራጨቱንም አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል።
በሙሐመድ ሁሴን (አዳማ)
ልማት ባንክ የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና ለሚሰጡ ተቋማት ብድር ሊሰጥ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የሦስተኛ ደረጃ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት ለሚችሉ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት፤ ባንኩ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ የሚደረጉ የሕክምና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ እንዲጀመሩ ለማስቻል የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና የሚሰጡ ተቋማትን ለመደገፍ ተዘጋጅቷል። በዘርፉ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀረቡ የጤና ተቋማት መኖራቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ የብድር ፕሮጀክቱን በቀጣዮቹ አራት ወራት ለማፅደቅና ወደ ሥራ ለመግባት መታቀዱን ተናግረዋል።
እንደ ዶክተር ዮሐንስ ገለጻ፤ የጤናው ዘርፍ የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልገዋል። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው የልማት ባንክ የፋይናንስ አጋር ሆኖ ለመቅረብ...
https://www.press.et/?p=85938
ከአንድ ማዕከል የኤሌክትሪክ አገልግሎትን መከታተል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
******
(ኢ.ፕ.ድ)
ከአንድ ማዕከል በመሆን የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለመከታተል የሚያስችል የስካዳ አውቶሜሽን አገልግሎት ተግባራዊ እንደሚያደርግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። ተቋሙ ከመሠረተ ልማት ግንባታና ጥገና ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ፈጣንና ተደራሽ እንዲሆን እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመብራት አገልግሎት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮች ተለይተው ሥራዎች እየተሠሩ ነው።
ሥራዎቹ በአጠቃላይ በ2017 ዓ.ም ሲጠናቀቁ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፈጣን፣ ተደራሽ እና እንከን የለሽ ይሆናል ብለዋል።
የመብራት አገልግሎት ጥራት እንዳይኖር ከሚያደርጉት ችግሮች አንዱ የመብራት መቆራረጥ እና ለረጅም ጊዜ ጠፍቶ መቆየት መሆኑን ያነሱት ዋና ሥራ....
https://www.press.et/?p=85937
በኢትዮ- ኬኒያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀምሯል
********
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤላክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል፡፡

በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ ከጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን ቆይቷል፡፡

ዛሬ በይፋ ኃይል ማስተላለፍ የጀመረው የኢትዮ - ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ አንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማስገባት አቅም ያለው ሲሆን ከኬንያ አሌፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤላክትክ የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡

የኢትዮ- ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ፣ ለካሳ ክፍያና የተሰረቁ መሰረተ ሌማቶችን ለመተካት የወጣውን ወጪ ጨምሮ ወደ አምስት መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶሊር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

ከዚህ ውስጥ 214 ነጥብ 5 ሚሉዮን ዶላሩ ለኮንቨርተር ስቴሽኑና ለግራውንድ ኤላክትሮድ መስመር የግንባታ ሥራ እንዲሁም 120 ሚሉዮን ዶላሩ ደግሞ ለማስተላለፊያ መስመሩ የዋለ ነው፡፡

የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራ "CET" በተሰኘ የቻይና ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያውና የግራውንድ ኤላክትሮድ መስመሩ ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የተዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር እና የፕሮቴክሽንና የዳታ ኮሙዩኒኬሽን መስመር (ኦፕቲካሌ ግራውንድ ፋይበር) 440 ኪል ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን 994 የከፍተኛ ኃይሌ ተሸካሚ የብረት ታወሮች አሉት።

ኢትዮጵያ የምታስተላልፈው ኃይል ያልተቆራረጠና አስተማማኝ እንዲሆን የሚያግዙ ተግባራትን ያጠናቀቀች ሲሆን በኬንያ በኩል ተመሳሳይ ሥራዎች ተሰርተው በቅርቡ ወደተግባር እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

የማስተላለፊያ መስመሩ ከደቡብ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወላይታ፣ ጋሞ እና ኮንሶ ዞን እንዲሁም ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስት የቦረና ዞን አቋርጦ ነው ወደ ኬንያ ኃይል የሚያስተላልፈው።

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከሱዳን እና ከጅቡቲ ጋር የኃይሌ ሽያጭ እያካሔደች ሲሆን ከሶማሌላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤላክትሪክ ኃይሌ ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማለች።
ባለፈው ዓመት ለሱዳን እና ለጅቡቲ ኤክስፖርት ከተደረገው የኤላክትሪክ ኃይሌ 95 ነጥብ 4 ሚሉየን የአሜሪካን ዶሊር ገቢ ተገኝቷል፡፡

(ፎቶ ፋይል)