Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሰላም ማስከበር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በሰንዴ ምርት የተመዘገበው ድል በከተማ ግብርና ይደገማል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሰላም ማስበር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በስንዴ ምርት የተመዘገበው ድል በከተማ ግብርናም ይደገማል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነትና አለም አቀር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ አስታወቁ።

አቶ ሳዳት በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የሌማት ትሩፋት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እንደገለጹት፣ አገራችን ተገዳ በገባችበት ጦርነት ምንም እንኳ ታሪክ የማይረሳውን ዋጋ ብትከፍልም በልጆቿ ጀግንነት በድል አጠናቅቃለች። ከዚህ አንጻር ከግንባር ውጊያ አስከ ደጀንነት ድረስ ያላቸው ተሳትፎና ድጋፍ የሴቶች ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በጠቅላይ ሚንስትሩ መሪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አገሪቱ የተስተካከለ የአየር ንብረት ባለቤት እንዲትሆን ከማድረግ ባሻገር በምርትና ምርታማነት ላይ ጉልህ ሚና መኖሩን የገለጹት አቶ ሳዳት፤ በምግብ ራስን በመቻል በተለይ በሰንዴ ምርት እየተሰራ ያለው ሥራ ትልቅ ተስፋን የፈጠረ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።

ለምግብ ዋስትና ለከተማ ግብርና ወሳኝ ሚና መኖሩን የተናገሩት ኃላፊው፤ ከዚሁ አንጻር የሴቶች ሊግ መላው የአገሪቱ ሴቶችን በማንቀሳቀስ በከተማ ግብርና እያከናወነ ያለዉ ሥራ አመስግነው በከተማ ግብርና ውጤታማ ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በመድረኩ በሰላም ማከስከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሴቶች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዋቅሹም ፍቃዱ
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሥልጠና እየሰጠ ነው
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በውጭ ግንኙነትና በብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ዙሪያ በአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ሥልጠናውን እየሰጡ ያሉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እንደ በለጸጉት ሀገራት ሃያል ባትሆንም በሃያላን ውሳኔ የሚመራ አለም ውስጥ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ሚናዋን በውል ማሳየት ያስፈልጋል።

በሥልጠናውም የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጋፋ የሌላውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መመከት የሚያስችል ግንዛቤ እየተሰጠ ነው።

በዋቅሹም ፍቃዱ (ሱሉልታ)
ጊዜ ያቀናት የጣና የአብራክ ክፋይ- ቁንዝላ
****
(ኢ.ፕ.ድ)
የውቢቷ ባህር ዳር ጀንበር የማለዳ ፈገግታዋን ጣና ላይ ጣል አድርጋለች። በሰፊው ሀይቅ ላይ የተጋደመው ባህርም ከሩቅ ሲያማትሩት አይንን ይስባል። ድንግል ውበትና ማራኪ የተፈጥሮ ሀብት አቅፋ የምትጠብቀን የጣና የአብራክ ክፋይ ቁንዝላ መደረሻችን ሆናለች።

ቁንዝላ በደቡብ ምዕራብ ጣና ሀይቅ ላይ የምትገኝ ትንሽ የወደብ ከተማ ናት። ምንም እንኳን ከክልሉ ዋና ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ብትሆንም የተፈጥሮ ሀብቷን ትጠቀምበት ዘንድ ትኩረት ሳይሰጣት ቆይታለች። በርካቶች ቀለብ ይሰፍርልናል ብለው ተስፋ የጣሉበት ጣና ለቁንዝላ ባዕድ ሆኖባት ቆይቷል።

ክንፈ ሳፋፊዎቹ ፍጡራን ካልሆኑ በቀር የቁንዝላውን ጣና ሰው አይን አይኑን ብቻ እየተመለከተ ትውልድ እያለፈ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። የውሃና መሬት ሀብት ማእከል ከዛሬ ሁለት ዓመታት ተኩል በፊት በአካባቢው የተፈጥሮ ሀብትን ጥቅም ላይ ለማዋል የአካባቢውን ማህበረሰብ ያማከለ ፕሮጀክት ነድፎ ሥራ መጀመሩ ቁንዝላ አዲስ ተስፋ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86077
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከአራት ሺ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን እያጡ ነው
**
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ከ2010 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም በየዓመቱ 4ሺ 396 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስታወቀ።

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዱልበር ሸምሱ በኢትዮጵያ ለ15ኛና በዓለም ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “እናስታውስ፣ እንደግፍ፣ ለውጥ እናምጣ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ በዋለው የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ማስታወሻ ቀን ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ በየዓመቱ 4 ሺ 396 ሰዎች በትራፊክ አደጋ በሚደርስ ጉዳት ሕይወታቸው እያለፈ ነው።

በአገር አቀፍ ደረጃ ባሳለፍነው አንድ ዓመት ብቻ በፌዴራል ፖሊስ በቀረበ ሪፖርት 3 ሺ 971 ሞት፣ 5ሺ 586 የከባድ የአካል ጉዳት፣ 4ሺ 739 የቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧልም ብለዋል።

አቶ አብዱልበር አክለውም፣ በትራፊክ አደጋ በደረሰ ጉዳት ሳቢያም ከሕይወት ህልፈት በዘለለ በንብረት ላይ በደረሰ ጉዳት ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት ደርሷል።

በኢትዮጵያ በመንገድ ትራፊክ አደጋ በቀን የ12 ሰዎች ሕይወት በአማካኝ ያልፋል ያሉት አቶ አብዱልበር፤ በቀን...
https://www.press.et/?p=86076
«ስምምነቱ ለፓን-አፍሪካኒዝም መጠናከር ትልቅ ጥቅም አለው» - አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን
***
(ኢ.ፕ.ድ)
በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተደረገው የሰላም ስምምነት ለፓን-አፍሪካኒዝም መጠናከር ትልቅ ጥቅም ያለው መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን አስታወቁ።

አምባሳደር እሸቴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ የተደረገው የሰላም ስምምነት ለፓን-አፍሪካኒዝም መጠናከር ትልቅ ጥቅም ያለውና አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ማሳያ ነው። በተለይም የህብረቱ ዋና መቀመጫ እንዲሁም ለፓን- አፍሪካኒዝም ፋና ወጊ ለሆነችውና ሌሎችን አነሳስታ ለዚህ አስተሳሰብ መሪ ሚና ለነበራት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትርጉም አለው።

የፓን-አፍሪካኒዝም ዋናው መነሻው የአስተሳሰቡ ማዕቀፍ አፍሪካውያን የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መምራት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86066