Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መልካም ዕ ድል🙏
አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ከሆኑት ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮ ጋር ተወያዩ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል የሆኑትን ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የክብር ቆንስሉ በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ኢትዮጵያንና ህዝቧን በመወከል እያበረከቱት ስላለው አስተዋጽኦ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮያ እና ቤላሩስ በተለይ በኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ ግብርና ሜካናይዜሽን እና ማዕድን ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል። "ይህን ለማሳካት በእኛ በኩል የምንችለውን እናደርጋለን" ብለዋል።
ሚስተር ዲሚትሪ ሉካሼንኮ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቲዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለሱዳን ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የፌዴራል መንግስት ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሱዳን ጦርነትን ተከትሎ ወደኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ግብረኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሱዳን የተከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99673
“ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን"
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
************************
(ኢ ፕ ድ)
ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ፤ ወዳጅ እንዲተማመን፣ ጠላት እንዲመነምን መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን ሲሉ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ባለቤትነት በእውነተኛ ታሪክ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99679
ከ59 ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች በከተማ ግብርና ላይ እየተሳተፉ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ በከተማ ግብርና የሚሳተፉ ዜጎች ቁጥር ከ59 ሺህ በላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አካሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ በከተማ ግብርናና ሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ዜጎች በስፋት እንዲሳተፉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
በዘጠኝ ወራት በእንስሳት ዘርፍ 17 ሺህ 224፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ 42 ሺህ 374 በድምሩ 59 ሺህ 571 ዜጎች በከተማ ግብርና ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99689
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ ገባ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።
ልዑኩ ጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል አድርገውለታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የላፕሴት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን አገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ስራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።
ከኢትዮጵያና ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ ይዘጋጃል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ከኢትዮጵያና ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ ሊያዘጋጅ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሰታወቀ።
ኮንፈረንሱ "ማህበራዊ ጥበቃ ለሃገር ገጽታ" በሚል መሪ ቃል ግንቦት 15 እስከ 16 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶክተር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በኮንፈረንሱ ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ።
በመድረኩ የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞች አተገባበርና ሥርዓት ግንባታን የሚሳዩ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ይቅርባሉ ያሉት ሚኒስትሯ በምሁራንና በባለሙዎች ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋል።
በሃገሪቱ በተለያዩ ተቋማት በማህበራዊ ጥበቃ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮግራሞችን የሚያሳይ ኤግዚቢሽንም ለዕይታ ይቀርባል።
ኮንፈረንሱ የተለያዩ አካላትን ግንዘቤ ለማሳደግና በቀጣይ ሁሉም አካላት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ድጋፍ እንደያጎለብቱ በማድረግ ጠንካራ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት በመዘርጋት ዜጎችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እገዛ እንደሚደርግ ይጠበቃል ብለዋል።
ኮንፈረንሱ ግንቦት 15 እና 16 የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
በዳግማዊት አበበ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አትላንታ ከተማ በሳምንት አራት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ጀምሯል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ አትላንታ ከተማ በሳምንት አራት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ መጀመሩን አሰታውቋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲክሰን፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰንን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲክሰን የተመራልዕኩ በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።
የኢፕድ የስራ ማስታወቂያ፤ መልካም ዕድል 🙏