Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የኮሚሽኑ አባላት የሀገራዊ ምክክር ፅንሰ ሀሳብን ያብራሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ሀጋራዊ ምክክርን ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችን አቅርበዋል ፡፡
ከቀረቡት የዝግጅት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት የተደረጉ ዝግጅቶች ዋናውን ቦታ የሚይዙ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ ውይይትና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡
በውይይቱም ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች መልሶችንና ማብራርያዎችን መስጠታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦

❶ አቶ አሰፋ ጥላሁን በየነ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣
❷ አቶ በቀለ ወርቁ መንገሻ የሰሜን ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ፣

❸ አቶ ዳኛቸው ፈንታሁን ቁምላቸው የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ፣
❹ አቶ በለጠ ጥጋቡ ዘውዴ የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር ህዝብ ግንኙነት አማካሪ፣
❺ ወይዘሮ ሐብታም አውደው ገበያው የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር የአደረጃጀት አማካሪ፣

❻ አቶ ኑረዲን ሰይድ ኡመር የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳድር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣

❼ አቶ አንተነህ ታደሰ ከበደ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳድር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥተዋል።
“የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የሚመራና የሚተዳደር ማድረግ ተችሏል”
- ሙፈሪሃት ካሚል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት አመቱ ቴክኖሎጂ መር የሆኑ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የሚመራና የሚተዳደር ማድረግ መቻሉን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99583
ዩኒቨርሲቲው በ60 ሚሊዮን ብር በጀት ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ይገኛል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች በማከናወን ላይ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የማህበረሰቡን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉፕሮጀክቶች ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99608
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ላለው የመልሶ ግንባታ ስራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
******************
(ኢ ፕ ድ )
በሰሜኑ ጦርነት በትግራይ ክልል የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99602
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል አገራዊ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልን ዓላማ ያደረገ አገራዊ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99587
“ጠንካራ አመራር እየፈጠርን ኢትዮጵያን ለማበልፀግ የጀመርነውን ጉዞ ከዳር እናደርሳለን”
- አቶ መለስ ዓለሙ የዴሞክራሲና ሲቪል ባህል ግንባታ ሚኒስትር
************************
(ኢ ፕ ድ )
ጠንካራ አመራር እየፈጠርን ኢትዮጵያን ለማበልፀግ የጀመርነውን ጉዞ ከዳር እናደርሳለን ሲሉ የዴሞክራሲና ሲቪል ባህል ግንባታ ሚኒስትር አቶ መለስ ዓለሙ ተናገሩ።
የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የሴቶች አመራር ሰጪነት ሀገር አቀፍ የአሠልጣኞች ሥልጠና በትናንትናው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99620
የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ ልዑክ ለልምድ ልውውጥ ኢትዮጵያ ገባ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ ልዑክ ከኢትዮጵያ ፓርላማ ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል።
በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ለልዑካን ቡድኑ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መልካም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ለልዑካን በድኑ አቀባበል ባደረጉበት ወቅት ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀዋል።
የሁለቱ ሀገራት ምክር ቤቶች ያላቸውን ልምድ የሚለዋወጡበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የገለፁት ሚነስትር ዴኤታው፤ በሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የበለጠ በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተው በትበብር እንደሚሰሩ የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ፤ ልምድ ለውውጡ ጠቃሚ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር የከተበሩ ጀምስ ንክሳማሎ ለልዑካን ቡድኑ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነው፤ የሁለቱ ሀገራት ምክር ቤት አባላት የሚያደርጉት የልምድ ልውውጥ ዋና አላማው የወከላቸውን ሕዝብ በብቃት እንዲያገለግሉ ለማስቻል ነው ብለዋል።
ሀለቱ ሀገራት በጋራ የሚያከናውኗቸው በርካታ ተግባራት መኖራቸውን የገለጹት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ፤ በምክርቤታዊ አሰራሮች ዙሪያ በሚካሄዱ የልምድ ልውውጥ ውይይት ጠቃሚ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሆነ መናገራቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
የጡት ካንሰር ሞትን ለመቀነስ ምዕናባዊው ሆስፒታል ወደ ትግበራ እየገባ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ )
የጡት ካንሰር ሞትን ለመቀነስ እንደሚያስችል የታመነበት ምዕናባዊው ሆስፒታል ወደ ትግበራ እየገባ ነው ሲል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ:: የምናባዊ ሆስፒታሉ ህክምና በጡት ካንሰር የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ይቀንሰዋል ተብሏል::
ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ቆይታ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99647
ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከሚኒስቴሩ በተገኘው የዘጠኝ ወር ሪፖርት መሰረት፤ በ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 381 ሺህ 543 ነጥብ 43 ቶን የሆርቲካልቸር ምርቶችን ወደውጭ ሀገራት በመላክ 549 ነጥብ 46 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99633
መልካም ዕድል ለሥራ ፈላጊዎች🙏