የቃሊቲ- ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ‼️
👉 አጠቃላይ አፈጻጸሙ 62 በመቶ ደርሷል
👉 መንገዱን እስከ ሰኔ 30 ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ አጠቃላይ አፈጻጸም 62 በመቶ እንደደረሰ እና መንገዱን እስከ ሰኔ 30 ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። የመንገዱ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር የሚሆነው የግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ እንደተደረገለትም ተገልጿል።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት የመንገዱን የግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት በማልበስ እስከ ሰኔ መጨረሻ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በሚሰራው ሥራ እስከ አሁን ዘጠኝ ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት ንጣፍ ማልበስ ተችሏል።
https://www.press.et/?p=101350

ድርጅቱ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ለማስፋትእንደሚሰራ አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የጀርመን ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ)ኢትዮጵያ ከ2011ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር ስኬታማ የሆነችበትን አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የሁለተኛውን ምዕራፍ ለማጠናከር የሚያግዝ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ:: ድርጅቱ የግብርናውን ሥራ የሚያግዝ የስልጠና እና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ከመንግሥት ጋር በመሥራት የቆየ መሆኑንም አስታውቋል::
በጂ አይ ዜድ የፕሮግራም ኮፖናንት ማኔጀር አቶ መላኩ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) እንደገለጹት፤ድርጅቱ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ከመንግሥት ጋር በቅርበት እያከናወነ ያለውን ሥራ ለማጠናከር ከአረንጓዴ አሻራ ጋር የሚሄድ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ይገኛል:: በኢትዮጵያ ለአራት ተከታታይ አመታት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የነበሩት መልካም ተሞክሮዎች፣ክፍተቶችና ተግዳሮቶች ተቀምረው አዲስ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም...
https://www.press.et/?p=101392

ኢትዮጵያ እና ብራዚል ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማሙ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና ብራዚል ያላቸውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማምተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መክረዋል።
ኢትዮጵያ ከብራዚል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጊዜው አሁን መሆኑን የገለፁ ሲሆን ኢትዮጵያ በብራዚል ዳግም ኤምባሲዋን መክፈቷም ግንኙነቱን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አቶ ደመቀ መኮንን አስታውሰዋል።
ብራዚል በኢትዮጵያ በዘላቂ የደን ልማት አስተዳደር በጥጥ ምርትና በአፈር ጥበቃ ላይ ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለቸው መልካም አበርክቶም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት፣ አቪዬሽን፣ ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ በአከባቢ ጥበቃ እና በማዕድን እና ኢነርጂ ከብራዚል ጋር በትብብር ለመሥራት ያላትን ፍለጎት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ በበኩላቸው፣ አገራቸው በስፖርት እና የተለያዩ መስኮች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ጠቅሰው ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባሻገር በባለ ብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መድረኮች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ቀጣይ የፖለቲካ ውይይት እንዲካሄድም መግባባት ላይ መደረሱን የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።