Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#የአፍሪካ_ቀን‼️
አፍሪካዊያን በጋራ የመሠረቱት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ አፍሪካ ህብረት ከተመሠረተ 60 ዓመታትን አስቆጠረ።
ይህንን በዓል በማስመልከት የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ዛሬ ይታያልል።
በፎቶግራፍ አውደ ርዕዩ የትናንቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ባለፉት 60 አመታት የተጓዘውን ጉዞ የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች ለእይታ ቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እለታዊ መረጃን እየዘገበ ታሪክ በመሰነድ 82 አመታት ‼️
የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት የምስረታ በአል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሐማት፣ የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በተገኙበት “የእኛ አፍሪካ የወደፊት ዕጣችን” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትረ ዐቢይ አህመድ፤ "አፍሪካ ባላት የህዝብ ብዛት ልክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በወቅቱ ነጻነታቸውን በተጐናጸፉ 32 ሀገራት መመስረቱን አስታውሰው፤ ለአፍሪካ ብልጽግና በጋራ በመስራት የመስራች አባቶቻንን አላማ ማሳካት ያስፈልጋል ብለዋል።

አሁን አፍሪካን ወደ አንድነትና ወደ ብልጽግና ለማሻገር ባላት የህዝብ ብዛት ልክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል ሲሉም ነው የተናገሩት።

ጠንካራ አህጉራዊ ሚዲያ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንደ ረሃብና ግጭት ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት ይገባል፤ አህጉሪቷ በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ተጠቅሞ ለዜጐቿና ለኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ ማድረገ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በሙስና፣ በግጭትና በብልሹ አሰራር ምክንያት አብዛኛው ህዝብ በድህነት የሚኖር በመሆኑ ይሄንን ተግዳሮት መቅረፍ የግድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
አዲስ ዘመን ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
“አጀንዳ 2063ን ተግባራዊ በማድረግ አፍሪካን የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አህጉር ማድረግ ይገባል”
ሙሳ ፋቂ ማሐመት
****
(ኢ ፕ ድ)
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት የምስረታ በአል በህብረቱ ዋና መስሪያ ቤት ተከብሯል።

በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሐመት እንደገለጹት፤ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ብዙ ስኬቶችን ቢያሳካም በርካታ ችግሮችም ነበሩበት ብለዋል።

አጀንዳ 2063ን ተግባራዊ ለማድረግ የጦርነት ድምጽ የማይሰማባት አህጉር ማድረግ ይገባል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ የውስጥ ግጭትን መቀነስ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።

የህብረቱን 60ኛ አመት ስናከብር ግጭቶችን፣ አሸባሪነትንና ድህነትን መዋጋት ያስፈልጋል፤ በግጭት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጐችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ (ሲድካ) ሊቀመንበር ሊዎ ጃወሁይ ጋር ዛሬ በቤጂንግ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት አቶ ደመቀ ቻይና በአገሮች የውስጥ ነጻነት ጣልቃ ሳትገባ የጋራ ተጠቃሚነት መርሆዎች ላይ በመመስረት ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቻይና በደቡብ-ደቡብ የትብብር ማዕቀፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኗንም ተናግረዋል፡፡

በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም ( ፎካክ) የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ ይፋ በተደረጉት ዘጠኙ መርሃ ግብሮች መሰረት እ.ኤ.አ. ከ2022 እስከ 2024 የተያዙ አዳዲስ እና ነባር ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ እስከ ፕሮጀክቶቹ ፍጻሜ ድረስ ተቋሙ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው ቻይና ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የመልሶ መቋቋምና ዳግም ግንባታ ድጋፍ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሊቀመንበር ሊዎ ጃወሁይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ አጋር ብቻ ሳትሆን በአፍሪካ ትልቅ ተፅዕኖ ያላት አገር በመሆኗ ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ በትምህርት፣ በግብርና፣ በተፋሰስ ልማት እና ሌሎችም መስኮች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡
ለፕራይም ቲሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
****************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለፕራይም ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አሰታወቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መገናኛ ብዙኃን በዜጎች መካከል አብሮነትን ከሚሸረሽርና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለአለመተማመን ከሚዳርግ የይዘት ስርጭት እንዲቆጠቡ ግዴታ ይጥላል፡፡

በኢፌድሪ ህገመንግስት፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና በሌሎች ተያያዥ ሕጎችም ፤ የመገናኛ ብዙኃን በተለይም የጋራ እሴቶችን የሚንዱ፣ አለመቻቻል እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ እና ዜጎችን ለግጭት ሊያነሳሱ የሚችሉ ስርጭቶችን ከማስተላለፍ እንዲታቀቡ ይደነግጋሉ፡፡

ፕራይም ቴሌቪዥን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሕግጋት የሚጥሱ ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ሲያሰራጭ መቆየቱን በክትትል ሥራችን አረጋግጠናል። ከክትትል ውጤቱም በመነሳት በተደጋጋሚ እርምት እንዲወሰድ ግብረመልስ ተሰጥቶታል፤ በቅርቡም በቀን 4/9/2015ዓ.ም በባለሥልጣ ጽ/ቤት ውይይት ማካሄዱን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ፕራይም ቴሌቪዥን ስህተቱን በመቀጠል የዜጎችን አብሮነት የሚጎዳ፣ ይልቁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሹ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አሉታዊና ሕግን የሚተላለፉ ይዘቶችን በማሰራጨት ዜጎችን ላልተገባ ውጥረትና አደጋ አስተዋፅኦ የማድረግ አዝማሚያ እንደታየበትም ተጠቁሟል፡፡

ይህም በተለይም ፕራይም ቴሌቪዥን እንደ ንግድ ብሮድካስተር ከገባው የውል ግዴታና ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር ተገቢ ያልሆነ ተግባር እንደሆነ ታምኖበታል ሲልም ባለስልጣኑ ለኢፕድ በላከው መግለጫው አስታውቋል፡፡

ስለዚህም ፕራይም ቴሌቪዥን ከዚህ ድርጊቱ እንዲታረም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማት አሸነፈ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማት አሸንፏል፡፡ አየር መንገዱ ሽልማቱን የተቀዳጀው በምርጥ የበረራ መስተንግዶ፣ መዝናኛ ፣ ምግብና መጠጥ፣ ምቾት እንዲሁም በገመድ ዓልባ የኢንተርኔት “ዋይ ፋይ”አገልግሎት ዘርፎች መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።