Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአገልግሎት ሒሳብ አሰባሰብና ክፍያ በሕግ እንዲመራ ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የክፍያ ተመን መመሪያን በአስቸኳይ እንዲያጸድቅ እና ተሰብሳቢ ሂሳብ በሦስት ወራት ጊዜ እንዲሰበስብ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2013 ዓ.ም የኦዲት ግኝትን ገምግሟል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ፤ አገልግሎቱ ባልጸደቀ ህግ ሂሳብ መሰብሰቡና ክፍያ መፈጸሙ ትክክል አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳይፈቀድ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100965
በመዲናዋ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከ17 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ በመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከ17 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተቋም ደረጃ 200 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መዘጋጅቱን አስታውቋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ከ17 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመዲናዋ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100982
"በቻይና የተደርገው ኦፊሴላዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር እድል የሰጠ ነው"
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
**********************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር እድል የሰጠ መሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታወቀ።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ክንውኖችን አሰመልክተው በሰጡት መግለጫ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ኦፊሴላዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ይህም የሁለቱን አገራት ትብብርና ወዳጅነት ወደ ላቀ ስኬታማ ደረጃ ለማሸጋገር እድል የሰጠ ነው ብለዋል።


የጉብኝቱ አላማ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር፣ ቻይና ለኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አመንጪ እንደምሆኗ የአገሪቱ ባለሀብቶች መዋእለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ለማድረግ እንዲሁም ታሪካዊውን ግንኙነት የሚመጥን ውክልና እንዲኖር ኤምባሲ መርቆ ለመክፍት እንደሆነ በመግለጫቸው ገልጸዋል።


ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ጋር መምክራቸውን በመጥቀስ፣ በዚህ ወቅትም ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በአለም አቀፍ ግንኙነት የበለጠ መተሳሰር ፍላጐት ማሳየቷን ተናግረዋል።

በአዲሱ ገረመው
የልጅነት ልምሻን በዘላቂነት ለመከላከል የክትባቱን ተደራሽነት ማስፋት ይገባል
****************************
(ኢ ፕ ድ)

የልጅነት ልምሻን በዘላቂነት ለመከላከል የፖሊዮ ቫይረስ ክትባትን ተደራሽነት ለማስፋት እንደሚሰራ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የፖሊዮ ቫይረስ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ላይ ያከናወነውን ጥናትና የተገኙ ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት በትናንትናው ዕለት አቅርቧል።

በሀገሪቱ የሚከናወኑ የልጅነት ልምሻ ቫይረስ ዳሰሳ ጥናት መቀዛቀዝ፣ በቆላማ አካባቢዎች ያለው የድንበር ወሰን ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በርካታ መሆኑ፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች መከሰት በጤናው ዘርፍ ላይ ተግዳሮት እንደሚሆኑ በጥናቱ ተገልጿል።

ጥናቱ በቀረበበት ወቅት የጤና ሚኒስቴር የእናቶች ህፃናትና ወጣቶች ዘርፍ መሪ ዶክተር መሰረት ዘላለም እንደተናገሩት፤ በሽታው ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100987
የግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልእክት‼️ 

በሰሞኑ ዝናብ ቦረና ላይ በስፋት የእንስሳት መኖ እና ሰሊጥ ተመርቷል። ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከድርቅ ወደ አምራችነት መቀየሩ ተስፋ ሰጪ ነው። ውኃን በማቆርና በመቆጠብ ብልሐት ከተጠቀምን የችግርን ጊዜ ሳንቸገርበት እናልፈዋለን።
አገልግሎቱ ለእጀባ፣ ለበረራ ደኅንነት መኮንኖችና አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመረቀ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለሪፐብሊካን ጋርድና ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ እጀባ ፣ለበረራ ደኅንነት መኮንኖችና አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመርቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፥ በትብብርና በአጋርነት አብረውት ከሚሰሩ የውጭ መረጃና ደኅንነት ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ስልጠና በዋናነት በቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ፣ በፈንጂ ምህንድስና ፣ በድሮን አጠቃቀም ቅየሳና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፥ አደጋ መቼና እንዴት እንደሚከሰት በእርገጠኝነት መናገር ባይቻልም በማያቋርጥ ስልጠናና ልምምድ ብቁና ሁልጊዜም ዝግጁ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ በመሆኑ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ይህ አይነቱን ስልጠና አዘጋጅቷል።
በመሆኑም አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሀገር መሪዎችን ፣ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ከአደጋ የመጠበቅ እንዲሁም የበረራ ደኅንነትን የማረጋገጥ ተልዕኮዎችን ለመፈጸም የሰው ኃይሉን በተከታታይ ስልጠና እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።
ሰልጣኞችም በስልጠና ወቅት በንድፈ ሃሳብ፡ በተግባርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስልጠና ማግኘታቸው ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬታማ አፈፃፀም ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድወሰን ካሳ በበኩላቸው የቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ መኮንኖች ከፍተኛ ደኅንነታዊ አንድምታ ያላቸውን ግለሰቦች ደኅንነት ለመጠበቅ ተገቢውን ዕውቀት፣ ክህሎት፣ አስተሳሰብ እና ስነምግባር ሊጨብጡ ይገባል ብለዋል።
እያንዳንዱ የቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ ስምሪት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ እንዲሁም ከሚገመቱና ካልተጠበቁ ስጋቶች እና ጥቃቶች የሀገር መሪዎችን፣ ቁልፍ የመሰረት ልማት ተቋማትን በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ዕቅድ አዘጋጅቶ የመሰማራት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም ገልፀዋል።
በብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በንደፈ-ሃሳብና በተግባር የተሰጠውን ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኞችም በስልጠና ያገኟቸውን ዕውቀትና ክህሎቶች በተግባር ልምምድ ማሳየታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመላክቷል።