Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አምስተኛው አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ንግድ ትርኢት ተከፈተ
******
(ኢ ፕ ድ)

11 አጋራት የሚሳተፉበት አምስተኛው አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ንግድ ትርኢት ዛሬ በኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል።

የንግድ ትርኢቱን የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የአገርን ምርትና ገበያ ለወጪው አለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም የወጪውን ለማወቅ ትርኢቱ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዘርፉ በአገራት መከካል ልምድ ለመለዋወጥና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚረዳም ጠቅሰዋል።

ንግድ ትርኢት "manufacturing for enhanced employment" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂ ተኮር የማኑፋክቸሪንግ ግበአቶች ከአምራች ኩባንያዎች ለሸማቹ ማህበረሰብ እንደሚቀርብ ተጠቅሷል።

በንግድ ትርኢቱ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ህንድ፣ ጆርዳን፣ ፓኪስታን ሳኡዲ አርቢያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስና ቻይና ተሳታፊ ናቸው።

በአዲሱ ገረመው
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ለአፋር ክልል የ285 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
******
(ኢ ፕ ድ)

በሰሜኑ ጦርነት የተነሳ ለችግር የተጋለጡና በአፋር የሚገኙ 24 ሺህ 200 ተፈናቃዮችን ለመርዳት 170 ሚሊዮን ብር መመደቡን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተጨማሪ በአፋር ክልል በከተሞች ለሚተገበረው ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት 115 ሚሊዮን ብር ተመድቧል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ድጋፉ በአጠቃላይ 285 ሚሊዮን ብር ነው፤ ገንዘቡ ቀጥታ ለተጎጂዎች በአካውንት የሚደርስ ነው ብለዋል።

ድጋፉን የተቀበሉት የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል አርባ ሚኒስቴሩ ከተፈናቃዮች ድጋፍ ባለፈ በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ገንዘብ መመደቡን አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም
በሰላም ማስከበር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በሰንዴ ምርት የተመዘገበው ድል በከተማ ግብርና ይደገማል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሰላም ማስበር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በስንዴ ምርት የተመዘገበው ድል በከተማ ግብርናም ይደገማል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነትና አለም አቀር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ አስታወቁ።

አቶ ሳዳት በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የሌማት ትሩፋት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እንደገለጹት፣ አገራችን ተገዳ በገባችበት ጦርነት ምንም እንኳ ታሪክ የማይረሳውን ዋጋ ብትከፍልም በልጆቿ ጀግንነት በድል አጠናቅቃለች። ከዚህ አንጻር ከግንባር ውጊያ አስከ ደጀንነት ድረስ ያላቸው ተሳትፎና ድጋፍ የሴቶች ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በጠቅላይ ሚንስትሩ መሪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አገሪቱ የተስተካከለ የአየር ንብረት ባለቤት እንዲትሆን ከማድረግ ባሻገር በምርትና ምርታማነት ላይ ጉልህ ሚና መኖሩን የገለጹት አቶ ሳዳት፤ በምግብ ራስን በመቻል በተለይ በሰንዴ ምርት እየተሰራ ያለው ሥራ ትልቅ ተስፋን የፈጠረ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።

ለምግብ ዋስትና ለከተማ ግብርና ወሳኝ ሚና መኖሩን የተናገሩት ኃላፊው፤ ከዚሁ አንጻር የሴቶች ሊግ መላው የአገሪቱ ሴቶችን በማንቀሳቀስ በከተማ ግብርና እያከናወነ ያለዉ ሥራ አመስግነው በከተማ ግብርና ውጤታማ ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በመድረኩ በሰላም ማከስከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሴቶች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዋቅሹም ፍቃዱ
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሥልጠና እየሰጠ ነው
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለመካከለኛና ከፍተኛ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በውጭ ግንኙነትና በብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ዙሪያ በአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ሥልጠናውን እየሰጡ ያሉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እንደ በለጸጉት ሀገራት ሃያል ባትሆንም በሃያላን ውሳኔ የሚመራ አለም ውስጥ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ሚናዋን በውል ማሳየት ያስፈልጋል።

በሥልጠናውም የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጋፋ የሌላውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መመከት የሚያስችል ግንዛቤ እየተሰጠ ነው።

በዋቅሹም ፍቃዱ (ሱሉልታ)