Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
ኢትዮጵያን ለመለወጥ መፍትሔ ተኮር መሆን የግድ ነው። የተለያየ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡበት ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጀምሯል። እንበርታ ፣ እንፍጠር ፣ ፈተናን ለማለፍ መፍትሔ ላይ እናተኩር።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በአፍሪካ ልማት ባንክ የአስተዳደሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው
**************
(ኢ ፕ.ድ)
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በግብጽ ሻርም አል-ሼይክ በተጀመረው የአፍሪካ ልማት ባንክ የአስተዳደሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ስብስባው “የግሉን ዘርፍ ፋይናንስ ለአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ እድገት ....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02KiEQiVxvLNzP98HVLYd5qwSTz8RvAiwJLNYK6ezscBbVtWcJdzGZF3NAej8c2bol
የግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም የሥራ ማስታወቂያዎች። መልካም ዕድል🙏
#ከኢፕድ_ማህደር ‼️
ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ የተያዘው ወንድ ልጅ ከእስሩ ነጻ ሆነ
አፍሮ ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ በመገኘቱ ለባህል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት ፈጽሟል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በቅርቡ ታስሮ የነበረው አበበ ወልደፃድቅ ከክሱ ነጻ ሆኖ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን የአዲስ አበባ አውራጃ ፍርድ አቃብያን ህግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
አበበ ክስ ቀርቦበት ሊታሰር የቻለው በቅርቡ አፍሮውን ሹሩባ ከተሰራ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ አፍንጮ በር አካባቢ 50...https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02iQuLEVfPQVVhW1guLe227x24WgNghLDZpqnT5pxVMS72WrFWYFhCrgUrejqp3qSsl
አቶ ደመቀ መኮንን ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
**********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ሐርጂት ሲንግ ሳጃንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ሁለቱ አካላት በኢትዮጵያ እና ካናዳ መካከል ያለውን የልማት ትብብር የበለጠ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid0sFY4b3HeburMERJN8oGh8B1pPpxWzEHdP7qB87hnsApHTtPjJRmYTN5gQ9rxkH6Fl
የአሜሪካ ኤምባሲ በእውቀት ሽግግር ላይ የሚሰራ ማእከል በቅድስተ ማርያም ዩኒቨርስቲ ከፈተ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአሜሪካ ኤምባሲ የእውቀት ሽግግር ላይ የሚሰራ የኮሎኔል ጆን ሲ. ሮቢንሰን መታሰቢያ ማእከልን በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲ ከፈተ።
ማእከሉን መርቀው የከፈቱት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ማእከሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ወጣቶች ሳይንሳዊ እውቀትን የሚያገኙበት፣ ከቴክኖሎጂ ጋር የሚላመዱበትና የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን....
https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02UXUi3pVWgUnT7rny3MD3m3kcc7BrG9sxLt7E7yUGK29sqUCBekGAAa9r5PzFRre7l