Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግብርና ዘርፉን የሚደግፉ አካላትና አመራሮች የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ
**************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚደግፉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የአለም ባንክ፣ የአሜሪካ ተራዕዶ ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የጀርመን የልማት ድርጅት እንዲሁም የጃፓን የልማት ድርጅት አመራሮች ተገኝተዋል።

የቀረበው የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽን ግብርናው አሁን የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅ ትልቅ እድል እንደፈጠረላቸው ጎብኚዎቹ ተናግረዋል፡፡

በአማን ረሺድ
የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪው አቅማቸውን ያገናዘበ አለመሆኑን ወላጆች ገለፁ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉 ጭማሪው የዋጋ ግሽበቱን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የግል ትምህርት ቤቶች ገልጸዋል

👉 ከወላጅ ጋር ስምምነት ሳይደረስ ክፍያውን መወሰን እንደማይቻል መንግስት አሳውቋል


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=99409
የ6ኛ ክፍል ተፈታኞች የሥነ ልቦና ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን ቢሮው ገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የ6ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞቹ ሕፃናት ከመሆናቸው አንጻር በዋናው ፈተና ጊዜ ፍርሃት እንዳይሰማቸው የሥነ ልቦና ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=99479
መልካም ዕድል ለሥራ ፈላጊዎች🙏
ኢትዮጵያ የተገበረችው «ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ»
ሰላምን ለማረጋገጥ ትልቅ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው «ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ» ለመላ አፍሪካውያን ትልቅ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ገለጹ፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪና መምህር አቶ ሱራፌል ጌታሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ በሰሜኑ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=99456
ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛዎች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳዊት መሐሪ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ ተቋራጮች ጋር በጋራ እንዲሠሩ የሚያስገድደው ረቂቅ ሕግ ዝግጅት ተደርጎበታል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=99460
በሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሰራዊት ግዳጁን በብቃትና በጀግንነት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ፣ በሶማሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ሜጄር ጄኔራል አማረ ገብሩ እና ከፍተኛ አመራሮች በበሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት የግዳጅ አፈፃፀም ጎብኝተዋል ።
የቡድኑ አባላት ሻቲጋዱድ ባይደዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴክተር ሶስት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል በስፋት ፈንቴ እንዲሁም የሴክተሩ ከፍተኛ መኮንኖች አቀባበል አድርጎላቸዋል ።
የሴክተር ሶስት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል በስፋት ፈንቴ በሱማሊያ አጠቃላይ የተሰማሩ የሠላም አስከባሪዎች በየሴክተሩ የሰሯቸውን ስራዎች በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል ።
አምባሳደሩ በተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆነውን የአልሸባብ ቡድን በመፋለም እና በተለይም ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ አሥተዋፅኦው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
አጠቃላይ ለሱማሊያ ህዝብና መንግስት እያደረጋችሁት ያለው አስተዋፅኦ የሚደነቅ ነው ያሉት አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቀጣይ ህዝባዊነታችሁን እና ሰብአዊነታችሁን በማጠናከር ከፀጥታ ሃይሉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበትና በትብብር በመስራት አህጉራዊ ተልዕኳችሁን በጀግንነት መፈፀም አለባችሁ ብለዋል ።
በሱማሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ሜጀር ጄኔራል አማረ ገብሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ እያደረገች ያለውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ በመቀጠል እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተልዕኳችሁን ማስቀጠል ይጠበቅባቸኋል ሲሉ መግለጻቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል።
የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት ተፈፅሟል።
ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ በአለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።
ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ አይዘነጋም።
በዳግማዊት ግርማየድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል።
የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት ተፈፅሟል።
ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ በአለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።
ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ አይዘነጋም።
በዳግማዊት ግርማ