Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም የሥራ ማስታወቂያዎች። መልካም ዕድል🙏
"ማህበራዊ ጥበቃ ለሰብአዊ መብትና ደህንነት መሰረት በመጣል የመንግስትን ማህበራዊ መሪ ከህዝቡ ጋር የሚያስተሳስር ተግባር ነው" - አቶ ደመቀ መኮንን
***************************
(ኢ ፕ ድ)
ማህበራዊ ጥበቃ ሰብአዊ መብትና ደህንነት መሰረት የሚጥልና የመንግስትን ማህበራዊ መሪ ከህዝቡ ጋር የሚያስተሳስር ተግባር ነው ሲሉ ምክልት ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።
ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ "ማህበራዊ ጥበቃ ለሃገር ግንባታ....
https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02Cguv9ehKqteTsyXFBXuK4LhLFUG5nuZudKU7nBTt37YHHeGuDEsaYwzfh2CxX7Frl
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከካናዳ አለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ላይ እየተሰሩ ያሉና ውጤት የተመዘገበባቸውን የግብርና ልማት ስራዎችን ለካናዳ አለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር እና ለልዑካን ቡድናቸው አብራርተዋል፡፡
https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid024WHX3cyhJwPwbQ3B6s3uftQ7kPBmpNhe3Tvavr3npLVD2yzu1wkzA5Lrd6vQFRsBl
የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ከ20 በላይ ድርጅቶች ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸው የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታወቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
መንግስት ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዛወር ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ከ20 በላይ ኩባንያዎች በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸው የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታወቀ።

በመንግስት የተያዙ 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዛወር መንግስት ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

ፋብሪካዎቹም አርጆ ዴዴሳ፣ ከሰም፣ ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ ጣና በለስና ተንዳሆ ናቸው።

ከ20 በላይ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መንግስት ባወጣው ጨረታ ላይ ለማሳተፍ ፍላጎት አሳይተዋል። በዚህም የጨረታ ማስረከቢያውን ሂደት የሚገልጽ አጠቃላይ የጨረታ ሰነድ መውጣቱ ተገልጿል።
“ግብጽ የአረብ ሊግ መሪነቷን በመጠቀም የዓባይ ግድብ ላይ ያላትን ኢፍትሃዊ ፍላጎት ለማሳካት እየሞከረች ነው‘
- ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ የውሃ ፖለቲካ ተመራማሪ
************************
(ኢ ፕ ድ)
ግብጽ የአረብ ሊግ መሪነቷን በመጠቀም በዓባይ ግድብ ላይ ያላትን ኢፍትሃዊ ፍላጎት ለማሳካት እየሞከረች መሆኑን የውሃ ፖለቲካ ተመራማሪና የዓባይ ግድብ ዓለም አቀፍ ተደራዳሪ ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአረብ ሊግ መግለጫ የሰጠው ምላሽ የዓለምአቀፍ ማህበረሰቡ እውነታውን....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02Jk8ggfZdKWPLZD6rXpv3SN9cGH3kfnHr993DQgsnAN36eXwpou9EQchVHBK2n849l
በአማራ ክልል 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል አምሥተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ መርሃ ግብር አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። እስካሁን ከ850 ሺህ በላይ ችግኞች ለተከላ ደርሰዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አልማዝ ግዜው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመጪው.....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid05QP2yzAZFed9NjER5mZggH72e8AgJk9NuaCHveQzrcxxZXwBcqnpijKoYXzybEgBl
የቀደምት አፍሪካውያን መሪዎችን ራዕይ እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን ይገባል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ህብረትን 60ኛ ዓመት ስናከብር ቀደምት የአፍሪካ መሪዎች ጠንካራና አንድነቷ የተጠበቀ አህጉር ለመፍጠር የነበራቸውን ራዕይ እውን ለማድረግ መትጋት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው የአፍሪካ ህብረት የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት በማስመልከት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ ቀደምት የአፍሪካ ....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02zJkGnvJKHtLLFTFZXiSBfEgNu8N8d8yxgfrWwqri5Lwju1ZpyYqYtWvJ8neQdiKfl