Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገኝተን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙሪያ ውይይት አድርገናል።

ከከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር እና አመራሮቻቸው ጋር በአዲስ አበባ እና የዋሺንግተን ዲሲ የእህትማማችነት ስምምነት ወደ ተግባር እንዲለወጡ ለማስቻል ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደናል። በተለይ በመንግስትና የግል አጋርነት በሚገነቡ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከተማን መልሶ በማልማት፣ የተሻለ ገቢ አሰባሰብ፣ የውሃ ማከም፣ በትራንስፖርት፣ በዙሪያ ካሉ ከተሞች ጋር የልማት ስራዎች በማቀናጀት ላይ ልምዶችን በመቀመርና በመለዋወጥ በትብብር ለመስራት ተግባብተናል።

በመንግስት እና የግል አጋርነት በሚገነቡ፣ ከተማን መልሶ የማልማትና መልሶ በመጠቀም ስራዎችንም ጎብኝተል።
“ሽፍታው ዋሻ”‼️

የባሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች አካል ነው። አቀበት የበዛው ጠመዝማዛው መንገድ። በተራራው አናት ዋሻዎች በኩራት ተጀቡነው ይገኛሉ። ከነዚህ ዋሻዎች ባንደኛው ታዛውን ያበጀ ሰብስቤ የተሰኘ ሽፍታ ነበር አሉ። ዋሻውም ከዚህ ሽፍታ ስያሜውን እንዳገኘ ይነገራል።

ይህ የሞት ዋሻ ለተጓዥ ምቹ አይደለም። የእናቶች ዋይታ የአባቶች ቁጭት በተደጋጋሚ ይደመጥበታል። እህህ አስብሎ የሚያስቃስት ከባድ ሕመም የሚያስታቅፍ ክፉ ነው። የሰው ደም እንደ ውሀ መጋት ለምዷል። የእልፎችን ሕይወት ያለ ርህራሄ ቀጥፏል።

ወላጅን ቀባሪ አሳጥቷል። ልጅን ያለ አሳዳጊ አስቀርቷል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ መገኛው ነው። ከባሌ ዞን አዲስ አበባም ይሁን ሻሸመኔ ለሚሄድ መንገደኛ....
https://www.press.et/?p=100712
ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሄደ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከተሞች ተካሂዷል።

ሰልፈኞቹ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ላይ የሚፈፀመውን ስም ማጥፋት በፅኑ በመቃወም ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት የገለጹት ሰልፈኞቹ  “ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የኢትዮጵያዊያን ዋስትና በመሆኑ ሁሌም ከሠራዊታችን ጎን እንቆማለን” ሲሉ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊትን የሚያጥላሉና የስም ማጥፋት የሚፈፅሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርበዋል።
የግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ፣ መልካም ዕድል‼️
የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች መዳረሻቸውን በጓንዦ ከተማ እንዲያደርጉ ለኢትዮጵያ አምራቾች ጥሪ ቀረበ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የጓንዦ ከተማን ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ለማቀናጀት መንግስት ፍላጎት ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጓንዦ ከተማ ከንቲባ ጉዎ ዮንጋንግ ባደረጉላቸው የእንኳን ደህና መጡ ግብዣ ላይ እንደተናገሩት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩ የበለጠ እንዲጠናከር በጓንዦና በኢትዮጵያ ከተሞች ማካከል ጉድኝት መፍጠር ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

የጓንዦ ከተማ 16 ሚሊዬን ነዋሪ ያላት ስትሆን የቻይና የቢዝነስ መናኸሪያ የሆነው ጓንዶንግ ግዛት ዋና ከተማ ናት፡፡

የከተማው ከንቲባ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች መዳረሻቸውን በጓንዦ እንዲያደርጉ ለኢትዮጵያ አምራቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጓንዦ በመብረር ሁለቱን አገሮች ብቻ ሳይሆን ቻይናና አፍሪካን አንዳስተሳሰረ ጠቅሰው በተለይም የኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በጓንዦ የሚያደርገውን በረራ ባለማቋረጡ አመስግነዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጓንዦ ቆይታቸው የኤሌክትሮኒክስ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና ከሃይል ማመንጫ ጋር የተያያዙ ኩባንያዎችን በመጎብኘት በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ጋብዘዋል፡፡