Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አትላንታ ከተማ በሳምንት አራት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ጀምሯል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ አትላንታ ከተማ በሳምንት አራት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ መጀመሩን አሰታውቋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲክሰን፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰንን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲክሰን የተመራልዕኩ በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።
የኢፕድ የስራ ማስታወቂያ፤ መልካም ዕድል 🙏
ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን ከ61 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል
************************
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ከ61 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍያ መፈጸማቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አሰታወቀ።
በገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ሂሳቦች ዳይሬክቶሬት ገቢ ሂሳቦች ማጠቃለያ ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ አሸናፊ እንደገለፁት በ2015 በጀት ዓመት አስር ወራት ውስጥ በኤሌክትሮኒክ የመክፈያ ዘዴ ግብራቸውን ከከፈሉ 20 ሺህ 772 ግብር ከፋዮች ውስጥ 8 ሺህ 56 ግብር ከፋዮች በዘንድሮ የበጀት ዓመት የክፍያ አማራጩን ለመጠቀም የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
በተጨማሪም 61 ቢሊዮን 468 ሚሊዮን 847 ሺህ 530 ብር በአስር ወሩ በዚሁ የክፍያ መንገድ መሰብሰብ ተችሏል።
ስርዓቱ ግብር ከፋዮች ከአላስፈላጊ የገንዘብና የጊዜ ብክነት ተላቀው በቀላሉ ግዴታቸውን እንዲወጡ ያስቻለ መሆኑን ቡድን አስተባባሪዋ አንስተዋል፡፡
በአጠቃላይ የኤሌክትሮኒክ መክፈያ ስርዓት ከተዘረጋበት ጊዜ አንስቶ 22 ሺህ 419 ግብር ከፋዮች የከፈሉ ሲሆን 127 ቢሊዮን 180 ሚሊዮን 14 ሺህ 279 ብር በዚሁ የመክፈያ አማራጭ መሰብሰቡ ተመልክቷል፡፡
«የሱዳን ሰላም ከኢትዮጵያ ሰላም ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ለሱዳን ሰላም መሥራት ይገባል» - ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የሱዳን ሰላም መሆን ከኢትዮጵያ ሰላም ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ ልትቀጥል እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናት ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ገለጹ።
ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሥርዓቶች ውስጥም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99753
👉 «የመንገድ መሠረተ- ልማት ችግር ፓርኮችን ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎች እያጋለጠ ነው»- ብሔራዊ ፓርኮች
👉 «ችግር ያለባቸውን ፓርኮች በመለየት መንገድ እንዲሟላላቸው እየሠራን ነው» -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርኮች አስተዳደር
****************
(ኢ ፕ ድ)
የመንገድ መሠረተ- ልማት ችግሮች ፓርኮችን ለተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች እያጋለጠ መሆኑን የጋምቤላና የኦሞ ብሔራዊ ፓርኮች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርኮች አስተዳደር በበኩሉ የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ፓርኮች በመለየት ችግሮቻቸውን ለመፍታት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ አሰግድ ገብሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በፓርኩ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99754
1
ዩኒቨርሲቲው ለመውጫ ፈተና 3 ሺህ 600 ተማሪዎችን እያዘጋጀ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና የሚወስዱ 3 ሺህ 600 ተማሪዎችን እያዘጋጀ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ይሰጣል።
የመውጫ ፈተና አዲስ አሠራር በመሆኑ በተማሪዎች ዘንድ መደናገጥና ፍርሃት እንዳይፈጠር ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሥነልቦና የማዘጋጀትና በትምህርታቸው ብቁ እንዲሆኑ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99760
በማዕድን ዘርፍ በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት እና ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ ጋር በማዕድን ዘርፍ በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሁለቱም ሀገራት የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዘርፉ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሮቹም ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በማዕድን ዘርፍ በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት እና ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ ጋር በማዕድን ዘርፍ በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሁለቱም ሀገራት የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዘርፉ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሮቹም ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።
ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
የኮንስትራክሽን ኤክስፖና አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከዲ ኤም ጂ ኢቨንትስ፣ከኢትኤል ኢቨንትስና ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን ያዘጋጁት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ የሀገሪቱን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለማነቃቃትና የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
መድረኩ የዘርፉን ተዋናዮች ለማገናኘትና አብሮ የመስራት ባህልን ለማጎልበት የላቀ ሚና ይኖረዋል። ከ24 ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
ኤክስፖው ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገት ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ለማግኘት፣ ለልምድ ልውውጥ፣ በዘርፉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡
በኤክስፖው ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ላይ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ከኤክስፖው ጎን ለጎን በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጀ የሚኒስትሮች የጋራ ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።
መላኩ ኤሮሴ