Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ እግድ መነሳቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ
ክልሎች በመጋዘን የሚገኘውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ በወቅቱ እንዲያደርሱ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሎች በመጋዘን የሚገኘው ሰባት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ በወቅቱ ማድረስ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።
የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ለ2015/16 ምርት ዘመን 12 ነጥብ 87 ሚሊዮን ኩንታል በመግዛት እና የከረመውን ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ጨምሮ በምርት ዘመኑ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100618
በትግራይ ክልል በሁለት ወራት የእናቶችና ሕፃናት ክትባት ሽፋንን 83 በመቶ ማድረስ ተችሏል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ክልል ጤና ዘርፍ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ በሁለት ወራት ውስጥ በተከናወኑ ስራዎች የእናቶችና ሕፃናት ክትባት 83 በመቶ መድረሱን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ተስፋይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የክልሉ የጤና ዘርፍ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ምንም አይነት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100629
ለአርሶ አደሮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው
- የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
የዲጂታል ግብርና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በሚል መሪ ሀሳብ የፖናል ወይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ለአርሶና አርብቶ አደሮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ሥርዓት ለመዘርጋትና በግብርናው ዘርፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተደራሽነትን እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የግብርናው ዘርፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አገራዊ የኢኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው፡፡
የኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊን በበኩላቸው እንደ አገር በግብርናውን ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሩ መረጃ ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ይረዳል፡፡
በተለይም እንደ አገር ዘርፋ የተሻለ ቴክኖሎጂ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በውይይቱ የፌድራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በማርቆስ በላይ
የአዲስ ዘመን ጋዜጣ የግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ፣ መልካም ዕድል‼️
ዶክተር አረጋዊ በርሄ የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ይናገራሉ‼️

👉 ኢትዮጵያ ዓባይን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ መጠቀሟን ትቀጥላለች፣

👉 ዓባይን የመጠቀም ጉዳይ ዓባይ በሚደርስባቸው የተፋሰሱ አገሮች ብቻ መታየት ይኖርበታል፣

👉 የዓረብ ሊግም ጉዳዩን ሲያይ በሐቅ እና በፍትሐዊነት ላይ ተመሥርቶ አልነበረም፤ ከግብፅ ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት በሚያንፀባርቅ መልኩ አድሏዊ በሆነ መንገድ ነው፤ ይህ በዓለም አቀፍ የውኃ ሕግ ተቀባይነት የለውም፣

👉 በየትኛውም የሕግ መለኪያ የዓረብ አገሮችም ሆኑ ምክር ቤቱ በምንም መልኩ ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች በሚመለከታቸው የተፋሰሱ አገሮች ላይ ጣልቃ መግባት አይችሉም፣

👉 ግብፅ ከድሮ ጀምሮ የዓባይን ውሃ ለመቆጣጠርና የበላይነቷን ለማረጋገጥ በየትኛውም መልኩ ጥረት ታደርጋለች፣ የዓባይን ውሃ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እስከ መክፈት የደረሰችበት ጊዜም ነበር፣

👉 በፍትሐዊነት መንገድ ሦስቱ አገሮች ቁጭ ብለው ተወያይተው ችግሩን መፍታት ይችላሉ፣

👉 የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የሚለውን መርሕ ተከትላ አስፈላጊም ከሆነ ሁለተኛ ወገን ጨምራ በመወያየት የጋራ ጥቅምን ማስከበር ይቻላል፣

👉 ከመነሻው ግብፅ ፍትሐዊ የሆነ የውሃ ክፍፍልን አትፈልግም፤ ይህንን ፍትሐዊ ያልሆነ ክፍፍል ሊደግፍና ተግባራዊ እንዲሆን ሃሳብ ሊሰነዝርላት የሚችለው የዓረብ ሊግ ወይም ዓረብ አገራት ናቸው ብላ ታምናለች፣

👉 ግብፆችን ወዳልተገባ አካሔድ የሚገፋቸው በአንድ በኩል ፍራቻ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውሃውን ተጠቅማ ማደግ ከጀመረች ወደ ፊት የበላይነትን ትይዛለች ከሚል ስጋት እንጂ ሌላ ተጨባጭ ምክንያት የላቸውም፣

👉 ለሦስተኛ ጊዜ ውሃው የተሞላ ሲሆን፣ በሁለት ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ተጀምሯል፣

👉 ከሚመነጨው ኃይል ወደ ሱዳን ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ በመሸጥ ላይ ነው፣

ሙሉ ቃለምልልሱን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100635
የሃስት ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ወንጀል ፈጻሚዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ማህተሞችን በመጠቀም የሃስት ሰነዶች ሲያዘጋጁ የነበሩ ወንጀል ፈጻሚዎች የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

አቶ አሻግሬ በለጠ አለሙ የተባለው ግለሰብና ግብረአበሮቹ በአራዳ ክፍለ ከተማ 511 ማህተሞችን በመጠቀም የሃሰት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ሰነዶች ሲያዘጋጅ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ከ1500 እስከ 4500 ብር በማስከፈል የሃስት ሰነዶችን በማዘጋጀት የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል።

ወንጀል ፈጻሚው አቶ አሻግሬ በለጠ አለሙ እና ግብረአበሮቹ ሃስተኛ የሆኑ የመከላኪያ ሠራዊት የስንብት ወረቀት፣ የመከላከያ የፍቃድ ወረቀት፣ የብሔራዊ መረጃ መታወቂያ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣ የመከላከያ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ሻ/ቃ፣ የመከላከያ ሠራዊት መታወቂያ አዘጋጅተው ተይዟል።

