Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በግብርናው ዘርፍ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በውይይታቸው በአየር ንብረት ለውጥ፣ በምግብና የምግብ ደህንነት፣ በአፈር ጤንነትና በውሃ ሃብት አያያዝና አጠቃቀም፣ በግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ስራዎች፣ የገጠር የፋይናንስ አቅርቦትና አገልግሎትን ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ላይ በስፋት ተወያይተዋል፡፡

በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ በግብርናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክትና ፕሮግራሞች ላይ በሚሰሩት ስራ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በጣሊያን ሊጉሪያ፣ ቪያሌ ዲአወስታና ቱስካኒ ክልሎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላ በጄኖአ ከተማ ተከፈተ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ከ150 በላይ የሚሆኑ ከሶስቱ ክልሎችና ከጄኖአ ከተማ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የጄኖአ ከተማ አስተዳደርና አመራሮች፣ ትላልቅ ባለሀብቶችና የጄኖአ ወደብ አመራሮችና ተቆጣጣሪዎች በተገኙበት በጄኖአ ከተማ ስለኢትዮጵያ አሁናዊ ጉዳዮችና የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል።

በውይይቱ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታና አዲሱ የኢኮኖሚ ሪፎርም እና በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ እና የክብር ቆንስል ሆነው የተሾሙት አቶ ጃንፔሮ ሱቺ ሲሆኑ፣ በመድረኩ የጣሊያን የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አምባሳደር ጂዩሴፔ ሚስትሬታ የክብር እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል።

በመድረኩ በኢትዮጵያ በሎጂስቲክና ታዳሽ ኃይል ኢንቨስት እያደረጉ ያሉት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስላለው ሰላም አስተማማኝና ሰፊ ገበያ ያለ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የጣሊያን ንግድ ማህበር የሆነው Confindustria Assafrica ተወካዮች ማንኛውንም የኢንቨስትመንትና ንግድ እንቅስቃሴ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለማጠናከር የሚፈለግባቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#የአፍሪካ ቀን‼️

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት የተመሠረተበት 60ኛ ዓመት በእስራኤል ተከበረ።

በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተስፋዩ ይታይህ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት ምስረታ ላይ የመሪነት ሚና እንደነበራት አስታወሰው አሁንም ለህብረቱ ግቦች መሳካት ለምታደርገው አስተዋጽኦ በሚመለከት ገለፃ አድርገዋል።

በዕለቱ ባህላዊ ምግብ፣ ሙዚቃና የሀገሪቱን መልካም ገፅታ የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ምስሎች ለእይታ ቀርበዋል። የተለያዩ የአፍሪካ አገራትም የየራሳቸውን የባሕል ምግብና ሙዚቃ ትርኢት ለታዳሚዎች አቅርበዋል።

ተቀማጭነታቸው በእስራኤል ያደረጉ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የእስራኤል የሠራተኛ ሚኒስትር፣ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ታላላቅ ኩባንያ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በዓባይ ሃይቅ ላይ አሳ ማስገር ተጀምሯል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ላይ አሳ ማስገር መጀመሩንና በቀን በአማካኝ አሥራ ሁለት ኩንታል የዓሣ ምርት እየተገኘ መሆኑን የቤንሻንጉል ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ካሊፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ክልሉ በአንፃራዊነት ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የዓሣ ምርት የሚገኝበት ነው። የክልሉ ነዋሪዎችም የዓሣ ምርቱን ለምግብነት ብቻ ሳይሆን ለገበያ በማዋል በገቢ ምንጭነት ይጠቀሙበታል።
የቤንሻንጉል ክልል የዓባይ ግድብ መገኛ መሆኑን ያወሱት ኃላፊው፤ አሁን ላይ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100852
እንጀራ ከማጀት - ወደ ኢንዱስትሪ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ለሚ የእንጀራ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተንጣለለ ሥፍራ ላይ በውስጣቸው በርካታ የእንጀራ መጋገሪያ ብሎኮችን ይዞ የተገነባ ማዕከል ነው፡፡ ብሎኮቹ እያንዳንዳቸው እስከ 250 የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ በውስጣቸው ይዘዋል፡፡
ይህ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንጀራን ወደኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስገባት ብሎም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋን ነዋሪዎች ለመደገፍ ከባለሃብቶች በማሰባሰብ የተገነባ ነው፡፡ ማዕከሉ በአሁኑ ወቅትም ሙሉ ለሙሉ ወደስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የማዕከሉ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100887