Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር በዛላ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ እርሻን ጎበኙ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጂጌ በዛላ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ እርሻ ማሳን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት አቶ ተስፋዬ እንደገለፁት አከባቢው ለተከታታይ አመታት በእርጥበት እጥረት ለድርቅ የተጋለጠ ቢሆንም የጠንካራ የስራ ባህል ባለቤት የሆነው የዞኑ አርሶ አደር ተስፋ ሰጪ የበቆሎ እርሻ አሳይቶናል ብለዋል።
በጉብኝቱም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ሲል ምክር ቤቱ ዘግቧል።
የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የተቋማት አፈጻጸም ግምገማ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የምክር ቤት አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የተቋማት አፈጻጸም ግምገማ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ባለፈው ሳምንት የሚኒስትሮች የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም መገምገሙ ይታወቃል።
በመድረኩ የዘጠኝ ወር የማክሮ ኢኮኖሚውን እና የሴክተሮች ልዩ አፈጻጸም ተገምግሟል።
የሚኒስትሮች የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ በመወያየት አቅጣጫ ማስቀመጡም ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ የሚኒስትር ዴኤታዎችና የተቋማት የዘርፍ አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፤ ባቀረቡት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት የማኮሮ ኢኮኖሚው አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በየዘርፎቹ በበጀት ዓመቱ 7 ነጥብ 5 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት የሚያስችል አመላካች ውጤት መኖሩን ተናግረዋል።
በዚህ መድረክ በስድስት ወራት ግምገማ ወቅት የተቀመጡ አፈጻጸሞች ግምገማ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም እንደሚገመገም፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ተናግረዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በመድረኩ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤት አባላትና ቋሚ የኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
መድረኩ ነገም የሚቀጥል ሲሆን በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ የሚመክር ይሆናል።
ክልሎች በግብርና ተፋሰስ ስራ ላይ አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች በግብርና ተፋሰስ ላይ አመርቂ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የየክልሉ የግብርና ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች ገለፁ፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አልማዝ ጊዜው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ በስምንት ሺህ 548 ተፋሰሶች ላይ ለመስራት ታቅዶ ከተያዘው እቅድ በላይ እንደተሰራ ገልፀዋል፡፡
እንደ ዶክተር አልማዝ ገለፃ፤ እቅዱን ለማከናወን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100053
(ፎቶ ፋይል)
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
ኢትዮጵያን ለመለወጥ መፍትሔ ተኮር መሆን የግድ ነው። የተለያየ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡበት ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጀምሯል። እንበርታ ፣ እንፍጠር ፣ ፈተናን ለማለፍ መፍትሔ ላይ እናተኩር።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በአፍሪካ ልማት ባንክ የአስተዳደሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው
**************
(ኢ ፕ.ድ)
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በግብጽ ሻርም አል-ሼይክ በተጀመረው የአፍሪካ ልማት ባንክ የአስተዳደሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ስብስባው “የግሉን ዘርፍ ፋይናንስ ለአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ እድገት ....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02KiEQiVxvLNzP98HVLYd5qwSTz8RvAiwJLNYK6ezscBbVtWcJdzGZF3NAej8c2bol
የግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም የሥራ ማስታወቂያዎች። መልካም ዕድል🙏
#ከኢፕድ_ማህደር ‼️
ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ የተያዘው ወንድ ልጅ ከእስሩ ነጻ ሆነ
አፍሮ ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ በመገኘቱ ለባህል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት ፈጽሟል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በቅርቡ ታስሮ የነበረው አበበ ወልደፃድቅ ከክሱ ነጻ ሆኖ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን የአዲስ አበባ አውራጃ ፍርድ አቃብያን ህግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
አበበ ክስ ቀርቦበት ሊታሰር የቻለው በቅርቡ አፍሮውን ሹሩባ ከተሰራ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ አፍንጮ በር አካባቢ 50...https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02iQuLEVfPQVVhW1guLe227x24WgNghLDZpqnT5pxVMS72WrFWYFhCrgUrejqp3qSsl