Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢፕድ የስራ ማስታወቂያዎች፤ መልካም ዕድል‼️
የአፍሪካ ኅብረት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ ም ጀምሮ ይከበራል
**************************
(ኢ ፕ ድ)

የአፍሪካ ኅብረት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት እንደሚከበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኅብረቱ አባል ሀገራት በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች በየሀገራቸው እንደሚያከብሩም ጠቁመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በዓሉን የምታከብረው የኅብረቱን ዓላማ ለማሳካት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን በማጉላትና የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ለማፅናት በሚያስችል ሁኔታ እንደሆነ ገልጸዋል።

ባለፉት 60 ዓመታት የአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ጉዞ፣ እንቅስቃሴ፣ ስኬቶችና ፈተናዎች ተዳስሰው አፍሪካውያን ለተሻለ ሥራ የሚንቀሳቀሱበት ይሆናል ብለዋል።

ከሱዳን ቀውስ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያና የሌሎች አገራት ዜጎችን የማስወጣቱ ሂደት ቀጥሏል። መረጃው እስከተሰበሰበበት ጊዜ ድረስ በመተማና በኩምሩክ በኩል በድምሩ 17 ሺህ 885 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። የሱዳን ችግርም በሰላም እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግሥት የጸና አቋም እንዳለው ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99837
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ጋር ብሄራዊ ሙዚየምን ጎበኙ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ጋር ብሄራዊ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
በኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራው የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን መጎብኘታቸው የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የጉብኝቱ መርሀግብር በቱሪዝም ሚኒስቴር እና በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ነዉ ተብሏል።
"ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች" አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
*******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።

አምባሳደሩ ምስጋኑ አርጋ የአለምአቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቢባቶ ዌንፎል ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በድርጅቱና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለውን ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የውጭ ስደተኞችን ተቀብላ የምታስተናግድ እንዲሁም የሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ያሉባት ሃገር እንደመሆኗ ከአለምአቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በጠንካራ ትብብር ትሰራለች ብለዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የፍልሰት የደቀነውን ችግር ለመቅረፍ ድርጅቱ የሚሰራቸውን ስራዎች የኢትዮጵያ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚደግፍ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋግጠዋል።

በተለያዩ ግጭት ባለባቸው ሃገራት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ለመደገፍ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ውይይት አድርገዋል።
የአለምአቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቢባቶ ዌንፎል ድርጅታቸው ለሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለውጭ ፍልሰተኞች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ዋና ተወካይዋ ኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት የምንሰጣት ሃገር ናት ብለዋል ፤ የውጭ ፍልሰተኞችን በመቀበል ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተች እንደመሆኗን በመጥቀስ ።
በኢትዮጵያ መንግስት እና አለምአቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት መካከል እያደገ የመጣ ግንኙነት መኖሩን አስታውሰው ፤ በቀጣይም ከፍልሰት ጋር በተያያዙ ማዕቀፎች ትብብራቸው እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የአፍሪካ አገሮች በሙሉ ለኢትዮጵያ ስንዴ የገበያ መዳረሻ ናቸው
******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በመስኖ ለምታለማው የስንዴ ምርት ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በሙሉ የገበያ መዳረሻ ናቸው ሲሉ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ አስታወቁ።
ዶክተር ማንደፍሮ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ ስንዴ በማምረቱም ሆነ በገበያው ብዙ ዕድሎች ስላሏት የአፍሪካ ሀገሮች የገበያዋ መዳረሻ ይሆናሉ።
በአሁን ወቅት የሌላውን አገር በመተው አፍሪካን ብቻ ብንወስድ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99904
በኢትዮጵያ ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶ በአሲዳማነት እየተጠቃ ነው
👉 በቀጣዩ ዓመት የአፈር ለምነት ሀገራዊ ንቅናቄ ይካሄዳል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ አሁን ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶው (ሰባት ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት) በአሲዳማነት እየተጠቃ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። አፈርን ከአሲዳማነት ለመታደግ በቀጣዩ ዓመት የአፈር ለምነት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚካሄድም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ የኢፌዴሪ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የፌዴራልና የክልል መገናኛ ብዙኃን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99924