የልጅነት ልምሻን በዘላቂነት ለመከላከል የክትባቱን ተደራሽነት ማስፋት ይገባል
****************************
(ኢ ፕ ድ)
የልጅነት ልምሻን በዘላቂነት ለመከላከል የፖሊዮ ቫይረስ ክትባትን ተደራሽነት ለማስፋት እንደሚሰራ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የፖሊዮ ቫይረስ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ላይ ያከናወነውን ጥናትና የተገኙ ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት በትናንትናው ዕለት አቅርቧል።
በሀገሪቱ የሚከናወኑ የልጅነት ልምሻ ቫይረስ ዳሰሳ ጥናት መቀዛቀዝ፣ በቆላማ አካባቢዎች ያለው የድንበር ወሰን ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በርካታ መሆኑ፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች መከሰት በጤናው ዘርፍ ላይ ተግዳሮት እንደሚሆኑ በጥናቱ ተገልጿል።
ጥናቱ በቀረበበት ወቅት የጤና ሚኒስቴር የእናቶች ህፃናትና ወጣቶች ዘርፍ መሪ ዶክተር መሰረት ዘላለም እንደተናገሩት፤ በሽታው ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100987

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልእክት‼️
በሰሞኑ ዝናብ ቦረና ላይ በስፋት የእንስሳት መኖ እና ሰሊጥ ተመርቷል። ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከድርቅ ወደ አምራችነት መቀየሩ ተስፋ ሰጪ ነው። ውኃን በማቆርና በመቆጠብ ብልሐት ከተጠቀምን የችግርን ጊዜ ሳንቸገርበት እናልፈዋለን።

አገልግሎቱ ለእጀባ፣ ለበረራ ደኅንነት መኮንኖችና አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመረቀ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለሪፐብሊካን ጋርድና ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ እጀባ ፣ለበረራ ደኅንነት መኮንኖችና አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመርቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፥ በትብብርና በአጋርነት አብረውት ከሚሰሩ የውጭ መረጃና ደኅንነት ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ስልጠና በዋናነት በቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ፣ በፈንጂ ምህንድስና ፣ በድሮን አጠቃቀም ቅየሳና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፥ አደጋ መቼና እንዴት እንደሚከሰት በእርገጠኝነት መናገር ባይቻልም በማያቋርጥ ስልጠናና ልምምድ ብቁና ሁልጊዜም ዝግጁ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ በመሆኑ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ይህ አይነቱን ስልጠና አዘጋጅቷል።
በመሆኑም አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሀገር መሪዎችን ፣ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ከአደጋ የመጠበቅ እንዲሁም የበረራ ደኅንነትን የማረጋገጥ ተልዕኮዎችን ለመፈጸም የሰው ኃይሉን በተከታታይ ስልጠና እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።
ሰልጣኞችም በስልጠና ወቅት በንድፈ ሃሳብ፡ በተግባርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስልጠና ማግኘታቸው ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬታማ አፈፃፀም ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድወሰን ካሳ በበኩላቸው የቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ መኮንኖች ከፍተኛ ደኅንነታዊ አንድምታ ያላቸውን ግለሰቦች ደኅንነት ለመጠበቅ ተገቢውን ዕውቀት፣ ክህሎት፣ አስተሳሰብ እና ስነምግባር ሊጨብጡ ይገባል ብለዋል።
እያንዳንዱ የቪ አይ ፒ ደኅንነት ጥበቃ ስምሪት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ እንዲሁም ከሚገመቱና ካልተጠበቁ ስጋቶች እና ጥቃቶች የሀገር መሪዎችን፣ ቁልፍ የመሰረት ልማት ተቋማትን በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ዕቅድ አዘጋጅቶ የመሰማራት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም ገልፀዋል።
በብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በንደፈ-ሃሳብና በተግባር የተሰጠውን ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኞችም በስልጠና ያገኟቸውን ዕውቀትና ክህሎቶች በተግባር ልምምድ ማሳየታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመላክቷል።

“ቦረና ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከድርቅ ወደአምራችነት መቀየሩ ተስፋ ሰጪ ነው”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
ለአምስት ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ በድርቅ ተጎድቶ የነበረው የቦረና ዞን ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከድርቅ ወደ አምራችነት መቀየሩ ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
በቅርቡ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ 96 ሺህ 189 ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ በሰሞኑ ዝናብ ቦረና ላይ በስፋት የእንስሳት መኖ እና ሰሊጥ ተመርቷል። ውሃን በማቆርና በመቆጠብ ብልሐት ከተጠቀምን የችግርን ጊዜ ሳንቸገርበት እናልፈዋለን።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101037

የቦሌ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ 6 የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡
የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከተገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተሳስሮ ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ከሚወስደው የቀለበት መንገድ ጋር በተለያዩ መጋጠሚያዎች የሚያገናኙ የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ የቦሌ ሚካኤል የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታ እውን እንዲሆን ምክንያት ሆኗል፡፡
ፕሮጅክቱ ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አሰር ኮንስትራክሽን የተባለ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጭ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ በሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ኩባንያ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ቀደም ሲል 600 ሜትር ርዝመት ያለው የቦሌ ሚካኤል ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል 3.8 ኪሎ ሜትሩ የመጀመርያ አስፋልት ደረጃ ለብሷል።
በተጨማሪ በቀሪው 200 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