በተጨማሪም ግለሰቦቹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፌደራል አስተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት፣ የፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ማዕከላዊ፣ 31ኛ ክፍለ ጦር መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሉ የሃስት ሰነዶችን በማዘጋጀት ለወንጀል መፈጸሚያ እንዲውሉ ሲሰሩ እንደነበረ በኤግዚቢትነት የተያዙ ማስረጃዎች ያሳያሉ ሲል የአዲስ አበባ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
የአረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የያዘው አቋም በወንድማማች የኢትዮጵያና የግብጽ ህዝቦች መካከል መጠራጠርን የሚፈጥር ነው-አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ
******
(ኢ ፕ ድ)

የአረብ ሊግ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የያዘው አቋም በወንድማማች የኢትዮጵያና ግብጽ ህዝቦች መካከል ልዩነትና መጠራጠርን የሚፈጥር አካሄድ መሆኑን የውኃ ኃብት አስተዳደር አማካሪው አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያለውን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስረዳት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘርባትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ይኖርባታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ያደረገ ጥናት በማከናወን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከጀመረች አስር ዓመታት አልፈዋል፡፡

ግድቡ ኢትዮጵያ ፍትሐዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርህን በመከተል በተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ከላይኛውና ታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር በጋራ የመልማት አላማ እንዳላት የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን በተፈጥሮ ሀብቷ መልማትና መጠቀም የማይፈልጉ አካላት፤ የግድቡን ግንባታ በሚመለከት ያልፈረመቻቸውን የአንድ ወገን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በማንሳት ይቃወማሉ።

የነዚህ አካላት ሚዛን የሌለውና እውነታ ላይ ያልተመሰረተ አካሄድ ኢትዮጵያ ዛሬም በድህነት እንድትማቅቅ ከመፈለግ የመነጨ መሆኑን ምሁራን ይገልጻሉ።

ከዚህም ባለፈ ከዓለም አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የውሃ አጠቃቀም ህግ ባፈነገጠ መልኩ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ተፅዕኖ ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡

የውኃ ኃብት አስተዳደር አማካሪው አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በወሰን ተሻጋሪ ወንዞች መካከል የሚፈጠረውን ልዩነት በተመለከተ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ባይገባ ተመራጭ ነው፡፡

በወሰን ተሻጋሪ የውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚፈልጉ ሶስተኛ ወገኖች ቢኖሩም አብዛኞቹ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የሚሞክሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የአረብ ሊግን ጨምሮ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩ አካላት የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ ዘላቂ ተጠቃሚነት ከማጎልበት ይልቅ ልዩነት የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት በውሃ አጠቃቀም ላይ ያሏቸውን ልዩነቶች በራሳቸው ተመካክረው ከመፍታት የተሻለ አማራጭ እንደሌላቸው በመጠቆም።

የዓባይን ወንዝ ምክንያታዊና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚወስነው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ብቻ ነው ያሉት አቶ ፈቅአህመድ፤ መንግስት የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ የውሃ አጠቃቀም መርህ እንዲወጣ በማድረግ በጋራ የመልማት ፍላጎት እንዳለው ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

የአረብ ሊግ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ወንድማማች በሆኑት የኢትዮጵያና ግብጽ ህዝቦች መካከል ልዩነትና መጠራጠርን ስለሚፈጥር የግብጽ ህዝብ ሊቀበለው አይገባም ብለዋል፡፡

የአረብ ሊግ "የአረብ የውኃ ካውንስል" በሚባለው ምክር ቤታቸው አማካኝነት በርካታ የውሃ አካላትን በስሩ አካቶ የአረብ ውኃ በሚል እየሰየመ "ከእኛ ውጭ ማንም መጠቀም አይችልም" የሚል ተቀባይነት የሌለውና አካሄድ እየተከተለ ነው ተናግረዋል።

ቱርክ የሚገኙ የኤፍራጠስና ጤግሮስ ወንዞችን፤ ዮርዳኖስን፣ የናይል ገባሮችን ከዛም አልፎ የዋቢ ሸበሌና ገናሌ ዳዋ ወንዞችን የአረብ ውኃ እንደሆኑ የተሳሳተ አስተሳሰብ እያራመደ መሆኑን በመጥቀስ ይህ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለውና ኢፍትሐዊ አካሄድ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው ፕሮጀክት ፍትሐዊና ምክንያታዊ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ፈቅ አህመድ፤ የግድቡ ግንባታ ሂደት ሉዓላዊ መብትንና ዓለም አቀፍ የውኃ ህግን የተከተለ መሆኑን ለዓለም በአግባቡ ማሳወቅ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ለዚህም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውዥንብር ውስጥ እንዳይገባና ትክክለኛውን መረጃ እንዲያውቅ በማድረግ የተሳሳተ መረጃ የሚነዙ አካላትን አካሄድ ማክሸፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገኝተን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙሪያ ውይይት አድርገናል።

ከከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር እና አመራሮቻቸው ጋር በአዲስ አበባ እና የዋሺንግተን ዲሲ የእህትማማችነት ስምምነት ወደ ተግባር እንዲለወጡ ለማስቻል ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደናል። በተለይ በመንግስትና የግል አጋርነት በሚገነቡ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከተማን መልሶ በማልማት፣ የተሻለ ገቢ አሰባሰብ፣ የውሃ ማከም፣ በትራንስፖርት፣ በዙሪያ ካሉ ከተሞች ጋር የልማት ስራዎች በማቀናጀት ላይ ልምዶችን በመቀመርና በመለዋወጥ በትብብር ለመስራት ተግባብተናል።

በመንግስት እና የግል አጋርነት በሚገነቡ፣ ከተማን መልሶ የማልማትና መልሶ በመጠቀም ስራዎችንም ጎብኝተል።