Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመረቀው የአንድነት ቤተ መዛግብት በፎቶ‼️
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመረቀውን የአንድነት ፓርክ የዕጽዋት ማዕከልን በፎቶ‼️
የቃሊቲ- ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ‼️

👉 አጠቃላይ አፈጻጸሙ 62 በመቶ ደርሷል
👉 መንገዱን እስከ ሰኔ 30 ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ አጠቃላይ አፈጻጸም 62 በመቶ እንደደረሰ እና መንገዱን እስከ ሰኔ 30 ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። የመንገዱ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር የሚሆነው የግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ እንደተደረገለትም ተገልጿል።

አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት የመንገዱን የግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት በማልበስ እስከ ሰኔ መጨረሻ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በሚሰራው ሥራ እስከ አሁን ዘጠኝ ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት ንጣፍ ማልበስ ተችሏል።
https://www.press.et/?p=101350
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር ዛሬ ተገናኝተናል። በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን።
ድርጅቱ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ለማስፋትእንደሚሰራ አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የጀርመን ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ)ኢትዮጵያ ከ2011ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር ስኬታማ የሆነችበትን አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የሁለተኛውን ምዕራፍ ለማጠናከር የሚያግዝ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ:: ድርጅቱ የግብርናውን ሥራ የሚያግዝ የስልጠና እና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ከመንግሥት ጋር በመሥራት የቆየ መሆኑንም አስታውቋል::

በጂ አይ ዜድ የፕሮግራም ኮፖናንት ማኔጀር አቶ መላኩ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) እንደገለጹት፤ድርጅቱ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ከመንግሥት ጋር በቅርበት እያከናወነ ያለውን ሥራ ለማጠናከር ከአረንጓዴ አሻራ ጋር የሚሄድ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ይገኛል:: በኢትዮጵያ ለአራት ተከታታይ አመታት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የነበሩት መልካም ተሞክሮዎች፣ክፍተቶችና ተግዳሮቶች ተቀምረው አዲስ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም...

https://www.press.et/?p=101392